«ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች እየራቅሁ ነው» ያለን የአማራ ጉዳይ የተነሳ ሲመስለው ግን ርቆ መራቅ የማይሆንለት ጃዋር መሐመድ! – አቻምየለህ ታምሩ

አንድ ወዳጄ ከወራት በፊት በውስጥ መስመር በኩል «ጃዋር መሐመድ ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች መራቅ እፈልጋለሁ ያለውን እንዴት ታየዋለህ?» የሚል ጥያቄ አቅርቦልኝ ነበር። እኔም በመልሴ «ሐጂ ጀዋር የኦነግ ልጅ ነኝ ብሏል፤ የኦነግ ልጅ እንደመሆኑ መጠን ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛ መራቅ እፈልጋለሁ ቢሉም ስለ ኦሮሞ ሳይሆን የአማራ ጉዳይ የተነሳ ሲመስለው ግን «ለመተንተን» ተመልሶ ይመጣል» ብዬው ነበር።

እንዳልሁትም ወለጋ ግፉዓን በኦነግ ሸኔ ሲዘረፉ፣ሲረሸፉና አስከሬናቸው ሲቃጠል፣ ከሀያ በላይ ባንክ በኦነግ ሲዘረፍ፣ቡራዩ የዘር ፍጅት ሲካሄድ፣ ሻሸመኔ ሰው ዘቅዝቀው ሰቅለው ግዳይ ሲጥሉለት፣ከአርሲ ወደ ወለጋ ይጓዝ የነበረው ተሿሚ በኦነግ ዐይኑ እንደ ሙጀሌ ተነቅሎ ሲወጣ፣ሐረር ባንክ ሲዘረፍና ንጹሐን ሲገደሉ፣ወዘተ አንድም ሳይተነፍስ ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች የራቀ የመሰለው ጃዋር መሐመድ ከአማራ ጋር የሚያገናኝ አንዳች ነገር የተከሰተ ሲመስለው ግን «በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ» እየተባለ «ትንተናና አስተያየት» ሊሰጥ በቴሌቭዥኑ መስኮት እንዲሁም በፌስቡኩ ዱቅ ይላል።

ከአማራ ጋር ይያያዛሉ በተባሉቱ የአጣዬውን የኦነግ ጭፍጨፋ፣ የከሚሴውን የኦነግ ወረራ፣ የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ፣ የሰኔ 15ቱን የባሕር ዳር ግድያ፣ የአማራ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዳመጡ ተደርጎ በማኅበራዊ ሜዲያ ውጤታቸው የመታየቱን ጉዳይ ተከትሎ ከሁሉ አስቀድሞ በፌስቡኩ አስተያየት የሚሰጠውና በቴሌቭዥኑ ቀርቦ የሚተነትነው ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች እየራቅሁ ነው ያለውን ጃዋር መሐመድ ነው።

ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች እየራቅሁ ነው ያለውን ጃዋር መሐመድ ከአማራ ጋር የሚገናኝ ጉዳይ የተነሳ ሲመስለው ከራቀበት የማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች ከሁሉም በፊት ቀርቦ በመገኘት አስተያየትና ትንተና የሚሰጠው የአባቱ ቤት ማለትም የኦነግ ቤት ፖለቲካ
የሆነው አማራ ይጠላዋል ብለው የሚያስቡትን መጥላት፤ይወደዋል ብለው የሚያስቡትን ደግሞ መውደድ ፖለቲካው ስለሆነ ነው። ስለኦነጋውያን ፖለቲካ የበለጠ ለመረዳት «የኦነጋውያን ፖለቲካ የጥንብ አንሳ ፖለቲካ» በሚል የጻፍሁትን ያነቧል።

በእስካሁኑ ትዝብቴ ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች እየራቅሁ ነው ያለውን ጃዋር በኦሮምኛም ይሁን በአማርኛ በፌስቡክና በቴሌቭዥኑ አስተያየትና ትንተና ያለፈበትን ወቅት አላስታውስም።

እነሆ ዛሬ ከማኅበራዊ ሜዲያና ከብዙሐን መገናኛዎች የራቀው ጃዋር «ሕፃናትን ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ አማርኛ ቋንቋን ይማራሉ ማለት ጦርነት ማወጅ ነው» የሚል ነገር ይዞ መጥቷል። ጃዋር ይህ የአማርኛ ጥላቻ ጅራፉን ይዞ ብቅ ያለው ትምህርት ሚኒስቴር ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ አማርኛና እንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲሰጥ ወስኗል ያሉትን በመቃወም ነው። ልብ በሉ አዲሱ ፖሊሲ ሕጻናት ከአንደኛ ክፍል ጀምረው የባዕድ ቋንቋ የሆነውን እንግሊዝኛ ቋንቋን እንዲማሩ ይደነግጋል። ለነጃዋር ጦርነት የሚሆነው ኢትዮጵያዊውን ቋንቋ አማርኛን ከአንደኛ ክፍል ጀምረው የኢትዮጵያ ሕጻናት መማራቸው እንጂ የባዕዱን ቋንቋ እንግሊዝኛን ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ መማራቸው አይደለም።

