ወደ ኢትዮጵያ እመጣለሁ በመንግሥት ደረጃ ተጋብዣለሁ። – ተስፋዬ ገብረአብ

ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ስቶክሆልም እያለ ነበር ያነጋገርነው። ስቶክሆልም የተገኘው አዲሱ መጽሐፉን [የቲራቮሎ ዋሻ] ለማስተዋወቅ እንደሆነ ነግሮናል። ይህ አዲሱ ሥራው ዘጠነኛ መጽሐፉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ባሳተማቸው መጽሐፍቶቹ የተነሳ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ አንባቢያን ስሙን ያነሱታል፤ ይጥሉታል። እርሱም ይህንን ያውቀዋል።

ስንት መት ሆነህ?

እድሜዬ ማለትህ ነው?

አዎ

ልክ 50፤

አረጀህ?

አዎ እያረጀሁ ነው። ለመሞት 50 ዓመት ብቻ ነው የቀረኝ [ሳቅ]

ከሀገር ከወጣህ ትንሽ ረዘም ያለ ጊዜ ስለሆነህ ከአዲስ አበባ፣ ከኢትዮጵያ ምንድን ነው የሚናፍቅህ?

የሚናፍቀኝ አንድ ነገር ብቻ ነው። ቢሾፍቱ ሐይቅ፤ ሆራ፣ የአድዓ መልከዓ ምድር፣ ባቦ ጋያና ጋራ ቦሩ የተባሉ በልጅነት የሮጥኩባቸው መስኮች፣ ሐይቆች፤ እነ በልበላ ወንዝ፣ እነዚህን ድጋሚ ማየት ይናፍቀኛል።

በአንድ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ትመጣለህ ተብሎ በሰፊው ሲወራ ነበር፤ ቀረህ?

አይ አልቀረሁም። አልሟላ እያለኝ ዘገየ እንጂ አልቀረሁም፤ እመጣለሁ። በመንግሥት ደረጃም ተጋብዣለሁ። ስላልሞላልኝ ነው እስካሁን ያልመጣሁት።

 

ስለዚህ ቲኬትም ቀንም አልቆረጥክም ማለት ነው?

ቀንም አልቆረጥኩም፤ ቲኬትም አልቆረጥኩም። ባለፈው ግን ወደ ስቶክሆልም ስሄድ በአዲስ አበባ በኩል አልፌያለሁ።

የአማርኛ ሥነጽሑፍን የሚያጠኑ ሰዎች በራዎችህ የት ስፍራ ላይ እንዲመድቡህ ነው የምትፈልገው? ከነ በዓሉ . . .

እንደዚህ አይነት ነገር አስቤ አላውቅም። መጻፍ እወዳለሁ፤ ያመንኩበትን ነገር እጽፋለሁ። ሰዎች ቢወዱትም ባይወዱትም በፍፁም አስጨንቆኝ አያውቅም። ካልወደዱትና ከወረወሩት የሰዎቹ ፈንታ ነው። እኔ ማድረግ ያለብኝ ጥሪዬን መከተል ብቻ ነው ብዬ ነው የማስበው።

አንባቢዎች አልወደድነውም ያሉህ ራ አለህ?

ሥራዎቼን በጣም የሚወዱትና በጣም የሚጠሉት ነው የሚያጋጥሙኝ። መካከል ላይ የሆኑ አይገጥሙኝም። ምክንያቱ አይገባኝም።

የሚወዱት ሰዎች ለምን ወደድነው እንዳሉህ ኋላ ላይ እናወራለን። አልወደድነውም ያሉህ ሰዎች ምክንያታቸው ምንድን ነው?

እነርሱ የሚሉኝን ምክንያት አይደለም መናገር ያለብኝ፤ እኔ ለምን እንደጠሉኝ ሳስብ ያልተለመዱ ነገሮችን ስለምፅፍ ነው። ለምሳሌ የቡርቃ ዝምታን በጣም የሚወዱት ሰዎች አሉ፤ በጣምም የሚጠሉት ሰዎች አሉ፤ ለምን ይጠሉታል ብዬ ሳስብ በአማርኛ የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ያልተለመዱ ገፀባሕሪያት እዚያ ውስጥ አሉ።

በአማርኛ የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ የተለመደው ጫላ ወይንም ጫልቱ የሚል ስም ለቤት ሠራተኛና ለዘበኛ ሲሰጥ ነው፤ ኦሮሞ ስም ያለው ዋና [ዐቢይ] ገፀባህሪ ሆኖ አያውቅም። ከመነሻው በዚህ የተከፉ ሰዎች አሉ። የደነገጡ ሰዎች አሉ። የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ሥራዎች የሆኑ ልብወለዶችን ሰብስበህ ተመልከታቸው። ከፊያሜታ በስተቀር [የበዓሉ ግርማ ኦሮማይ ረዥም ልብወለድ ገፀባህሪ] በጠቅላላ አማራ ናቸው። ወይንም የአማርኛ ስም ያላቸው ናቸው።

ይህ ነው የተለመደው። ፀሐፊው ከኦሮሞም ይሁን ከትግራይም ይሁን በተለምዶ የአማርኛ ስም ነው ለገፀባህሪያቱ የሚሰጠው። ይህ የእኔ አጀማማር ወጣ ያለ ስለነበር ከመነሻው ሰዎች እንዳልወደዱት አይቻለሁ።

አንተም ጠቀስ አድርገሀዋል። የአማርኛ ሥነጽሑፍ ላይ ስማቸው የገነነ ደራሲን ከሌላ ብሔር የመጡ ናቸው። አሁን አንተ የምትላቸውን ጉዳዮች በራዎቻቸው ውስጥ ለማንሳት ለእነርሱ ለምን የከበደ ይመስልሀል?

