ሰበር ዜና… እስክንድር “የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው” ጃዋር መሐመድ (ቀሲስ ኤፍሬም)


* የኦሮሚያ ፖሊስን “እወቅልኝ” ብሏል ጃዋር፣
* እስክንድር አሁንም ጥሪውን በመሰረዝ የቤተ ክርስቲያን ጥሪ ሌላ ትርጉም እንዳይሰጠው ማድረግ አለበት እንላለን፣

” ባልደራስ” የተባለው እንቅስቃሴ መሪ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይና ከአዲስ አበባ ጋር በተገናኘ መግለጫ ለመስጠት ጥሪ ማድረጉን ተከትሎ “ይህ ሰውዬ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው። ልክ እንደ አባይ ጸሃዬ ነው። እነሱ ያወሩትን ወሬ ያወጣል። በር ዘግተው ያሴሩትን ሴራ እሱ አዳባባይ ያወጣል” ሲል በፌስቡክ ገጹ አስተያየት የሰጠው ጃዋር መሐመድ ነው።

የኦሮሚያ ፖሊስን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን “እንዲያውቁት” ግልባጭ አድርጎላቸዋል። የጃዋር “አስተያየት” እንደ “ትእዛዝ” እንደሚቆጠር በብዙ ገጠመኞች እንደታየ ማስታወስ እንችላለን።

——
SHARE!!!
ሌሎችም ቢያነብቡት ይጠቅማል ብለው ካሰቡ ሼር ያድርጉ። ከጽሑፉ ውስጥ እርስዎ በግልዎ ሊያደርጉት የሚገባዎ ነገር ያለ ከመሰልዎ ከማድረግ ወደኋላ አይበሉ። ያነበቡትን በሚጠቅም መልክ ሥራ ላይ ማዋል ሃይማኖታዊም ሀገራዊም ግዴታ ነው።

ቀሲስ ኤፍሬም

2 COMMENTS

  1. አሁን በጣም አሳዛኝ የኢትዮ ታሪክ ምእራፍ ላይ ደርሰናል ። በግልም ሆነ በድርጅት የሚደረግ ማንኛቸውም ሂደቶች ጊዜአችን ነው ወይም ተረኞች ነን በሚሉት ግለሰቦች ና ድርጅቶች የኢትዮጵያን እጣ ፈንታ ለመመንዘር ሽር ጉድ ሲሉ አሁን እያየን ነው። የነርሱ ሽርጉድ ሳይሆን አሳዛኙ ጉዳይ ፣እነርሱ በእስክንድር ላይ ያወጁትን ጦርነት ፣የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተቆርቋሪ መሳዮች፣ የጀዋርና መሰሎቹን አርማ ይዘው የሚያውለበልቡት ናቸው ።
    እስክንድር በተለያየ ጊዜ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ባደረገው ሙከራ ምን አይነት እንግልት አና ጭቆና አልፎም የባልደራስ አባላት መታሰራቸው ይታወቃል። የዚህን ጊዜ ቀሲስም ሆነ መምህር አንድም ድምፃቸውን ያሰሙ የሉም። ገና ለገና ጀዋር እንዲህ ብሏል ብሎ የግለሰብም ይሁን የድርጅትን ዴሞክራሲያዊ መብት መጋፋት ፣ከየትኛው ጎራ አዛኝ መሳዮች እንደተፈለፈሉ የኢትዮ ፓለቲካ ሂደት እያሳየን ነው። ጀዋር ኃይሎችነው ለመከከፋፈል የሚያደርገውን ጥረት በተዘዋዋሪ አጋር መሆን በመጨረሻው አስጠያቂ ነው ። የህዝብ ሂደት ጀዋር ምን አለ ተብሎ አይደለም ስልት የሚወጣው።ይሄ ምናልባት ለተከታዮቹና ለኦዴፓ ሊሆን ይችላል ።
    የኦርቶዶክስ ሐይማኖት ተከታዮች በኦሮሞ ብሔረሰብ ከ45% በላይ መሆናቸው ነው የነጀዋር ስጋት። ለዚህም ነው የጎን አርእስት እየፈለገ እነ እስክንድርን ለማሳጣት የሚዳዳው። ይሄም ፍራቻ ነው፣ የኦሮሚያ ፓሊስ በግዛታችን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የመስከረም 4 ጥሪ አልተፈቀደም እውቅና የለውም ብሎ መግለጫ ለመስጠት የተገደደው ። ሰለዚህ ኦርቶዶክስም ተከታይም ያልሆነ ነግ በኔ ብሎ ይሄንን ጥሪ ተቀብሎ ተቃውሞውን በሰፊው ማሳየት ያለበት።
    መስከረም 4 ትን በተመለከተ ሁሉም ለአዲስ አበባ የቆመ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ የሚል ኃይል ሁሉ በአጋርነት ሃገሪቱን ማዳን ያለበት ። ጃዋር በየቀኑ የአይምሮ ፅንስ ጭንግፍ ባስወረደ ቁጥር ለርሱ መልስ ለመስጠት መሯሯጥ እኔ ነኝ ብሎ እንዲያብጥ አድርጎታል። ይህ ያልገባው አንደኛውን ዝም ቢል ፣ሌላውን ለተጨማሪ ሰህተት አይዳርግም። አበው ብለዋል “ብረት በግለቱ ” ። አሁንም እንደ እስክንድር በጉዳዩ መረባረብ ትክክለኛ ሂደት ነው።

  2. እስክንድር እና ጃዋር ለአገራችን ፖለቲካ ጠንቅ ናቸው። ሁለቱም አክራሪዎች፣ ዝና ፈላጊዎች ናቸው። ሁለቱም በግርግር የተገኙ እንጂ አንዳች ቁምነገር በመሥራት አይታወቁም። እስክንድር እስር ቤት መክረሙ ማንነቱን ሸፍኖለት ነበር። አሁን ሲገለጥ ለካንስ ኦሮሞ ጠል፣ አክራሪ አማራነት የተጠናወተው ነው። ጀዋር ሥራ ፈት የነበረ፣ ውጭ አገር እንደ ኦ ኤሜ ኤን ሎተሪ ወጥቶለት “ቄሮ ቄሮ” እያለ እንደ ቁራ በርሮ አገር የገባ ነው። ሁለቱ ግለሰቦች ረብሻ በማነሳሳት ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ይገባል። ቡራዩ ላይ ስለ ተፈጸመው ግድያና ረብሻ ፍርድ ፊት መቅረብ ይገባቸዋል!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.