የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደ ዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ አይነት ጠላት በታሪኳ አጋጥሟት አያውቅም!

ዮዲት ጉዲት በተነሳች ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ገዳሞቿን አውድማለች፤ ካሕናቷን አርዳለት፤መጻሕፍቶቿን አውድማለች፤ የቤተ ክርስቲያኗን አንድነት ግን ለማፍረስ አልሞከረችም።

ግራኝ አሕመድም በተስፋፋ ጊዜ የኢትዮጵያን ገዳማትንና ታላቁን አክሱም ጽዮንን ጨምሮ በርካታ ጥንታዊና ታላላቅ ደብሮችን አቃጥሏል፤መተኪያ የማይገኝላቸውን ካሕናትና ጳጷሳት አርዷል። የቤተ ክርስቲያኒቷን ቅርሶችና ሊተኩ የማይችሉ መጽሐፍቶቿን ዘርፏል፣አውድሟል። ሆኖም ግን አንድነቷን ለማፍረስ አልሞከረም።

ፋሽስት ጥሊያን ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ በአንድ ቀን ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ የደብረ ሊባኖች ገዳም መነኮሳትንና እድሜያቸው ከ18 ዓመታት በላይ የሆኑ ዲያቆናት፣ ካሕናትንና ተማሪዎች ፈጅቷል፤ ሌሎች ገዳማትንና አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናትን አውድሟል፤ ጥንታዊ መጽሐፍቶቿን ዘርፏል፣ የተረፉትን አቃጥሏል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ይህን ያደረገው ጥሊያን የቤተ ክርስቲያኒቷን አንድነት ግን ለማፍረስ አልሞከረም።

እንዴውም በአምስቱ ዓመታት የፋሽስት ጥሊያን ወረራ ወቅት ከወረራው በፊት ሁለት አገራት የነበሩት የኢትዮጵያና የኢጣሊያን ኤርትራ ውስጥ የነበሩ ቤተ ክርስቲያናት ሳይከፋፈሉ በአንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስር ሆነው እንዲቀጥሉ ተደርጓል። በአምስቱ ዓመት የፋሽስት ጥሊያን የመከራ ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ወርዶ የፋሽስት ባንዲራ ሲሰቀል የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አምስት ዓመታት ሙሉ ሳይቋረጥ ይውለበለብ የነበረው ኤርትራ ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያኖች ቅጥር ግቢ ውስጥ ብቻ ነበር።

ከፋሽስጥ ጥሊያን በኋላ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምና መለስ ዜናዊ የሚባሉ ሁለት ገዳዮችን አውርዶባት ነበር። ሁለቱ አገዛዞች የቤተ ክርስቲያን ጳጳሳትና ቄሳውስቷ በግፍ ገድለውባታል፤ በሁለቱ አገዛዞች ታፍነው ተወስደው ዛሬም ድረስ የት እንደገቡ የማይታወቁ ታላላቅ ሊቃውንቶቿ አልተገኙም። በተለይ በዘመነ መለስ ዜናዊ ሕወሓት ነባሩን የሲኖዶስ አባላት አባሮ ለሕወሓት የገበሩ የሲኖዶስ አባላትን በማደራጀት አዲስ ሲኖዶስ መስርቶ አዲሱን ሲኖዶስ የሕወሓት የሃይማኖት ክንፍ በማድረግ ቤተ ክርስቲያን ባለፉት ሀያ ሰባት ዓመታት የአገዛዙ ካድሬዎች መፈንጫ ቢያደርጋትም ቤት ክሕነት ትጠራ የነበረው የኢትዮጵያ ቤተ ክሕነት ተብላ ነበር።

በዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ ዘመን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ያጋጠመው ችግር ግን ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተች ጀምሮ አጋጥሟት የማያውቅ መከራ ነው። እርግጥ ነው በዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ዘመንም ልክ እንደ ግራኝ፣ ዮዲትና ጥሊያን ዘመን ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥላለች፣ካሕናቱ ታርደውባታል፤መነኮሳቱ ተደፍረዋል፤ ሀብቷ ተዘርፏል።

በዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ዘመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያጋጠማት በታሪኳ አጋጥሟት የማያውቀው መከራ በታሪኳ ያጋጠሟት ጠላቷ ሁሉ ያልሞከሩት የቤተክርስቲያኒቷን አንድነት ለማፍረስ የተደቀነባት አደጋ ነው። ይህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ሁሉ በቤተ ክርስቲያኒቷ ታሪክ ቃጥተውባት የማያውቁት አንድነቷን የማፍረስ አደጋ የተደቀነው ደግሞ ዐቢይ አሕመድ በሊቀመንበርነት የሚመራው ድርጅት የፓርላማ አባል በነበረ ፖለቲከኛና ኦሕዴድ ባሰማራው ቡድን ነው።