ጃዋር ልጁን በሚያስተምርበት አገር ሕጻናት ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከ ሶስት ቋንቋ ድረስ ይማራሉ። ምንም እንኳ አማርኛ የአማራ ቋንቋ ብቻ ባይሆንም ፖለቲካው ግን የአማራ ጥላቻ ስለሆነ ልጁን በሚያስተምርበት አገር ሕጻናት የሚያገኙትን እድል የኢትዮጵያ የድኃ ገበሬ ልጆች እንዳይጠቀሙበት ሳይመረምሩ የሚከተሉትን የጥላቻ ፖለቲካ ሰለባዎች ተቃውመው ይቀሰቅሳቸዋል። ምርምር ከማድረግ ባልተናነሰ ከአፍ መፍቻ በተጨማሪ ሌላ ቋንቋ መማር ተጨማሪ የእውቀር በርን ይከፍታል። በአገዛዙ በሪፑብሊካን ጋርድ የሚጠበቁት የድንቁርና መምሮቹ እነ ጃዋር ግን የእውቀት በር የሚከፍተውን ተጨማሪ ቋንቋ መማርን ጦርነት እንደማወጅ ይቆጥሩታል። አገዛዙ

ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ከአንደኛ ክፍል ጀምረው አፋቸውን ከፈቱበት ቋንቋ በተጨማሪ ምርጫቸው የሆኑ ተጨማሪ የአገራችንን ቋንቋዎች ቢማሩ የእውቀር በር ይከተትላቸዋል እንጂ ጃዋር እንዳለው ጦር ሜዳ እንደመግባት አይነት ጉዳት አይደለም። የአገራችን ታላላቅ ሰዎች ሁሉ ከአንድ በላይ ቋንቋ የሚናገሩ ናቸው። ታላላቆቹ እነ እነ ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም፣ ከንቲባ ገብሩ ደስታ፣ ዶክተር ሎሬንሶ ታዕዛዝ፣ ፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተ ወልድ፣ ብላታ ደሬሳ አመንቴ፣ አናሲሞስ ነሲብ፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ አቶ ሐዲስ አለማየሁ፣ ዶክተር ገብረ ሕይዎት ባይከዳኝ፣ አቶ አሰፋ ጫቦ፣ በአሉ ግርማ፣ ወዘተ… ጳውሎስ ኞኞ፣ ኢላላ ኢብሳ፣ ወዘተ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ከሆኑት ከአማርኛ፣ ከኦሮምኛ፣ ከትግርኛ፣ ወዘተ. . . ወዘተ በተጨማሪ ከውጭ አገር ቋንቋዎችም እንግሊዝኛን፣ ፈረንሳይኛን፣ አረብኛን፣ ሞስኮብኛን፣ ጀርመንኛንን፣ ወዘተ በልጅነታቸው የተማሩ ናቸው። ለእነዚህ የኢትዮጵያ ታላላቅ ሰዎች ሰፊ የእውቀት በር የተከፈተላቸውና ታላቅ ሰው ለመሆን የቻሉት ብልሆቹና አሳቢዎቹ ወላጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ከአንደኛ ክፍል፣ ከልጅነታቸው ጀምሮ ከአንድ በላይ ቋንቋ እንዲማሩ ስላደረጓቸው ነው። የድንቁርና መምሕሮቹ ግን የኢትዮጵያ የድኃ ገበሬ ልጆች የእውቀት በር እንዳይከፈትላቸው ከአንድ በላይ የኢትዮጵያ ቋንቋ መማርን ጦርነት እንደማወጅ አድርገው ይዘምቱበታል።