አልከበዳቸውም፤ ፈሩ። ኢትዮጵያ ላይ ከኦርቶዶክስ ውጪ ሊነግሥ አይችልም። አሁን በምናወራው ጉዳይ ደግሞ በዚህ መልኩ ነበር የሚፃፈው። ለአብነት በዓሉ ግርማን እንውሰድ።

ከአድማስ ባሻገር በሚለው ሥራው ላይ ሉሊት ታደሰ የምትባል ገፀባህሪ በዋና ገፀባህሪነት ተስላለች። ይህቺን ገፀባህሪ ከአበራ ወርቁ ጋር አድርጎ ነው የሚያስተዋውቀን።

ከአበራ ጋር ተኝተው ሳሉ ለሊት ላይ ለአበራ ስሟን መቀየሯን ትነግራዋለች። ጫልቱ ነው ስሟ። ጫልቱ ተብዬ አዲስ አበባ ላይ ልኖር አልችልም። ለዚህ ነው የቀየርኩት ትለዋለች።

ስም መቀየር የከተሜነት የዘመናዊነት ጣጣ አይመስልህም?

የከተሜነት ጣጣ ብቻ አይደለም። ለምሳሌ ከአንድ የጎንደር የገጠር አካባቢ ወይንም ከዚያው ከደብረሲና የገጠር አካባቢ የመጣች ሴት በተመሳሳይ ከበከጆ ከመጣች ሴት ጋር ተመሳሳይ የገጠሬነት ጭቆና ይደርስባቸዋል። ከበከጆ የመጣችው ላይ ግን ድርብ ይሆናል። ድርብ ስልህ ገጠሬነት አንድ መሳቂያ መሳለቂያ ነው፤ ማንነት ደግሞ ሌላ መሳቂያ መሳለቂያ ያደርጋታል።

ያቺ ከገጠር የመጣችው ገጠሬነቷ ብቻ ነው መሳለቂያ የሚያደርጋት፤ እንጂ ማንነቷ መሳለቂያ አያደርጋትም። ስለዚህ ከገጠር የሚመጡ ሰዎች ከፍተኛ ተፅዕኖና ችግር ይደርስባቸዋል። ሌሎች ገጠሬዎች ግን ድርብ ችግር ያጋጥማቸዋል። መራራ የሚያደርገው ይሄ ነው። ይህ ነው የማንነት ጭቆናን የከፋና መራራ የሚያደርገው።

በተለያዩ መንገዶች ስንመለከተው ከተሜነት የራሱ መገለጫ አለው። አንተ እነዚህ ከገጠር መጡ የምትላቸው ሰዎች በስማቸው ብቻ ነው ተገፉ ነው የምትለው ወይንስ በሌሎች ባህሎቻቸውም ተገፍተዋል ትላለህ?

የስም ለውጥ የከተሜ ብቻ አይደለም። የኦነግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ ሆሮ ጉዱሩ ሀገራቸው ነው። የጥንት የቅድም አያታቸው ሀገር ነው ሆሮ ጉዱሩ። ነገር ግን እዛው ሆሮ ጉዱሩ ላይ ነው ስማቸውን እንዲለውጡ የተገደዱት። ሲወለዱ ስማቸው መገርሳ ነበረ። ተማሪ ቤት መገርሳ የሚባል ስም ይዘህ አትገባም ተባሉና ፍሬው ተባሉ። በኋላ ነው ይህ ዳውድ የሚለው ስማቸው የመጣው።

ሩቅ ምናስኬደን አባዱላ ገመዳም እንደዛው ነው። ተገዶ ነው ምናሴ የሚለውን ስም ይዞ የነበረው። እርሱም ሦስተኛ ስሙ ነው አሁን። ኩማ ደመቅሳም እንደዛው። የብዙ ሰዎች ታሪክ የሚያሳየን በዚያው በተወለዱበት አካባቢ ሳይቀር ተፅዕኖ እንደሚደርስባቸው ነው።

ወደ ደራሲያኑ እስቲ እንመለስ…

ርዕሰ ጉዳያችን ተጠምዝዞ ወደዚህ መጣ እንጂ እነስብሀት ገብረእግዚአብሄርም ሆኑ ሌሎች በወቅቱ የነበሩ ደራሲያን ለምን አላሰቡትም ለሚለው ጊዜው የሚፈቅድ አልነበረም። እኔ ያደረኩትን ለማድረግ ወቅቱ ይፈቅድ ስላልነበር እነበአሉ በገደምዳሜ፣ በጨረፍታ ይነኩት ነበር እንጂ ቀጥታ እንደዚያ ማድረግ አይቻልም።