በሌላ አነጋገር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስስቲያን ታሪካዊ ጠላቶች ሁሉ ያልሞከሩትን የቤተ ክርስስቲያኗን አንድነት የማፍረሱ ስራ እየተሰራ ያለው ዐቢይ አሕመድ በሚመራው ኦሕዴድ በሚባለው ድርጅት ነው። ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደ ዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ አይነት ጠላት በታሪኳ አጋጥሟት አያውቅም ለማለት የደፈርሁት።

የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት ለማፍረስ መነሳቱን የሚያሳየው ቤተ ክርስቲያኒቱ በ«ቀሲስ» በላይ የሚመራውን የኦሕዴድ ቤተ ክርስቲያን አፍራሽ ቡድን እንዲያስቆም የጠየቀችውን አገራዊ ጥሪ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲኗን ለማፍረስ የተነሳው የኦሕዴድ ቡድን መግለጫ አገዛዙ በመንግሥት ሜዲያዎች አሰራጭቶ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ ግን በዚያው ሜዲያ እንዳይተላለፍ መከልከሉ ነው።

አቻምየለህ ታምሩ

7 COMMENTS

 1. ቅዋሜም ልክ አለው:: ትንሽ ቆይተህ ወያኔ ይሻለን ነበር እንደምትል እልጠራጠርም:: ይህ ሁሉ ሀገራችን የገባችበት መከራ ምንጩ ፀረ ኢትዮጵያ ፀረ አማራ የሆነው የማፍያ ቡድን ህውሀት የዘረጋው መዋቅር ነው:: ኦሮሞሚያን የፈጠረ የኢትዮጵያን ህዝብ የለያየ የኢትዮጵያ ጠላት ህውሀት ነው::

 2. አይ ደመቀ የቁቤ ሰው ነህ መሰል እሱም እኮ ካንተ የተለየ አላለም አረዳድህ ቁቤያዊ ሁኖ ነው እንጅ። እነዚህ ትግሬዎች ባቢሎን አድርገውናል መጨረሻችንን እንጃ።

 3. ይሄ ፕጅ የኢትዮጵየ ጠላቶች ፔጅ ነው።የሀገርቷን ትላልቆቹን ብሔር ለማጣላት ሌት ተቀን የምሰረ የዘረኞች ፔጅ ነው።ሁሌ በዘር በተለይ በኦሮሞ ጥላቻ የነውዙ እንደአቻሜለህ ታምሩ ፣ግርማ ከሳን እነ የመሳሰሉትን ሰዎች የጥላቻ ፅሑፍ ነው የምየየቀርበው።የክርስቶስን ቃል ለህዝቡ ቋንቋ ማቅረብን የተቀደሰን አለማ ለመካድ ይሄን ሁሉ ጥላቻ መፃፍ ምን አስፈለገ።እርቅ እነ የነበሩትን ቆሻሻ እነ የጥላቻ ስረዎችን አውግዘን ወደ አንድነት የምየስከደውን መንገድ ትቶ መሬት ለይ የለውን እውነት እየካዱ በውሸት ወሬ ህዝብን እነ ህዝብን መቃቃር ምን ይበላል።ይበልኝ የጥላቻ በለቤቶች።ክርስትና ፍቅር ነው፣ክርስቶስ ሐዋርየቶቹን የሰማረው ህዱ እነ በቋንቋቸው፣በበህላቸው የእግዝአብሔርን ቃል/ወንጌልን አስተምሩ ብሎ ነው።ስለዝህ ምንድን ነው የምየንጨጫችሁ።

