በአዲስ አበባ በሚገኙ 125 ትምህርት ቤቶች በኦሮሚያ ስርአተ ትምህርት በኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት ሊሰጥ ነው – የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ 

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 125 ትምህርት ቤቶች በኦሮሚያ ስርአተ ትምህርት በኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት ለመስጠት ምዝገባ እያካሄደ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮን ጠቅሶ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ በኦሮምኛ ቋንቋ የሚሰጠው ትምህርት ከምዋዕለ ሕጻናት እስከ 8ኛ ክፍል ያሉትን የሚያካትት ነው።

በአመቱ 50ሺ ተማሪዎችን ለማስተማር እቅድ ተይዟል እስካሁንም 35ሺ ተማሪዎች ተመዝግበዋል ይላል መረጃው።

ምዝገባው በአራዳ፣በቂርቆስ፣በአዲስ ከተማ፣ልደታና በሌሎች ክፍለ ከተሞች በሚገኙ 125 ትምህርት ቤቶች መካሄዱን ተናግረዋል።

ከምዋዕለ ህጻናት እስከ 8ኛ ክፍል በኦሮምኛ ቋንቋ ይሰጣል የተባለው ትምህርት እንደ አንድ ትምህርት አይነት ሳይሆን በመደበኛነት በየትምህርት ቤቶቹ ከሚሰጡት ትምህርቶች ጎን ለጎን እንደሚሰጥም ነው በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የኦሮምኛ ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ ብርሃኑ ከበበው የገለጹት።

ለትምህርቱ መርጃ የሚሆኑ አንድ መቶ ሺ መጻህፍት ታትመው ለየትምህርት ቤቶቹ መሰራጨታቸውም ታውቋል።

ይህንኑ ትምህርት ለማስተማር የተመረጡ 1 ሺ 6 መቶ መምህራንም ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በዝውውር ከኦሮሚያ ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ታውቋል።

በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ይሰጣል ለተባለው የኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት የመማሪያ ክፍል ጥበት እንዳይጋጥም ለማስፋፊያ የሚሆን 3 ቢሊየን ብር መመደቡንም ሃላፊው አስታውቀዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ ምሁራን እንዳሉት ከሆነ እንዲህ አይነቱ አካሄድ አደገኛና ነገሮችን ወደ አላስፈላጊ አቅጣጫ እንዲሄዱ የሚያደርግ ነው።

ይሄ አካሄድ የኦሮሚያን የአዲስ አበባ ባለቤትን ለማረጋገጥ የሚካሄድ ሩጫ ነው ሲሉም ያክላሉ።-አካሄዱ ብዙ ዋጋ ሊያስክፈል እንደሚችል በማስጠንቀቅም ጭምር።

የሁሉም ከተማ በሆነችው አዲስ አበባ የአንድ አካል የበላይነትን ለማስፈን የሚደርገውን ሩጫ የሚመለከተው አካል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያስቆምም ጠይቀዋል።

መረጀው የኢትዮ 360 ነው ።

አስተያየትዎን ይፃፉ

3 COMMENTS

 1. ይች ምን አላት! “ዶሮ ሦሥቴ ሳይጮህ” ኦነግና ኦህዲድ ገና ብዙ ተዓምር ይሠራሉ። ለነገሩ ጊዜያቸው እጅግ አጭር በመሆኑ ይሩጡ፤ ህልም አይከለከልም። እኛም እየተካለበ የሚሰጠውን አጭር የመከራ ኮርስ ተል ተሎ እንማር። እኛም ጊዜ የለንም። ተያይዞ ጠፊ የኅልውና ዘመኑ አጭር ነውና።

 2. ጥሩ ቢሆንም በቂ ግን አይደለም ፤ ያው ጅምሩ ግን ጥሩ ነው ፤ ወደፊት ደግሞ እየሰፋ እና እየተደራጀ ሲሄድ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ይቻላል ፤ 50,000 ታቅዶ 35,000 ተመዝግበዋል የተባለው መልካም ሆኖ ባሉት ጥቂት ጊዜያት ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያስመዘግቡና የዘመናት ናፍቆታቸው መልስ እንዲያገኝ አናውንስ መደረግ አለበት በቂ የማስተዋወቂያ ሥራ ሳይሰራ 35,000 ተማሪ ከተመዘገበ የማሥተዋወቁ ሥራ ቢሠራ ከብዙ እጥፍ በላይ ተመዝጋቢ ይገኝ ነበር ፤