የስብሀት ገፀባህሪያትን፣ ሥራዎች መለስ ብለህ ብትቃኝ ይሁነኝ ተብሎ ላይሆን ይችላል ለገፀባህሪያቱ ያንን ስም የሰጣቸው፤ ነገር ግን ሰርቅ ዳንኤል ከእንደዚህ አይነት ነገር ለመዳን በቆንጆዎቹ ረዥም ልብወለድ ላይ በሙሉ ለገፀባህሪያቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ስም ሰጥቶ እናገኛዋለን።

ሰርቅ ዳንኤል ከእንዲህ አይነት እሰጥ አገባ ለመዳን ነው ብሎ ነው ብለን በድፍረት መናገር እንችላለን?

ለመዳን ብሎ ነው። በፍፁም ሳያስበው ጠቅላላ የመጽሐፍ ቅዱስ ስም ሊያደርግ አይችልም። እንዲህ ያለ የብሔር ችግር ውስጥ ላለመግባት ነጠላቸው ማለት ነው- ገፀባህሪያቱን።

ምክንያቱም ሳሙዔል የሚለው የማንም አይደለም። ክርስቲያን የሆነ በሙሉ ሳሙዔል ይላል። በዚህ መንገድ [ከብሔር ጉዳይ] ሊያመልጥ ሞክሯል። እነሐዲስ አለማየሁ የአካባቢያቸውን ስም ስለሚሰጡ ችግር የለባቸውም። ብርሃኑ ዘሪሁን ችግር አልነበረበትም። የሚፅፋቸው ፅሁፎችም በዚያው አካባቢ ስለነበሩ።

ስለዚህ የጠየቅከኝ ጥያቄ ለምንድን ነው አንባቢያን የቡርቃ ዝምታ ላይ ጥላቻ ያደረባቸው ለሚለው ይህ ያልተነካው ያልተደፈረው ነገር ላይ በመግባቴ ትንሽ ይልለመዱት ጉዳይ ስለሆነባቸው ይሆናል እንጂ የቡርቃ ዝምታን ሚዛናዊ ሆነህ ስታነበው ሕዝብና ሕዘብን የሚያጋጭ መጽሐፍ አልነበረም።

ራህን ወደድነው የሚሉህ አንባቢያን ለመውደዳቸው የሚሰጡት ምክን ምንድን ነው?

ለምሳሌ የስደተኛው ማስታወሻ ላይ ጫልቱ እንደ ሄለን የሚል ፅሑፍ ፅፌያለሁ። ብዙ ሰዎች እንባ እያነቃቸው እንዳነበቡት ይናገራሉ። የጫልቱን ታሪክ ለምን ወደዳችሁት ስላቸው እኔ ያለፍኩት ልክ ጫልቱ ባለፈችበት መንገድ ነው ያሉኝ ይበዛሉ።

በርካታ መጻሕፍትን ፅፈሀል። በጣም የሚታወቁት የቡርቃ ዝምታ፣ የቢሾፍቱ ቆሪጦች፣ የደራሲው ማስታወሻ፣ የስደተው ማስታወሻ የጋዜጠኛው ማስታወሻ ናቸው። የመጀመሪራህ ግን ያልተመለሰው ባቡር የሚል ነው አይደል?

ልክ ነህ።

በስም የጠቀስኳቸው መጻህፍት በዋናነት የኦሮሞ ፖለቲካን የታሪካቸው ማጠንጠኛ ያደርጋሉ። ያልተመለሰው ባቡር የሚለው መፅሐፍህም እንደነዚሁራዎችህ ያለ ነው ጭብጡ?

አይ፤ ያን ጊዜ ፖለቲካሊ ኮንሺየስ [በፖለቲካ የበሰልኩ] አልነበርኩም። ያንን ስጽፍ የ24 ዓመት ልጅ ነኝ። ባላሳትመው ይሻል ነበር። እንደው በመቸኮል ያሳተምኩት መጽሐፍ ነው።

ለምንድን ነው ባላሳትመው ያልከው?

የሥነ ጽሑፍ ይዘቱ ደካማ ነው። የመጽሐፉ አወቃቀር ጭብጡ ደካማ ነው። ከዚያ በተሻለ መስራት እችል ነበር። ብዙ ያልታሰበበት የልጅነት ሥራ ነው ብዬ ነው የማስበው። ቢሆንም አልጠላውም።

የፖለቲካ ንቃተ ሕሊናህ ከፍ ብሎ ይህ የኦሮሞ ጉዳይ እያሳሰበኝ ይመ ጀመር የምትልበት የታሪክ አጋሚ አለ?

አሁን በምትለው ረገድ አስቤ አላውቅም። ግን ከማንበብ ብዛት፣ ወደ ሕብረተሰቡ ጠጋ ብለህ ከማዳመጥ ብዛት፣ የተማርኩባቸው ጊዜያት ከ25 ዓመቴ በኋላ ይመስለኛል።

ያ ማለት ከውትድርና በኋላ ማለት ነው?