አንድ ሰው አማርኛ የሚማረው ለአማራ ሲልም ይመስላቸዋል። እንዲህ የሚያስቡ ሰዎች እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ድረስ እንግሊዝኛ ሲማሩ ግን ለእንግሊዞች ነው ብለው አያስቡም። እያንዳንዱ አማርኛም ሆነ ሌላ ቋንቋ የሚማረው የእውቀር በር እንዲከፈትለት ለራሱ ሲል እንጂ ለማንም አይደለም። ትግርኛ በማወቄ ተጨማሪ የእውቀት በር ተከፍቶልኛል። እኔ ትግርኛ ያወቅሁት ለራሴ እንጂ ለትግሬ ብዬ አይደለም። እንዴም ትግርኛ በማወቄ የተጎዳው ትግርኛ ተናጋሪው ሕወሓት ነው። ትግርኛ በማወቄ ተደብቀው በትግርኛ የሚጽፉትን ብዙ ሚስጥራቸው እንዳውቅና እየተረጎምሁ በፌስቡክ በመልቀቅ እንዲጋለጡ አድርጌያለሁ። እነዚህ አማራን የጎዱ እየመሰላቸው ሕጻናት ተጨማሪ ቋንቋ እንዳይማሩ የሚያደርጉ ጥንብ አንሳዎች ግን የሕጻናቱን የእውቀት በር ከመዝጋታቸው በስተቀር በአማራ ላይ የሚያስከትሉት አንዳች ጉዳት እንደሌለ ያወቁ አይመስሉም። ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ!

6 COMMENTS

 1. Achamyele,

  Cheap propoganda  is not helpful  for you and your people and your nazist organization, the NAMA. No power on earth will stop the Oromo people from fulfilling its aspirations as a freedom loving nation to regain its human dignity and rights. It is up to you to respect this great nation for the sake of your own benefits. For durable solutions use your mind as a rational thinker, but don’t use your belly like a big.   

  Don’t accuse Jawar Mohammed. He does always the right things. We, all the daughters and sons of Oromo, are Jawar Mohammed! You cannot intermediate any Oromo. Jawar is one of our heroes. We are proud of him. You can bring whatever you have in your stores. The offsprings of the ex-Neftegnas keep yourself away from Oromia. We will never accept the second class citizenship in our fatherland, Oromia. We will show who we are to the mindless ultra nationalists like Eskinder Nega, Dawit Woldegiogies, yourself and your associates. Keep on barking like  a dog! We are not demanding Bahir Dar, Gonder or Mekele. We are demanding our human rights only on our soils, Oromia.

  Finaly, I would like to remind you that you are sick and possessed by the spirit of hatred. Thus, it is better if you try to visit a psychiatrist.

 2. If there will be no mutual understanding, there will be no more Amharic language teaching in Oromia schools.

  We don’t want to see and hear any more Amharic as the first class language and afaan Oromoo as the second class language. The assimilation and discriminatory policies of the ex-nefteny will not work any more in Oromia.

  The racist individuals like this guy can keep their barking like a mad dog.

 3. The new policy is just “bemar yetelewese merz”. NO to the new policy. It looks like it is drafted by ABIN. Let the States determine their own policy. NO to CENTRALISM.

 4. “ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ከአንደኛ ክፍል ጀምረው አፋቸውን ከፈቱበት ቋንቋ በተጨማሪ ምርጫቸው የሆኑ ተጨማሪ የአገራችንን ቋንቋዎች ቢማሩ የእውቀር በር ይከተትላቸዋል”
  አቻምየለህ፣ አፍ በፈቱበት ስለ መማር ጠንቅቀህ አታውቅም። ያንተ ክርክር የአክራሪው የጃዋር ግልባጭ ነው። አክራሪ ነህ። እንዳልከው፣ ከአንድ ቋንቋ በላይ መናገር በእኛ ኣይነቶቹ አገሮች ድንቅ አይደለም። ችግሩ በእልክና በጽንፈኛ ፖለቲካ ሲደረግ ነው። እንደ ጀዋር አንተም ጽንፈኛ ፖለቲካ ተያይዘሃል። “በአገራችን ታሪክ እንዲህ ሲደረግ ነበር፣ አሁንም እንዲህ መሆን አለበት” አባባልህን ተደጋግሞ አይቻለሁ። ይኸ ዓይነት አስተሳሰብ አይሰራም፣ ጊዜ አልፎበታል። አማርኛ “ኦሮምያ” በተሰኘው ክልል አፍ ከፈቱበት ቋንቋ በተጨማሪ ቢሰጥ ብለሃል። መልካም። ኦሮምኛ “አማራ” በተሰኘው ክልል ግን እንዲሰጥ ጨርሶ አላሰብክም። አይገርምም? እዚህ በዚህ ራስህን ስትጻረር? ምክንያቱ ቅን ስላልሆንክ እና ስለ ትምህርት (ፔዳጎጂ) የማታውቀውን መዘባረቅ ስለምታበዛ ነው፤

 5. አለም እና ገመዳ እንደው ታስቃላችሁ እናንተ ባትኖሩ ሰው በምን ይስሐቅ ነበር? አቻምየለህ ባፍ መፍጫ ቋንቋህ አትናገር ያለበትን ኮፒ ፔስት አድርገህ አሳየን።
  አሁንስ ጨርቅ ጥላችሁ ሳታብዱ አትቀሩም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.