  የሆነው ሆነ እንደመነሻ ጅምሩ ጥሩ ነው ባይሆን በቂ ቅድመ ዝግጅት ከተደረገ በኋላ በርካቶች በእድሉ እንደሚጠቀሙ አይጠረጠርም ፤

  ነገር ግን ሰነፎች እንደሚሉት “አዲስ አበባን የኦሮሚያ የማድረግ ሩጫ ነው ” ይሄ ሚዛን የማይደፋ የሰነፎች እይታ ነው ፤ ፊንፊኔ ኦሮሚያ ዋና ከተማ እንደመሆኗ ኦሮሞ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ እንግዶች ወገኖቹን በስፋት የሚቀበልበት ሳሎኑ ናት ፤ መቼም በዘመናችን ብዙ ጉድ አይተናል ። ነውር እንደነውር ያልተቆጠረበትና እንደ ክብር የሚታይበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ፨ ባለጌ ተከራዮች አድብተውና ጊዜ ጠብቀው አከራያቸውን እየከዱ ከቀበሌ ተሞዳሙደው በራሳቸው ስም ቤቱን አዙረው አከራያቸውን ሲከዱና ሲያስለቅሱ በቅርቡ ታዝበናል ፤

  ከዚሁ ልምድ ይመስላል የኦሮሞ ሳሎን በሆነችው በአ አበባ (በፊንፊኔ) ተጠግተው ለዘመናት የኖሩ የተዋለዱ ሀብት ያፈሩ ወገኖች ባለቤቱን እስኪዘነጉና እንግድነታቸውን እስኪረሱ ድረስ ዝም ስለተባሉ አሁን አንዳንድ ሥራዎች መሠራት ሲጀመሩ መደንገጥ የጀመሩት ፤

  ባለርስቱን እስካወቃችሁና እስካከበራችሁት ድረስ ምን ያሰጋችኋል? ያው የትናንቱ ደግና አቃፊ ባለርስትኮ ነው ዛሬም ያለው ፤ ያባቶቹን ደግነት ሳያጥፍ ሁሉን እንደወገኑ የሚያይ እንደ ትናንቱ ብዙ ማንጓጠጦችን በሆደ ሰፊነት ችሎ ሁሉም በጋራ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚተጋ ።

  እና የገዛ ርስቱን ላስተካክል ላሰማምር ለእናንተም ምቹ ሁኔታን ልፍጠር፤ ባለ መደንገጥን ምን አመጣው? ይልቁንም ቋንቋው ለእናንተም ጠቃሚ ነውና ብትማሩት ያግባባችኋል እንጂ ምን ትከስራላችሁ? የኦሮምኛና የአገውኛን ቋንቋ ስይጣን ነው የፈጠራቸው ሲል ያልተጻፈ የሚተረጉም ጌታቸው ኃይሌ ራሱ ይንተባተበት ነበርኮ፥ የቀበሮዋ ነገር ሆኖበት እንጂ። ቀበሮዋ ከፍ ያለ የበሰለ ወይን አይታ ልትቆርጠው ብትዘል ብትዘል አልደርስበት ስላለች ይሄ ወይን ጥሬ ነው ብላ እንደሄደችው ማለት ነው ፤ ጌቾም ቋንቋውን በስተርጅና ለማወቅ ቢንተባተብ አልሆን ቢለው ሰይጣን ነው የፈጠረው ብሎ ሌሎች ወገኖቹም ተምረው እንዳይጠቀሙበት እንቅፋት አኖረላቸው ፤ እንጂማ ሰይጣን ቋንቋን የመፍጠር አቅም ቢኖረው ምነው ሰይጣናዊ ለሆነው ለርሱም ገልጾለት ለእናንተም እንዲገልጽላችሁ መንገዱን አልመራችሁ?