ከ25 ዓመት እድሜ በኋላ ማለት የፕሬስ መምሪያ ኃላፊነት ሥራዬን ትቼ የእፎይታ መጽሔት ዋና አዘጋጅ በነበርኩበት ጊዜ ማለት ነው።

በኢህአዴግ ውስጥ ጥሩ ተጠቃሚ ነበርክ። በርዓቱ ደስተኛ ስላልነበርክ ነው ማለት ነው እነቢሾፍቱ ቆሪጦችን እነየቡርቃ ዝምታን ለመጻፍ የተነሳሀው?

ተጠቃሚ የሆንኩበት ጊዜ የለም። ጋዜጠኛ ነው የነበርኩት።

ባለስልጣን ነበርክ

ባለስልጣን ነበርኩ። ሁለት ዓመት የፕሬስ መምሪያ ኃላፊ ነበርኩ። ነገር ግን ባለስልጣን መሆን ተጠቃሚ መሆን ማለት አይመስለኝም።

በጣም አስቸጋሪ ሥራ ነው የነበረው። ስለዚህ የፕሬስ መምሪያ ኃላፊ ከማለት ይልቅ ወታደርነት በለው። ወያኔ በጣም የተጠላ ሥርዓት ነበር። በተጠላ ሥርዓት ውስጥ በዚያ ከባድ ቦታ ላይ መመደብ ቅጣት ነው እንጂ ምቾት ወይንም ተጠቃሚነት አይመስለኝም።

ወታደር ከነበርክበት ጊዜና የፕሬ መምሪያ ኃላፊ ከነበርክበት ወቅት ስለማህበረሰቡ የተሻለ እንዳውቅ እድል ሰጥቶኛል የምትለው የትውን ነው?

ወታደር አልነበርኩም እኔ። አስራ ዘጠኝ ቀን ብቻ ነው በሥራ ላይ የነበርኩት። ስለዚህ ወታደር ነበርኩ ለማለት አይቻልም። ከወያኔ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ደግሞ ጋዜጠኛ ነው የነበርኩት።

ስለዚህ ሙሉ ሕይወቴን በጋዜጠኝነት ነው ያሳለፍኩት እያልከኝ ነው?

በጦርነት ውስጥ ያሳለፍኩት አስራ ዘጠኝ ቀን ብቻ ነው፤ ሌላውን ጋዜጠኛ ሆኜ ነው ያሳለፍኩት። ሌላው የ’ጋዜጠኛው ማስታወሻ’ ላይ የተገለፀ ስለሆነ እዚህ መድገም ብዙ አያስፈልግም።

መጽሐፍህ ላይ ነሳሀቸው ጉዳዮችን አሁን ካለው የፖለቲካ ሁኔታ አንጻር ስታቸው መልስ እገኙ ነው ትላለህ?

እላለሁኝ። በተለይ የኦሮሞ ጥያቄ ፤ እኔ የቡርቃ ዝምታን ስፅፍ ወያኔን አላስደሰተውም ነበር። ምክንያቱም ኦሮሞ ማንም የበላይ አያስፈልገውም። በኦሮሞነቱ መደራጀትና መኖር ካለበት በትክክል ኦሮሞን የሚወድ ኢትዮጵያን የሚወድ ሊመራው ይገባል። እንጂ አቅም በሌላቸው አሽከሮች ሊዘወር አይገባም የሚል መልዕክት ነው የሚያስተላልፈው የቡርቃ ዝምታ። እና ቁጭቴን ነው የገለፅኩት። ቡርቃ ዝም አለ ስል የኦሮሞ ሕዝብ ዝም አለ ማለቴ ነበረ።

የኦሮሞ ወጣቶች በቄሮ ቃሬ አማካኝነት ተነስተው ሀገሩን ሲያጥለቀልቁት የቡርቃ ወንዝ ከተደበቀበት ወጣ ብዬ እንደተሳካለት ሰው ራሴን ቆጥሬያለሁ። የኦሮሞ ወጣቶችም እኔን እንደሰሙኝ መጽሐፌን እንዳነበቡ ማወቄ የበለጠ ሞራል ሰጥቶኛል።

ህ ትግል የበኩሌን አስተዋጽኦ አድርጌለሁ ትላለህ?

አይ ትእቢተኛ አይደለሁም።

በትዕቢት አይደለም። አስተዋፅኦን በመቁጠር አንፃር ነው ያልኩት

ወደ አስተዋፅኦ ስንመጣ አንዲት ትልቅ የኦሮሞ እናት ዱላ ይዛ፣ ከፖሊሱ ፊት ቆማ ስትጮህ ስታይ የእኔ አስተዋፅኦ ከእርሷ ያነሰ ነው። ለዚህ ትግል አስተዋፅኦ ያደረጉ በርካታ ሰዎች አሉ፤ እኔም ከእነርሱ አንዱ ነኝ። ትንሽ ኮራ ብዬ ለመናገር ግን ብዙ ድፍረት የለኝም።

እፎይታ አሳታሚ በነበርክበት ጊዜ በአምስት ቅጾች የታተመው እፍታ መጽሐፍ ሀሳብ እንዴት ሊመጣ ቻለ?

