አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል

አማራ ሚዲያ ማዕከል
ነሐሴ 15 ቀን 2011 ዓም
አዲስ አበባ ሸዋ

በአዲሱ የኢትዮጵያ የትምህርት ፍኖተ-ካርታ መሠረት ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው አሰራር የትምህርት ምኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ በዛሬው ዕለት በትምህርት ፍኖተ-ካርታ ላይ ረዘም ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በቀጣይ ዓመት ከሚተገበሩ ለውጦች መካከል ጥቂቶቹን ወደ እናንተ ልናደርስ ወደድን::

1ኛ / ለስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና ይሰጣል ተብሏል።

2ኛ / ዘንድሮ ወደ 9ኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች በአስረኛ ክፍል የሚያጠናቅቁ ሳይሆን የአራት ዓመት የትምሀርት ቆይታ ያደርጋሉ።

3ኛ/ የሶስት ዓመት የዩኒቨርሲቲ ቆይታ አይኖርም!

4ኛ/ የሶስት ዓመት ቆይታ ወደ አራት ዓመት ከፍ ማለቱንና በመጀመሪያው ዓመት ሁሉም ተማሪዎች የአገራቸውን ታሪክና ጂኦግራፊን ጨምረው የተግባቦት ትምህርቶችን የሚያውቁበት ነው።

5ኛ/ የኢንጂነሪንግ፣ የህግ፣ የፋርማሲና ሌሎች የ4-5-6 ዓመት ፕሮግራም ያላቸው የትምህርት መስኮች ደግሞ በነበሩበት ይቀጥላሉ።

6ኛ/ አዲሱ የትምህርት መዋቅር በሶስት ክፍሎች ተመድቦ የሚሰራበት ሲሆን እሱም (የ6-2-4) ቅርጽ የሚኖረው ነው፤ ይህም የ6 ዓመት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት፤ የ2ዓመት የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምሀርትና የ4 ዓመት ደግሞ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሆን ተወስኗል።

7ኛ/ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ሲያጠናቅቁ ብሄራዊ ፈተና የሚወስዱ ሲሆን የ6ተኛ ክፍልን ሲያጠናቅቁ ደግሞ ክልላዊ ፈተና ይወስዳሉ።

8ኛ/ ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ድረስ የስነ-ምግባርና የስነ-ዜጋ ትምህርቱ በግብረገብ ትምህርት ተተክቶ በትኩረት ይሰጣል።

9ኛ/ ሁሉም መደበኛ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስኮች ከ12ኛ ክፍል በኋላ ይሰጣሉ።

10ኛ/ የመምህራን ምደባ፦ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ ባላቸው መምህራን፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሁለተኛ ዲግሪ ባላቸው መምህራንና ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ደግሞ የሁለተኛና ከዚያ በላይ ዲግሪ ባላቸው ትምህርት ይሰጣል፤ የቴክኒክና ሙያ ደረጃ አንድና ደረጃ ሁለት የሙያ ስልጠና የመጀመሪያ ደረጃ ዲግሪ ባላቸው የደረጃ አራትና አምስት ደግሞ የማስተረስ ዲግሪና ከዚያ በላይ ባላቸው ይሰጣል።

1 COMMENT

  1. የዩኒቨርሲቲ ሰቃይ ተመራቂዎች የማስተማር ጥልቀትን እንዲረዱ 2ኛ ደረጃ አስተምረው ማለፍ አለባቸው።በስመ ሰቃይ ተማሪ ዩኒቨርሲቲ ማስቀረት ልምዳዊ ስለሆነ መቅረት አለበት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.