የበላይ መኮንንም የዳንኤል ክብረትም ስህተት – ውብሸት ሙላት

በላይ መኮንን፣ ሕግ ትምህርት ቤት እያለን ማታ ማታ ሊማር ሲመጣ አየው ነበር፡፡ ሕግ ትምሀርት ቤት አየው ስለነበር ሕግ ተምሯል የሚል ግምት በላይ መኮንን ከድቁና አልፎም ቅስና አለው፡፡ ከእዚህ አንጻር በላይ መኮንን የሕግ ዕውቅት፣ የቤተ ክርስቲያን ሕግጋት ዕውቀትም ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይሁን እንጂ፣ በላይ መኮንን በሕግ ትምህርት ቤትም ይሁን በቤተ ክርስቲያን የተማራቸውን ትምህርቶች አፍስሷል፡፡ የተማረው ከጠፋበት ወይም ከተረሳው “አፍስሷል” ይባላል በቤተ ክርተስቲያን ትምህርት ቤት ብሂል፡፡ እንደምንድን ነው አፈሰሰ መባሉ የሚል ካለ እነሆ!

ብፁእ አባታችን

በሕግ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ዓመት ላይ (በድግሪም ይሁን በድፕሎማ) ከሚሰጡት ትምህርቶች አንዱ የሰዎች ሕግ (Law of Persons) ይባላል፡፡ በተፈጥሮም በሕግና በመቋቋም ሰው የሆኑትን ሁሉ መብታውን ግዴታቸውን ችሎታና ሥልጣናቸውን የሚጠናበት ትምህርት ነው፡፡ ይህ ትምህርት በዋናነት የሚሰጠው የፍትሐ ብሔር ሕጉ ላይ ተመርኩዞ ነው፡፡

በፍትሐ ብሔር ሕጉ ላይ በሕግ ሰው እንደሆኑ ዕውቅና ከተሰጣቸው መካከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አንዷ ናት፡፡ በላይ መኮንን ካልረሳው፣ ቢረሳውም የፍትሐ ብሔር ሕጉን ገልበጥ ገልበጥ ቢያደርግ፣ አንቀጽ 398 ላይ ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሕግ ነው የተቋቋመችው፡፡ በሕግ ሰው ናት፡፡ አንድ ሰው፡፡ እንደሰው የራሷን አሠራር፣ሕግና ደንብ የማውጣት ሥልጣን ተሰጥቷታል፡፡ የፍትሐ ብሔር ሕጉ አንቀጽ 398 እና 399 ላይ በግልጽ የተቀመጠ ነው፡፡

አይደለም በላይ መኮንን፣ክልል መንግሥታት እንኳን ይህን ሕግ ወደ ጎን በመተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሳትፈቅድ ሌላ ቅርጫፍ፣ የክልል ቤተ ክህነት ወዘተ የሚባል ነገር መክፈትም ማቋቋምም አይችሉም፡፡ ሕጉ ግልጽ ነው፡፡ በላይ መኮንን ቢያፈስም፡፡

በፍትሐ ብሔር ሕጉ ላይ በተሰጣት የሕግ ሰውነት እና ሥልጣን መሠረት የራሷ ሕግና አሠራር አውጥታ እየተጠቀመችበት ነው፡፡ ዋናው የአስተዳደር ሕጓ ቃለ አዋዲ ይባላል፡፡ በቃለ አዋዲው መሠረት ጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ሀገረ ስብከት፣ ወረዳና አጥቢያዎችን የያዘ ባለ አራት እርከን አስተዳደራዊ መዋቅር አላት፡፡ በላይ መኮንን የቤተ ክርስቲያኗን ሕግ ወደ ጎን በመተውና የብሔር ፖለቲካን በማስቀደም ወይም ይህንን ሕግ በመዘንጋት አሊያም በማፍሰስ አለማወቁን መረዳት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው የቃለ አዋዲው እንዲሻሻል ጥያቄ ማቅረብም አይደለም፡፡ ቃለ አዋዲ የሚሻሻልበት የራሱ ሥራትና ሂደት አለው፡፡ ሥራቱንና ሂደቱን ሳይጠብቅ አንድ አዳራሽ ውስጥ መግለጫ መሥጠት፣ ቤተ ክርስቲያንን በ30 ቀናት ምላሽ እንድትሰጠው መጠየቅ በክህነት ላይ ድፍረት ነው፡፡ በክህነት ላይ መዘባበት ነው፡፡ ቃለ አዋዲው ይሻሻል ቢባል እንኳን ጥናት ተደርጎ፣ ሲኖዶስ ተሰብስቦ ከእዚያ በኋላ ነው የሚሆነው፡፡