ወጣት በነበርኩ ሰዓት የምጽፋቸውን መጻሕፍትን የሚያሳትምልኝ አልነበረም። በተለይ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ትንሽ ያጉላላኝ ነበረ።

ደራሲና ጋዜጠኛ ብርሃኑ ዘሪሁን ጥሩ ወዳጄ ነበር። ሀዲስ አለማየሁም እንዲሁ ቤታቸው እየሄድኩ እንጨዋወት ነበር። ያኔ ወጣት ነኝ የ19 ዓመት ልጅ። በኢትዮጵያ ውስጥ ለወጣቶች መጽሐፍ ማሳተም ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያጫውቱኝ ነበር።

በተለይ ብርሃኑ ዘሪሁን ‘ተስፋ አትቁረጥ መበርታት አለብህ’ እያለ ይመክረኝ ነበር። እና በዚያን ጊዜ እኔ ድንገት ወደ ስልጣን መጥቼ እድሉን ሳገኝ እኔ እቸገር ስለነበር የወጣቶች ሥራዎች የመታተም እድል እንዲያገኝ በማሰብ ነው እፍታ ቅፅ 1 ብዬ የጀመርኩት። እስከ ቅፅ አምስት ድረስ ባለው በርካታ ወጣቶች ሥራዎቻቸው ታትመውላቸዋል።

እነ ተሾመ ገብረ ሥላሴ፣ እንዳለ ጌታ ከበደን የመሳሰሉ ገና ወጣት ደራሲያን ሥራዎቻቸው እንዲታተሙና እንዲታወቁ ማድረግ በመቻሌ እደሰታለሁ። እኔ ከተውኩት በኋላም እንዳለ ጌታ ከበደ ሊቀጥለው መሞከሩ አስደስቶኛል።

እንዳለ ጌታ ማስቀጠሉ ስትል ደቦ የተሰኘውን መሐፍ ማንሳትህ ነው?

አዎ ደቦን ማንሳቴ ነው።

እርግጥ ነው እፍታ ላይ ራቸው ከታተመላቸው አንዳንድ ደራሲያን መካከል በዛው ቀጥለው በርካታ መጻህፍትን ለአንባቢያን ቀረቡ አሉ። ነገርግን አንዳንዶቹ በዚው ጠፍተዋል። ሀገር ውስጥ ብኖር አሁንም ለበርካታ ደራሲን ራዎች የሕትመት ብርሃን ማግኘት አስተዋጽኦ አደርግ ነበር የሚል ቁጭት ተሰምቶህ ውቃል?

በጣም። ለምሳሌ ተሾመ ገብረ ሥላሴ ደቡብ ክልል ሩቅ ቦታ ሆኖ አንድ ደብዳቤ መጀመሪያ የጻፈው ለእኔ ነው። ያቺን ደብዳቤ ሳያት ይህ ልጅ ደራሲ ነው አልኩኝ። ሰዓዳ መሐመድ ወደ እኔ መጥታ ለመጀመሪያ ጊዜ ያበረታታኋት እኔ ነኝ። የሰዓዳ የብዕር ውበት እስካሁን ድረስ አይረሳኝም። እንዳለ ጌታ ከበደ ወልቂጤ ነበር የሚኖረው። ከወልቂጤ እየተመላለሰ እኔንና ስብሀትን ያገኝ ነበር። በዚያን ጊዜ በጣም የምንወደው ትንሽ ልጅ ነበር።

እነቶማስ አርጋው፤ በሕይወት የለም አሁን፣ አሁን ፊንላንድ የምትኖረው ማርታ- የአባቷ ስም ተረሳኝ፣ እንደዚህ አይነት ትንንሽ ልጆች ነገር ግን ጠንካራ ብዕር ያላቸውን ሳገኝ ሻይ እየጠጣን እናወራ ነበር፤ እንዲፅፉ አበረታታቸው ነበር። እንደዛሬው ዘመን የአንድ ወገን ጠላት ተብዬ ከመፈረጄ በፊት [ሳቅ]።

ከአማርኛ ደራሲያን የማን ተፅዕኖ አለብኝ ትላለህ?

በግድ ጥራ ካልከኝ ስብሀት ገብረ እግዚአብሔር፣ ብርሀኑ ዘሪሁን፣ በዓሉ ግርማን የማነሳ ይመስለኛል።

ከኢትዮጵያ ከወጣህ በኋላ ደቡብ አፍሪካ፣ ከዚያም አሜሪካ፣ አውሮ አሁን ደግሞ ኤርትራ እንደምትኖር ሰምቻለሁ። ቋሚ መኖሪያህ የት ነው?