 4. ውድ ዳንኤል፣
  ጸሐፊው አቻምየለህ ነው። “የታሪክ እና የምጣኔ ሃብት ተመራማሪ ነኝ” ይላል።
  እውነቱ ግን ሥራ ፈት ነው። አንስቶ መለደብ ነው ሥራው።
  “አፓርታይድ” እና “ፋሽስት” ን 10 ጊዜ ደጋግሞታል። “የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ” ሲለን
  ስለ አፓርታይድ ምንም እንደማያውቅ በራሱ እየመሰከረ ነው።
  ጊዜ ካገኘህ የአቻምየለህን፣ የሰርፀን፣ የግርማ ካሳን ጽሑፎች ሳተናው ላይ ተመልከት።
  ጥላቻ ብቻ ነው የሚጽፉት። ጥላቻቸው ደግሞ ኦሮሞ ላይ ብቻ ያነጣጠረ ነው። ልክ እንደ እስክንድር ነጋ።
  ያደገባቸው ዐመል ነው። ለማስጣል ጊዜ ይፈጃል። ደግነቱ የትም አይደርሱም!
  እኔም እንዳንተው ሳተናው ለምን ጥላቻ ያስተናግዳል ብዬ ነበር። ኋላ ሳስበው መቃቃር ካለበት
  ብዙዎች ስለሚመላለሱ ለገቢ ይሆናል አልኩ። በነገራችን ላይ፣ እስክንድርና ጃዋር ኣይነቶች አያስፈልጉንም።
  እነዚህ ሁለቱ ወደ ፊት በተለይ የቡራዩን እልቂት በተመለከተ ፍርድ ፊት ከመቅረብ አያመልጡም።

 5. አብይ ተኮትኩቶ ያደገው፣ በጸረ~አማራና ጸረ~ኢትዮጵያ የወያኔና የኦነግ መንግስት ስር ነው። ይህ ድርጊቱ ሁሉ ከስራው እጅግ የራቀ፣ ቃሉን የማያከብር፣ መሃይምን ፣ አስመሳይ፣ አማራ~ጠል ፍጡር ነው። ይህ ሰው የወደደውን ያከበረውን ህዝብ የከዳ፣ ህሊና የሌለው እንደሆን ራሱ አይክድም።
  አቶ አቻምየለው፣ ለሚል ለሚጽፈው መረጃ ያለው፣ ምጡቅ ምሁር ነው። ከላይ ያነሳቸው ጉዳዮች በሙሉ አሌ የማይባሉ ናቸው።
  አብይ አማሮችን ባህርዳር አስፈጅቶ፣ እርስ~በርስ ተጋደሉ በማለት፣ በሰበብ አስባብ አያሌ አማሮችን ያሰረ፣ ሰው ነው። ፍጡር ከባህርዩ በላይ ሊውል ስለማይችል፣ ከአቢይም ሆነ ከመሰሎቹ፣ ምንም አግባብና ህጋዊ ድርጊት አይጠበቅም። አበው ኡለት ድንቅ አባባል አላቸው። ‘ድመት መንኩሳ፣ ስራዋን አትረሳ’። እነ አቢይ የተንኮለኛ ድመት ተምሳሌት ነው።
  እነርሱን ማባበልም ሆነ ልብ ግዙ ማለት ዋጋ የለውም። ለጥፋት በር የከፈትነው፣ እንርሱን ከሰው የቆጠርነው ሌሎች ዜጎች ነን። “ሊገደል የመጣ፣ ምንትስ ፣ አባባ ቢሉት አይመለስ” ይባላል። ኦነግ፣ የውያኔው አገልጋይ፣ ለጥፋት የመጣ የአራዊት ቡድን ነው። እንደአራዊት ፣ መታየት አላበት ። ያኔ አይቀሬው ፍልምያ፣ ይገላግለናል።

 6. ህዝበክርስቲያኑና የለውጡ ሃይል የወያኔን ሴራ የዘነጋ ይመስላል:: የኦሮሞ ቤተክህነት አጀንዳ መጀምሪያ ያነሳው ከአልቃው ጋር የትቀሰፈው ታጋይ ጳውሎስ ነበር:: ከዚያ የጃዋር ጀሌ ቀሲስ በላይ በቅርቡ ሲያፋፍመው መጀምሪያ የደገፈው የወያኔ ዲጂታል የሳይበር መሪ አሉላ ሰለሞን ሲሆን ጽንፈኞቹ ተቃውሞስለፍ በማለት እልቂት ሊያስጀምሩ በመትጋት ላይ ናቸው:: ዶ/ር ኣብይ ሰሞኑን ከጽንፈኞቹ ጋር ትንቅንቅ ላይ ስለሆነ ተቃውሞ አድማ በመጥራት ለከሃዲዎቹ ጩቤ አናቀብል ተረባርበን በአንድነት የኦርቶዶክስ ትዋህዶንም የኢትዮጲያንም አንድነት እናስጠብቅ;: በኦህዲድ ውስጥ የተስገሰጉ ጽንፈኞች ለቀሲስ በላይ መድረክ እየሰጡ በኦሮሚያ ተቃውሞው ሰልፍ ኣይደረግም የሚሉት ህዝቡን ለማስቆጣትና በሚፈጠረው እልቂት ለውጡን ለመቀልበስ መሆኑ ይሰትዋል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.