የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 31ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ተከበረ

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 31ኛ ዓመት በዓለ ሲመት በተከበረበት ወቅት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለምታቀርባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ባለመስጠቱ ቤተክርስቲያኗ ለተደራራቢ ችግሮች መዳረጓ ተገልጿል፡፡

ቤተክርስቲያኗ የገጠማትን ወቅታዊ ፈተና ለማለፍ ዋናው መንገድ መንግስት የሀገርንና የቤተክርስያኗን ሰላም ለማስጠበቅ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባና፣ በመቀራረብና በመነጋጋር የተዘጋጀውን የሕግ ማዕቀፍ በመተግበር ቤተክርስቲያኗን በክብር ጠብቆ በማስቀጠል ለትውልድ ማስተላለፍ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ተመለክቷል፡፡

የብፁዕነታቸው በዓለ ሲመት ሲከበር፤ ብፁዕነታቸው በተወካያቸው አማካኝነት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ቤክርስቲያኗ ቀደም ሲል የነበሩባትን ችግሮች በመፍታት በእርቀሰላምና ሲኖዶሳዊ አንድነት ለበዓለ ሲመታቸው በመድረሳቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.