ቋሚ ያልሆነ ሰው ምን ቋሚ መኖሪያ ያስፈልገዋል ብለህ ነው? እስክትሞት ድረስ ዝም ብለህ መኖር ነው [ሳቅ]። ከ50 ዓመት በኋላ ምን ቋሚ መኖሪያ ያስፈልጋል። አሁን ያለሁበት ስድስት ወር እቆያለሁ [ቃለመጠይቁን ስናደርግ ስቶኮልም ነበር] ከዚህ በኋላ አሜሪካ እሄዳለሁ፤ እንደዚህ ስትል 60 ይገባል፤ በዚያው እድሜዬ አለቀ ማለት ነው። ለእኔ መኖር መጻፍ ብቻ ነው። ስለቋሚ መኖሪያ አስቤ አላውቅም።

ኢትዮጵም ስትመጣ ጠይቆ ለመሄድ ብቻ ነው እንጂ ረዥም ጊዜ ቆይቶ ለመኖር አታስብም ማለት ነው?

እንደሁኔታው ነው። እዚያ ረዥም ጊዜ ልቆይበት የምችልበት ሁኔታ ከተፈጠረ እቆያለሁ። ቢሾፍቱ ላይ አምስት ዓመትም መቆየት ከተቻለ ጥሩ ነው።

ሥራዎችህ በአማርኛ አንባቢያን ዘንድ ነው በስፋት የሚነበቡት። አንተ ደግሞ ርዕሰ ጉዳ አድርገህ የምታነሳው የኦሮሞን ጉዳይ ነው። በአማር እየፃፍክ በኦሮሚያ ውስጥ ያለው ሠፊው የኦሮሞ ወት ራዎቼን አንብቧል ትላለህ?

እንኳን ኦሮሚያ ላይ አሥመራ ላይ አማርኛ በደንብ የሚናገሩ አሉ። እድሜያቸው ከአርባ ዓመት በላይ የሆነ ኤርትራዊያን አማርኛ በደንብ ይችላሉ። ለምን የትምህርት ቤት ቋንቋ ነበር።

ስለዚህ እድሜው ከአርባ ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ በአብዛኛው [አማርኛ] ይችላል። ኤርትራ ውስጥም [አማርኛ] ይችላል። እና አማርኛ ሰፊ አንባቢ ያለው ቋንቋ ነው። ይህ ምንም የሚካድ አይደለም። አማርኛ ከሥራ ውጪ ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ አይቻልም፤ ሊሆንም አይችልም። አማርኛ በአፍሪካ ቀንድ በሰፊው ከሚነገሩ ቋንቋዎች መካከል አንዱ ነው። ውብ ቋንቋ ነው አማርኛ።

በኦሮሞዎች ዘንድ ፖለቲካው ያመጣው ጊዜያዊ ቁጣ አማርኛን መናገር ያለመፈለግ ዝንባሌ አለ። ግን ፍትህ ከሰፈነ በኋላ ሁሉም እንደገና ይመለሳል። ምክንያቱም ጠብ ያለው ከቋንቋው ጋር አይደለም፤ ከጭቆናው ጋር ነው። ስለዚህ አማርኛን ኦሮሞዎች እርግፍ አድርገው ትተውታል ብዬ አስቤ አላውቅም። ጊዜያዊ የፖለቲካው ትኩሳት ያመጣው ስሜት ይመስለኛል።

ራዎችህ መካከል የቡርቃ ዝምታ ወደ ኦሮምኛ መተርጎሙን አውቃለሁ ሌሎች ራዎችህ ወደ ሌላ ቋንቋ የተመለሱ አሉ?

አዎ የኑረነቢን ማህደር ወደ ጣሊያንኛ፣ ወደ እንግሊዘኛና ወደ ትግረ ቋንቋዎች ተመልሷል። የጀሚላ እናት የሚለውም እንዲሁ ተተርጉሟል።

አንዳንዶቹ ገና አልታተሙም። ወደ ኦሮምኛ የተተረጎመው እስካሁን የቡርቃ ዝምታ ብቻ ነው፤ ሌላ የለም። ጫልቱ እንደ ሄለን የምትለዋን ጽሑፍ ብቻ ወደ ኦሮምኛ ተርጉመው በድምፅ ጭምር እንዳለ ግን አውቃለሁ።BBC Amharic

8 COMMENTS

 1. በእርግጥ መንግስት በተባለውም ሆነ ክልል ተጋብዞ ከመጣ ኢትዮጵያ እንዲገባ ከተደረገ የአብይ መንግስት ለይቶለታል ማለት ነው። ቀሪውን እናያለን

 2. This man has kept on his business of fueling conflicts among tribes in Ethiopia. ke’shabia yetelakebetin agenda ahunm alresawum. endiawum afafimo qetlobetal. egziabher yiyilet. yalnebere tarik eyefetere hizbin manakes yeseyitan bahry new. yejun yistew kemalet besteqer min malet yichalal?

