አንዲት የራያ እናት ዛሬ በጠ/ሚር ጽ/ቤት ተገኝተዉ ለጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ምክትል ጠ/ሚር ደመቀ መኮንን የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት አቅርበዉ፤ የራያ ባህላዊ ልብስ አልብሰዋቸዋል

Meskerem Abera

ይህ የራያን ልብስ ስጦታ ተቀብሎ መልበስን ብቻ የሚያመላክት ነገር አይደለም።የአዴፓው አቶ ደመቀ ባሉበት ጠ/ሚውም ይህን ልብስ ለብሰው የተነሱት ፎቶ በአደባባይ ሲለቀቅ የራያ ህዝብ የሚያደርገውን በአማራ ክልል የመካለል ጥያቄ በዋነኞቹ ሰዎች ዘንድ እውቅና እንደተሰጠው የሚገልፅ ነገርም አለው።

አዴፓ በግዛትህ ልተዳደር የሚለውን የራያ ህዝብ ጥያቄ በተገቢው መንገድ በግልፅ መደገፉ አልሆን ብሎት ሲሽኮረመም ኖሯል። በአንፃሩ ህወሃቶች ከአማራ ክልል ተገንጥዬ ልቀላቀላችሁ ያላላቸውን የቅማንት እንቅስቃሴ አማራ ክልልን ስለሚረብሽላቸው ብቻ ይሉኝታቸውን ጥለው በግልፅም ሆነ በስውር ያበረታቱታል። የኦዴፓ ተሽኮርማሚ ባለ ይሉኝታነት ግን የራያ ህዝብን ትግል ጎድቶታል። ለማንኛውም ይህ ጥሩ ምልክት ነው።

ህወሃት ይህን አለባበስ(ምን ማለት እንደሆነ ስለሚገባው) አይቶ ቱግ ማለቱ አይቀሬ ነው። ለኦዴፓ እና አዴፓ ይቅርታ ሊጠይቁኝ ይገባል ሊልም ይችላል! ወይ ደግሞ ሁለቱንም የሚያጥረገርግ ደብዳቤ እየፃፈም ይሆናል

 

2 COMMENTS

  1. ኢትዮጵያዊነት ከልብስም በላይ ነው፡፡ ያምራል!!! ልብ ያለው ልብ ይበል አንድነት ከምንም ይበልጣል፡፡
    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡

  2. እንዴት አምሮባቸዋል? እንዲህ መልበስ ሲቻል ሱፍ ምን የሚሉት ነገር ነው?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.