በላይ መኮንን ብቻ ሳይሆን ዳንኤል ክብረትም ቢሆን ትክክለኛ ጥያቄ የተሳሳተ መልስ በሚል የጻፈው የተሳሳተ ነው፡፡ መልሱን (ማን እንደሰጠ ባታወቅም፣ ባይጽፈውምም) ትክክልም ስህተትም ነው ለማለት ልቦናው የነገረውን መለኪያ በማድረግ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት መሠረት አድርጎ መሆን ነበረበት፡፡ ጥያቄ ያቀረቡትን ካህናት የቤተ ክርስቲያን ቅናት ቢያድርባቸው ነው (የቤትህ ቅናት አቃጠለችኝ እንዲል መጽሐፍ ቅዱስ) በማለት ጥያቄው ትክክለኛ ነው መልሱ ግን ስህተት ነው በሚል ራሱ ተሳስቷል፡፡ መልሱ የሚመለሰው የፍትሐ ብሔር ሕጉንና ቃለ አዋዲውን መሠረት አድርጎ እንጂ በልበ ብርሃንነት የሚሆን አይደለም፡፡

በዚያ ላይ በኦሮምኛ ቋንቋ አግልግሎት ለመሥጠት በአጥቢያ፣በወረዳ፣በሀገረ ስብክት ደረጃ እንጂ ለሕዝብ የሚቀርበው በክልል ደረጃ ሁሉንም ወደ ላይ በመሰብሰብ እንዴት ይሆናል? በክልል አዲስ አበባ ላይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እያለ እዚያ ግቢ ውስጥ ለበላይ መኮንን የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ሃላፊ ሆኖ ቢሮ ቢሰጠው እንዴት ነው ኦሮሚያን ከአጥቢያ፣ወረዳና ሀገረ ስብከት በተሻሻለ አግልግሎት ይሰጣል የሚያሰኘው? በክልል ደረጃ ቤተ ክህነት ይቋቋም ቢባል እንኳን አሁን ካለው የጵጵስና ማእረግ የተለየ ማእረግ መኖር አለበት፡፡ ዳንኤል ክብረት ለትክክለኛ ጥያቄ፣ የተሳሳተ መልስ በሚል የሰጠው መልስ በቤተ ክርስቲያን ሕግጋት ሲታይ ዳንኤል የተሳሳተ መልስ በማለት የሰጠው መደምደሚያ ራሱ የተሳሳተ ነው፡፡

በአጭሩ፣ በላይ መኮንንን የፍትሐ ብሔር ሕጉንም ቃለ አዋዲውንም በመጣስ ከቤተ ክርስቲያኗ ሕግና ሥራት የወጣ ነው፡፡ በእዚህ መንገድም በፍትሐ ብሔር ሕጉ አንድ ሆና የተቋቋመችን ቤተ ክርስቲያን በክልል፣ በምናምን ቅርጫፍ ወይም ቢሮ ላቋቁም ነው ማለት ሕገ ወጥነት ነው፡፡ ከሕግ ውጭ ነው፡፡ ዳንኤል ክብረትም ቢሆን ቢያንስ የቤተ ክርስቲያኗን ሕግና ሥራት የጣሰ ሕዝብን የሚያደናግር አስተያየት በመሥጠቱ በዲያቆንነቱ በአባቶች የሚያስገጸው ነው፡፡ እንደ በላይ መኮንን ሕግ ወጥ ድርጊት ፈጽሟል ባያሰኝም፡፡

ውብሸት ሙላት

2 COMMENTS

  1. “The brilliant lawyer ” tries to teach us about law by itself, but not about justice. If he is a rational thinker, he should have to study about the history then Ethiopian orthodox churches in the last 150 years. Then can fully understand the authorities that committed by this institution.

    All wickedness in the Ethiopian politics spring from the Ethiopian orthodox churches all the times till now. But no more! Everyone is aware  of its wickedness. Now it is better, if you stop your malicious tactics and empty crying. It will not help you anymore.

    The main source of racism, discrimination, economic and political corruption in Ethiopia is the Ethiopian orthodox churches. Since the era of Menilik it is the right hand of the government. It is and was used as tools, in orderto to discriminate other languages and cultures. One thirds of the Oromo land were controlled by such evil doers. Now they make delibretly noises.  But there will never comeback to the old era. Enough is enough. Brig what ever you have in your corrupted stores. We will see who will be affected more.

  2. ጋመዳ ነብስህ ተጨነቀች በግል ኑሮህ ትጎዳለህ አስብበት ኢትዮጵያ የሀሳብ አፍላቂዎች ደሀ አይደለችም ለዛሁሉ ስድብ ስትጽፍ ሳታውቀው አእምእሮህ ይመረዛል ከተመረዘም ቆይቷል። ለመሆኑ ይልማ ዴሬሳንና ሎሬት ጸጋዬን ታውቃቸዋለህ?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.