 3. (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕ. 6)
  ———-
  16፤ እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤

  17፤ ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥

  18፤ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥

  19፤ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።

 4. “በመንግሥት ደረጃ ተጋብዣለሁ?”
  ማን ሆንክና? አይ ተስፍሽ። አሁንም ደላላነቱን አልተውክም!
  ይልቅ ብዙ ያስቆጣሃቸው ስላሉ እዚያው ሆነህ ተርትህን ብታወራ ይሻልሃል።
  1/ “ለምን እንደጠሉኝ ሳስብ ያልተለመዱ ነገሮችን ስለምፅፍ ነው” አልክ። ምክንያቱ ውሸት ስለምትጽፍ ነው።
  2/ ጠያቂው ጋዜጠኛ ቀሽም ነው፣ ለምሳሌ፣ ሀ/ ተስፋዬ “በአማርኛ የሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ የተለመደው ጫላ ወይንም ጫልቱ የሚል ስም ለቤት ሠራተኛና ለዘበኛ ሲሰጥ ነው፤ ኦሮሞ ስም ያለው ዋና [ዐቢይ] ገፀባህሪ ሆኖ አያውቅም” ላለው የቱ ጋ ብሎ ሊጠይቀው በተገባ ነበር! ለ/ ተስፋዬ ዓለምን ሲዞር የነበረው መጽሐፉን ሽጦ ካካበተው ገቢ ነው? ይኸ ቀላል ጥያቄ ነበር፣ አልተጠየቀም። ሐ/ “ደራሲና ጋዜጠኛ ብርሃኑ ዘሪሁን ጥሩ ወዳጄ ነበር። … ያኔ ወጣት ነኝ የ19 ዓመት ልጅ” ይለናል። ብርሃኑ ዘርይሁንና ሀዲስ አለማየሁ ሁለቱም ሞተዋልና “ወዳጆቼ” ነበሩ ቢለን ማስተባበል እንደማንችል ያውቃታል። ሆኖም ጋዜጠኛው ስላልተዘጋጀ ለማፋጠጥ አልቻለም። ተስፋዬ ይህን ቃለ መጠይቅ ሲሰጥ 50 ዓመቴ ነኝ ብሎናል፣ ብርሃኑ ዘርይሁን የሞተው በ1979ዓ.ም. ነው። ተስፋዬ ብርሃኑ ሲሞት 18 ዓመቱ ነበር፣
  3/ “ወታደር አልነበርኩም” ሲል ጠያቂው ተዘጋጅቶበት ቢሆን ኖሮ ከአዲስ ዘመን ላይ ከነፎቶግራፉ ባፋጠጠው! ለነገሩ ተስፋዬ ዓይኑን በጨው የታጠበ ስለሆነ ዞር ብሎ የማያውቁት አገር ሄዶ እንደገና ሥራውን ይቀጥላል!
  4/ ተስፋዬ ይዋሻል፣ ደራሲ ሲኾን ትግሉ ከእውነት ጋር እንጂ አለዚያ ፕሮፓጋንዲስት ነው!

 5. ተሰፈዬ የለውን፣የሰማውን እነ የምየውቀውን እውነታ ፅፏል።በሽተኛ እነ የአእምሮ ዘገምተኛ ከልሆን በቀር ስለ ኦሮሞ ህዝብ ሰቆቃ የፃፈውን የምክድ ዬለም።ይህንን እውነታ እንኳን ተረደቶ በጉደዩ የማየዝን አእምሮ ምን አይነት እንደሆነ ይገርመኛል።እንዴት የንን ወንዶሞቻችሁን የንቋሻሻ ስርዓት (ህዝብ አላልኩም) ትታችሁ ተስፈዬ ለይ ጣታችሁን ትቀስረላችሁ።ማንስ ነው ሀገሩ እንዳይገባ የምከላክለው።ይልቅስ የለፈው አልፏል እነ አሁን ስለ ይቅርታ እነ ፍቅር ተስፍሽ እንድፅፍ ብትማፃኑ ጥሩ ነው።ይህ ቆሻሻ አስተሳሰብ እነ የዘረኝነት እነ የትብት መንፈስ ከውድቀት ውጭ የምየመጠው ነገር ዬለም።ውውነተውን አምኖ ተስፈየን ከሁን በኋልላ ህዝብምንም የማይገባችሁ ድንጋይ ረሶች ነችሁ።በኦሮሞ ህዝብ ለይ ግፍ ስየደርስ የነበረውን አውግዘን በጋረ ተስማምተትን በፍቅር የጋረ ሀገረችንን እንገንባ።ይህ መሬት ለይ የለ ሐቅ ነው።

