አርቲስት ተዘራ ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በበርካታ ፊልሞች ላይ በትወና የሚታወቀው አርቲስት ተዘራ ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አርቲስት ተዘራ ለማ ትናንት ምሽት ቤቱ ውስጥ እያለ በድንገት ህመም ካጋጠመው በኋላ በአካባቢው ወደሚገኝ የህክምና ማዕከል ቢወሰድም ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

“ውሳኔ ፊልም” ላይ መጀመሪያ የትወና ስራውን የሰራው አርቲስት ተዘራ ከዚያን ጊዜ ወዲህም ከ20 በላይ ፊልሞች ላይ የተለያዩ ገፀ ባህሪያትን ተጫውቷል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ፥ ፍቅር ባጋጣሚ ፣ ታስጨርሽኛለሽ፣ ፍቅር በይሉኝታ፣ አልወድሽም፣ ወንድሜ ያቆብ፣ ኢንጂነሩ እና ጥቁር እና ነጭ ተጠቃሽ ናቸው።

አርቲስት ተዘራ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለአርቲስት ተዘራ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች እና የሙያ አጋሮች መጽናናትን ይመኛል።

ኤፍ.ቢ.ሲ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2011

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.