ጃዋር ሆይ፤ የሚሚን ዛሚ ከኪሳራ መታደግ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ማላገጥ ነው! (ከአበበ ቶላ ፈይሳ

ጃዋር የሚሚ ስብሃቱን ዛሚ ራዲዮ ገዛ የሚለውን ወሬ እንደሰማው ተጨባጭ ማስረጃ ካላየሁ አላምንም ብዬ ነነር። ትላንት ጃዋር የእንኳን ደስ አላችሁ አዋሽ ኤፍ ኤም ስራ ጀምሯል ብሎ የለጠፈው ፎቶ ላይ በርቀት ዛሚ የሚለውን ፅሁፍ ሳይ እውነትነቱን አረጋገጥኩ።

ሚሚ ስብሃቱ ማለት በትግሉ ወቅት በሚገደሉ በሚታሰሩ በሚቃወሙ የኦሮሞ እና አማራ ወጣቶች ላይ ስታላግጥ የነበረች ከዛም አልፋ ትርፍ በአደባባይ እከሌ ይታሰር ይቀፍደድ እያለች በራዲዮ ጣቢያ የእስር ጥቆማ ስትሰጥ የነበረች ሴትዮ ናት።

ይቺ ሴት ከለውጡ በኋላ ራዲዮ ጣቢያዋ ከስሮ ተዘግቶ ነበር (መሰለኝ) ዛሬ ጃዋር ከኦሮሞ ህዝብ በሰበሰበው ገንዘብ የሚሚ ስብሃቱን ኪሳር ሲታደጋት ስታይ ምንስ መፅሃፉ “የሚጠሏችሁን ውደዱ” ቢል ምንስ ፍቅር ያሸንፋል ቢባል… አንዲት ቀን እንኳ በስራዋ ተፀፅታ ይቅርታ ያላለችን ሴትዮ ኪሳራ በህዝብ ገንዘብ መሸፈን ምን ይሉት መልዓክትነት ነው?

እውነት እውነት እልሃለሁ ጃዋር ይሄ በኦሮሞ ህዝብ እንባ እና ደም መቀለድ ነው!

2 COMMENTS

  1. The Oromo nation has very rich cultures which promote love and forgiving. The woman has lost her war and now she is a normal citizen. Therefore, we have to show her the greatnesses of the Oromo.

    Jawar keep on such marvelous job!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.