የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረው ወርቅነህ ገበየሁ የተባበሩት መንግስታት ሥራውን እንዳልጀመረ ታወቀ

የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ምንጮች ሹመቱ ሳይሰረዝ እንዳልቀረም ለኢሳት ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ዋና ጸሃፊ  ሚስተር አንቶንዮ ጉተሬዝ  ዶ/ር ወርቅነህን  ኬኒያ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጀትት ጽ/ቤት ዳይሬክተር  ጄነራል አድርገው የሾሟቸው መጋቢት 8 /2019 ቢሆንም፣ ዶ/ር ወርቅነህ ባለፈው 6 ወር  በሥራ ገበታቸው ላይ አልተገኙም።
ድርጅቱን በግዚያዊነት የሚመሩት ሚስተር ሲድሃርት ቻተርጄ  እንዲሁም ሚስ አናሊዛ ኮንቴ እና ሚስ ማሙናህ ሸሪፍ መሆናቸውንም ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። ናይሮቢ የሚገኙ የድርጅቱ ሰራተኞች የዶ/ር ወርቅነህ ሹመት መሰረዙን በመናገር ላይ ሲሆኑ፣ ምክንያቱ ግን አልተገለጸም።
ኢሳት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ የሆኑትን ሚስተር ስቴፈን ዱጃሪክን እንዲሁም ራሳቸውን  ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።
ምንጭ:- ኢሳት

2 COMMENTS

  1. በየቦታው ያሉት በሁለት እጅ የማይነሱ የኢትዮጵያ ምሁራን ባሉበት አገር ወርቅነህ ገበየሁ፣ሰየ አብረሀ ምናልባትም ሐይለ ማርያም ደሳለኝን ቀጥሎም ታምራት ላይኔን የመሰሉ ነብስ በላ የሰብአዊነት ጠላቶች በተመድ ተቋማት ውስጥ ገብተው ሲሰሩ የኢትዮጵያ ምሁራን በረቀቁበት ቋንቋ ባላቸው የግንኙነት መስመር ተጠቅመው አጋልጠው ክዚህ ክብር ያለው ተቋም እንዲባረሩ ያለማድረጋቸው ምሁር አልባ አገር መሆናችንን ያሳያል።

  2. የአለም መንግስት የተባለው ድርጅት ፣ ባጠቃላይ የምዕራባውያንን ፍላጎት እንዲያሟላ የተቁዋቋመ ተቋም ነው። የነኚህን የተዘረዘሩትን እክይ ፍጡራን ማንነት ። ድርጅቱ ያውቃል። እንደሰዬ ያለን ነፍሰ ገዳይ ቢቀጥር ሊደንቅ አይገባም።

    ያንድ ወራዳ፣ መሃይምን፣ በዚህ ድርጅት ለከፈተኛ ስፍራ መሰየም ሊገርም ይገባል። ቴድሮስ አድሃኖም የተባለው ወያኔ በብዙ ወንጀል እጁ ያለ፣ የአማራን ህዝብ በተለይ፣ በወባ ያስፈጀ፣ የአማራ ሴቶችን፣ ያለፈቃዳቸው መሃን የሚያደርግ መድሃኒት በገፍ እንዲወስዱ ያደረገ፣ ከ $ 50 ሚሊየን ዶልር በላይ፣ ግሎባል ፈንድ ከሚባል አለም አቀፍ ድርጅት የተገኘን ገንዘብ የመዘበረ መሆኑ የሚወሳን ሰው፣ ከህክምና የማይተዋወቅ፣ ትምርቱ ትንኝ የሆነ፣ በድርጅቱ የ70 አመት ታሪክ፣ የረጅም ግዜ ልምድ ያለው ሃኪም ብቻ ይመራው የነበረውን የአለም ጤና ድርጅት በመሪነት ተሹሟል።
    የዚህ ሰው እጩነት ገና እንደተገለጸ፣ ስለዚህ ሰው ምንነትና ማንንነት ፣ በትንሹ ከ 10 ያላነሱ ጽሁፎች ፣ በድፍን አለም ተሰራጭተው ነበር። ግን አንዳች ለውጥ አላመጣም። ብቃት የላቸውማ ሰዎች ፣ዝር አይሉም ምክንያቱም፣ ድርጅቱ ፣ የታጨው ሰው፣ ከአገሩ መንግስት፣ ድጋፍ ሊኖረው ይገባል የሚል ፣ ማነቆ ስላለ።
    ዋናው ነገር አገራችን፣ በነኚህ ኢትዮጵያዊነትን ሊያጠፉ ከየስርቻው የወጡ አረመኔዎች መዳፍ ስር ፣ አገራችን እንድትወድቅ የፈቀድን ፣ ድኩማን ነን ልንወቀስ የሚገባን። እነርሱማ ፣ ያው ጠላት ናቸውና ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.