 6. ተሰፈዬ የለውን፣የሰማውን እነ የምየውቀውን እውነታ ፅፏል።በሽተኛ እነ የአእምሮ ዘገምተኛ ከልሆን በቀር ስለ ኦሮሞ ህዝብ ሰቆቃ የፃፈውን የምክድ ዬለም።ይህንን እውነታ እንኳን ተረደቶ በጉደዩ የማየዝን አእምሮ ምን አይነት እንደሆነ ይገርመኛል።እንዴት የንን ወንዶሞቻችሁን የንቋሻሻ ስርዓት (ህዝብ አላልኩም) ትታችሁ ተስፈዬ ለይ ጣታችሁን ትቀስረላችሁ።ማንስ ነው ሀገሩ እንዳይገባ የምከላክለው።ይልቅስ የለፈው አልፏል እነ አሁን ስለ ይቅርታ እነ ፍቅር ተስፍሽ እንድፅፍ ብትማፃኑ ጥሩ ነው።ይህ ቆሻሻ አስተሳሰብ እነ የዘረኝነት እነ የትብት መንፈስ ከውድቀት ውጭ የምየመጠው ነገር ዬለም።ውውነተውን አምኖ ተስፈየን ከሁን በኋልላ ህዝብምንም የማይገባችሁ ድንጋይ ረሶች ነችሁ።በኦሮሞ ህዝብ ለይ ግፍ ስየደርስ የነበረውን አውግዘን በጋረ ተስማምተትን በፍቅር የጋረ ሀገረችንን እንገንባ።ይህ መሬት ለይ የለ ሐቅ ነው።

 7. ተሰፈዬ የለውን፣የሰማውን እነ የምየውቀውን እውነታ ፅፏል።በሽተኛ እነ የአእምሮ ዘገምተኛ ከልሆን በቀር ስለ ኦሮሞ ህዝብ ሰቆቃ የፃፈውን የምክድ ዬለም።ይህንን እውነታ እንኳን ተረደቶ በጉደዩ የማየዝን አእምሮ ምን አይነት እንደሆነ ይገርመኛል።እንዴት የንን ወንዶሞቻችሁን የንቋሻሻ ስርዓት (ህዝብ አላልኩም) ትታችሁ ተስፈዬ ለይ ጣታችሁን ትቀስረላችሁ።ማንስ ነው ሀገሩ እንዳይገባ የምከላክለው።ይልቅስ የለፈው አልፏል እነ አሁን ስለ ይቅርታ እነ ፍቅር ተስፍሽ እንድፅፍ መበረታተት ጥሩ ነው።ይህ ቆሻሻ አስተሳሰብ እነ የዘረኝነት እነ የትብዕት መንፈስ ከውድቀት ውጭ የምየመጠው ነገር ዬለም።እውነተውን አምነን በኦሮሞ ህዝብ ለይ ግፍ ስየደርስ የነበረውን ስርዓት አውግዘን በጋረ በፍቅር የጋረ ሀገረችንን እንገንባ።ይህ መሬት ለይ የለ ሐቅ ነው።መደበቅ የማይቻለውን ነገር ለመደበቅ አትሞክሩ፣የማይረባ ክርክር እነ ንትርክ አቁሙ።ስለ ነገ የገረ ሐገራችን እነ እውነተኛ ዲሞክረሲን ከፌደራልዝም ጋር እንደት አንድ ለይ እንደምንተግብር፣ስለ የውሻት አንድነት ሳይሄን ስለ እውነተኛ የህዝቦች እንድሁም የብሔሮች እኩልነት፣ትስስር፣መከባበር እነ መተሳሳብን እነውረ።

 8. ጋዜጠኛው ከላይ እንደተባለው ደካማና ለተስፋዬ ፕሮፓጋንዳ የተመቸ ነበር ማለት ይቻላል። ተስፋዬ ህወአት ውስጥ ቅምጥል ካድሬና ባለስልጣን ያሻውን ቀጣሪና አባራሪ መሆኑን ማሳየት አለመቻል ጋዜጠኛው ወይ በእውቀት ወይ በመረጃ መጎዳቱን ያሳያል።

  ጫላና ጫልቱ ስማቸውን አፍረው ለወጡ ብሎ አማራውን በጨቋኝነት ሊከሰው ይሞክራል ከጫላና ጫልቱ በላይ አሞኘሽ፣ውሽንፍር የመሳሰለው የአማራ ስም ስም ከተሜዎችን ያስቀናል ብዙዎችም ወደ ከተማ ሲገቡ ለውጠውታል። በነዚህ ስሞች አበበ ሆነ ዘበርጋ ጫላም ሆነ ጋቢሶ አብሮ ስቋል ከተከሰስም ስም ቀያሪዎች የሚከስሱት ከተሜውን እንጅ የተለየ ነገድ አይኖርም።

  እንግዲህ እነ ጫላ በስማቸው አፍረው ቀይረውት ከሆነ እራሱ ተስፋዬስ ምነው ተስፋይ ከተባለው ኤርትራዊ ስም ይልቅ ተስፋዬ የሚለውን ስም መረጠ?

  ተስፋዬ ለጠያቂው የሰጠው መልስ ሁሉ ቅጥፈት ሁኖ ሳለ ጋዜጠኛው የተስፋዬን እውነት ለማምከን ብቃት ማጣት ይሆን ሌላ ሳይሞግተው ቀርቷል ለማንኛውም ከቢቢሲ አማርኛ አንድ ብለን ይዘናል አስቡበት የእንግሊዝኛውን የመስፈርት ደረጃ ለእማርኛውም ስለምንጠብቅ ከፍ ባለ ደረጃ አስተናግዱን።
  ይህ ካልሆነ ግን እንደ ኢሳት ጆሮም ሆነ እይታ አንሰጣችሁም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.