አስቡበት … የቅዱስ ፓትርያርኩና የአቶ ደመቀ መኮንን አጭር የሸራተን ውይይት

 አቢቹ በስብሰባው ላይ አልተገኘም። ፓትርያርኩም ወደ ቤተ መንግሥት አልሄዱም። ይኸው ነው።
ቅዱስ ፓትርያርኩና ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለአጭር ደቂቃዎች በሸራተን ሆቴሉ ስብሰባ ተነጋግረዋል።
ቅዱስነታቸው፦ “ እኔ ዛሬ የመጣሁት ትናንት ዛሬ እሱ ይመጣልእና እባክዎ ይምጡና ያግኙት ስለተባልኩ ነው እንጂ የማይመጣ መሆኑን ባውቅ እኮ አልደክምም ነበር።
አቶ ደመቀ መኮንን፦ እውነት ነው ብፁዕ አባታችን ሊመጣ አስቦ ነበረ። ከመንገድ ነው የገባው። ጫናም በዝቶበታል። ነገር ግን በአጭር ቀን ተገናኝታችሁ ትወያያላችሁ። እሱ ራሱም ይደውልሎታል።

ቅዱስነታቸው፦ ነገሩን ጉዳዩን አታቅሉት። በቶሎ መፍትሄ ብትፈልጉ ይበጃል። ይሄንኑ ነው የምለው። አስቡበት።
አቶ ደመቀ መኮንን፦ እሺ አባታችን…
ነሐሴ 28/2011 ዓም

ነገሰ ተፋረደኝ

 

 

1 COMMENT

  1. ብጹእነታቸውን ሥልጣን ላይ ያወጣ ህወሓት ነው። የህወሓትን ሥራ እንዲፈጽሙ። ባንድ ጀንበር አሳባቸውን ቀይረዋል ነው የምትሉ?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.