ዛሬ ለሱሉልታ ነዋሪዎች መብት መቆም ያልመረጠ ወይም ያልደፈረ አዲስ አበቤ፣ በጣም በቅርቡ የርሱም እጣ ተመሳሳይ እንደሚሆን ሊረዳው ይገባል

ዛሬ አንድ ዜጋ ኦሮሞ ባለመሆኑ ከሱሉልታ ከተባረረ፣ ነገ ከአዲስ አበባ እንደማይባረር ምንም መተማመኛ የለም። አዲስ የመከላከያ መስመርህን ሱሉልታ ለይ ብታደርግ ትጠቀማለህ።

በነሃሴ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደቡብ ኮሪያን ሲጎበኙ ሱሉልታ ፈረሰ፣ በመስከረም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንውዪርክ ለተባበሩት መንግስታት ስብሰባ ሲሄዱ ደግሞ አዲስ አበባ ይፈርሳል። ተቃዋሚ ፓርቲዎችና “ነፃ” ሚዲያዎች ደግሞ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃገር ውስጥ ቢኖሩ ኖሮ እኮ ይህ አይደረግም ነበር” ብለው ይሸነግሉሃል። እንዲህ እንዲህ እያልን ግንቦት 2012 እንደርስና፣ የህዝብ ቆጠራ ለማድረግ በማይቻልበት ሃገር ዓለምን ያስደነቀ ፍፁም ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማድረጋችን ይበስረል። ወያኔ 37፣ ኦነግ 37፣ አብን 37 መቀመጫዎች ይለቀቁለትና፣ አዲሱ የኢህአዴግ ፓርቲ ማሸነፉ ይታወጃል። የድጋፍ መግለጫዎቹ ለአሸናፊው ፓርቲ ሊቀመንበርና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከመላው የምእራብ አለም ሃገራት በአፋጣኝ ይላካል። በአለ ሲመቱም ከጥቅምት 1923 የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንግስና በላቀ ደረጃ ይተወናል። የውጪ በተለይም የምእራብ መንግስታትም ታላላቅ ባለስልጣኖቻቸውን ወደ በአለ ሲመቱ ይልካሉ። ስእሉን ሲያስቡት እጅግ የደመቀና አጓጊ ቢመስልም፣ በዚህ ተፅፎ ባለቀ ድራማ ላይ የሚደክሙት ወዳጆቼ ያሳዝኑኛል። ከዚያ ኢህአዴግ ቨርሽን 2.0 ለሌላ 25 ዓመታት ይቀጥላል። ልዩነቱ ገራፊዎቹ ትግሬዎች መሆናቸው ቀርቶ ኦሮሙኛ ተናጋሪዎች ይሆናሉ። ይህ መፃኢ እድሉ እንዲሆን የማይፈልግ አዲስ አበቤ ዛሬ ከሱሉልታ ከሚፈናቀሉት ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ጎን ሊቆም ይገባል!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.