ዳያስፖራዎች የአማራ ባንክ አክሲዮንን እንዴት መግዛት ይችላሉ?

ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖሩ ወገኖች (ዳያስፖራዎች) የአማራ ባንክ አክሲዮንን ለመግዛት የሚያስፈልገውን መስፈርት በተደጋጋሚ ይጠይቃሉ። ዳያስፖራው ስለ አማራ ባንክ ያለው መነሳሳት እጅግ ደስ የሚል እንደሆነም እያየን ነው። አማራው በኢኮኖሚውም የተጎዳ እንደመሆኑ የዳያስፖራው ሚና መጠናከር ይኖርበታል!

ሁለት አይነት ዳያስፖራዎች እንዳሉ ይታወቃል። ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው እና ዜግነት የቀየሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሊባሉ ይችላሉ። የባንክ አክሲዮን ለመግዛት የሚያስፈልገው ዶክመንት ለሁለቱ የዳያስፖራ አይነቶች የተለያየ ነው። እንግዲህ እኔ ባጣራሁት መጠን መረጃው ከታች ያለው ነው።

ሀ/ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ላላቸው የሚያስፈልገው መስፈርት፤

1)በሚኖሩበት አገር የኢትዮጵያ ኤምባሲ (ቆንስላ) የተረጋገጠ የውክልና ደብዳቤ

2) የኢትዮጵያ ፖስፖርት ኮፒ

3) አገር ቤት ያለው ተወካይ ሰው የታደሰ መታወቂያ ኮፒ

ለ/ ዜግነት ለቀየሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን

በውጭ ሀገር እየኖሩ ዜግነት ለቀየሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፓርላማው በቅርቡ የባንክ አክሲዮን እንዲገዙ የሚፈቅድ አዋጅ አፅድቋል። ነገር ግን የባንክ አክሲዮን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች ዝርዝር አዋጁን ተከትሎ ብሄራዊ ባንክ በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰን ነው እየተባለ ነው። ይህን መመሪያ እስኪገኝ እየተጠበቀ ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ “ቢጫ ካርድ” ካላችሁ አክሲዮን መግዛት ትችላላችሁ የሚል መረጃ አለ። ስለዚህ የጠራ ነገር የለምና ወደፊት የሚታወቅ ይሆናል። በቢጫ ካርዷ እንሞክረው ካላችሁ ደግሞ ከላይ እንደገለፅኩት ውክልና ልካችሁ መሞከር ይቻላል።

ለአማራ ባንክ መቆም የዳያስፖራው ሚና ከፍ ያለ ነው!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.