  በመሆኑም ሳሎኑን ብቻ አይደለም በጓዳውም እያኖራችሁ ያለውን ይህን አቃፊ ወገናችሁን እንደ ጠላት ከማየት ተቆጠቡ፤ በገዛ ርስቱ ለዘመናት አሉ የተባሉ ስድቦችን በቅብብሎሽ ቢጠግብና ታሪኩ ተበርዞ ተሰርዞ ተደልዞ እርሱ በሰራው ጀብድ ሲወዳደሱበት ሁሉ ያን ከቁብ ሳይቆጥር ይቅር እያለ ዛሬም ወገኖቼ ናችሁ ተዋልደናል ተዛምደናል እያለ ቻይነቱን እያስመሰከረ ይገኛልና እዚህ ገር ሕዝብ ላይ ደባ መስራትን ፈጣሪስ መች ይወዳል ፤ እንጂማ እንደየዘመናቱ ከመካከላችሁ እየወጡ መርዝ በሚተፉ ክፉዎች ምክንያት ” ቁጥር አንድ ጠላት ናችሁ “ብሎ መች ደመደመ???

  በመሆኑም እየሆነ ባለው ከመደንገጥ ቀርቦ መጠቀሙ የተሻለ አይሆንም? ክፉዎች ከውስጣችሁ በቅለው ጠብን ዘርተው እንዳትረጋጉ ከማድረግ ውጭ ሌላ ሥራ የላቸውም ፤ በቅርቡ እንኳ በአንዳንድ የአማራ ክልል ከተሞች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ይሰጠን ጥያቄ ክልሉ ወይም የከተማ አስተዳደሩ ባለመመለሱ ሕዝቡ ወደ ሚዲያ ቀርቦ ብሶቱን ሲገልጽ ታዝበናል ፤ ምክንያቱም መሬት ሰው ስለወደደ ብቻ እየተቆነጠረ የሚሰጥ አልሆነም ፤ በዚህ ሁኔታ ላይ አክቲቪስቶቻችሁም አንዳች ያሉት ነገር የለም ምክንያቱም መሬቱ የአማራ ክልል በመሆኑ ይሄን ባላየ ባልሰማ ማለፉ ለእነርሱ የተሻለ ስለሆነ ፤

  ኦሮሚያ ሲመጣ ግን ለዘመናት ማንም እንዳሻው የቻለውን ያህል ተንሰራፍቶ መሬት ይዟል ፤ አሁን አሁን ግን በአግባቡ ለመጠቀም ወደ ህግ ቀንበር ለማስገባት ሥራ መሠራት ሲጀመር የአክቲቪስቶቻችሁ አፎች ከያቅጣጫው የሚችሉትን ያህል እየተለጠጡ መርዝ መርዝ የሆኑ ቃላትን ይተፉ ያዙ ፤

  “የሰብአዊ መብት” ተከራካሪነትን በኦሮሚያ መሬት ላይ ተለማመዱበት፤ የሚገርመው ምንም እንኳ የህጋዊነት ጉዳዩ ራሱን የቻለ ፕሮሰስ ቢሆንምና አስተዳደሩ ማስተር ፕላኑን ተከትሎ ቦታው ለተለያየ ጉዳይ እንደሚፈለግ አረጋግጦ ወደ ስራ እስኪገባ ሕግን ባልተከተለ መልኩም ቢሆን ቤት የሰሩ ዜጎች ሰብሰብ ብለው መኖር ስለጀመሩ መብራት እና ውሃ የማግኘት መብታቸውን አክብሮ መስመር ስለዘረጋላቸው ማመስገን ሲገባና ፥ በቦታው እስከነበሩበት ጊዜ ድረስ ለተደረገላቸው ትብብር ክልላዊ መንግሥቱን ማመስገን ሲገባ እንደ ባለ ርስት እና ባለ መብት ውግዘትና ጫጫታ አልፎም ውሃና መብራትን እንደ ካርታ በመቁጠር ሁካታ መፍጠር ተገቢ አልነበረም ፤

  አሁን ደግሞ ትምህርት በፊንፊኔ ላይ በኦሮምኛ ቋንቋ የመሰጠቱን ጉዳይ እንደ በጎ እድል ተጠቅሞ እንደ መማር ጫጫታ ለመፍጠር መሞከርና በሌላ መልክ እንዲታይ መጣር ጥሩ አይደለም ፤ ዳሩ ሃሳባችሁ ሁሌም ተቃርኖ ነውና ብትንጫጩበትም አይገርምም፤ በጫጫታችሁ የሚለወጥ ነገር ባይኖርም ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.