ጥሩ አማካሪ የሌለው መሪ (ግርማ ካሳ)

ፕ/ሚ አብይ አማካሪ አድርጎ ከጎኑ የኮለኮላቸው ‘እሼ ጌታዬ” የሚሉ ሰዎችን፣ የስነ ልቦና ምሁራንን፣ ዲያቆናትን ነው፡፡ የፖለቲካ ስትራቲጂስቶች የሉትም፡፡ ቻሌንጅ ቲካ ስትራ አማካሪዎች የሉትም፡፡ ስለዚህ በሚያደርጋቸው ስራዎች እግሩ ላይ እየተኮሰ፣ ራሱን በራሱ ከጭዕዋታ ውጭ እያወጣ ወደ እየሄዴ ነው፡፡

ከዚህ በታች የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነች አንድ እህት የጻፈችውን እንደሚከተለው ላስነብባችሁ፡፡ እንደዚች አይነት እህት አማካሪ ቢኖሩት ኖሮ ይሄን ጊዜ ትሩ ነገ ሊመጣ ይችል ነበር፤፡

=================
ቤተመንግሥታቸውን ባሳደሱ ማግሥት፡ የፈረሰውን ቤተእግዚአብሔር መልሰው እንዲያሳንጹ ተጠየቁ፤ እምቢኝ አሉ! አለመታደል!

የዛሬውን የቅዱስ ሲኖዶስና የጠቅላዩን ውይይት ቃል በቃል የተከታተሉ ውስጠ-ዐዋቂዎች እንደነገሩን፡ ጠቅላዩ፡ በቤተክርስቲያን ላይ ስለደረሰው በደል፡ “ይቅርታ አልጠይቅም፤ ቤተ ክርስቲያንም አልሠራም” ብለዋል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር፡……ማ ተጎዳ?!!

ሲጀመር፡ ቤተክርስቲያን ለመሥራት፡ ሰው እግዚአብሔርን ደጅ ይጠናል እንጂ፡ እግዚአብሔር፡ የተቃጠለ ቤተክርስቲያን ምክንያት አድርጎ፡ በካህናት አንደበት የተገላቢጦሽ ሰውን ደጅ ሊጠናው ይገባ ነበር ወይ?!

ላለፉት 2000 ዓመታት፡ ከኢትዮጵያ ነገሥታትና ንግሥታት፣ መሳፍንትና መኳንንት፣ ልዑላንና ልዕልታት፣ ባለጠጎችና መናኞች፣ ባላባቶችና ባለርስቶች መካከል፡ ዕድሉ እንዲገጥመው ለእግዚአብሔር ተስሎ፡ ቤተ ክርስቲያን ያላነጸ መሪ ማንም የለም። ስሙ ከአምላክ ስም ጋር በመቅደሱ ዐብሮ እንዲታወስ ያልለመነ አስተዳዳሪ በኢትዮጵያ ምድር አልተፈጠረም። በዘመነ ኦሪት የነበሩትም ነገሥታት፡ የኦሪት መሰዊያ ከማሥሰራት ወደኋላ ያሉበት ጊዜ የለም። ከነርሱ ቀድሞ፡ ከሦስት ሺህ ዓመት በፊት፡ በአበው ዘመን፡ ከአዳም ጀምሮ የተሰጠው ሀብተ ክህነትና ሀብተ መንግሥት በረከት ተካፋይ ለመኾን የፈለጉ መሪዎች ኹሉ፡ በመላ የኢትዮጵያ ተራሮች ላይ መሰዊያዎችን በመሥራት ነው፡ ዘመነ መንግሥታቸውን የጀመሩት። በዕብራውያን መሥመር፡ የዚህ ትውፊት አስቀጣዮች የኾኑት አብርሃም፥ ይስኃቅ፥ ያዕቆብና ልጆቹም፡ በየደረሱበት የመጀመሪያ ሥራቸው፡ ለእግዚአብሔር መሰዊያ መሥራትና መስዋዕት ማቅረብ ነበር። በሐዲስ ኪዳንም፡ ቤተክርስቲያን በቂ ምዕመናን ካገኘች በኋላ፡ በየትኛውም የዓለማችን ክፍል የተነሱ ነገሥታት ኹሉ የተመዘኑት፡ ለሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት ማቅረቢያ በመገንባታቸውና ያንንም በአግባቡ እንዲተዳደር በማድረግ ወይም ባለማድረጋቸው ነው።
ይኽን ሥርዓትና ሃይማኖታዊ ምግባር በመከተል፡ ዛሬም፡ ሀብት፣ ወይም የማስተባበር ጥበብ አግኝተው ቤተክርስቲያን ለማስተከልና ስመ እግዚአብሔር በየትውልዱ እንዲጠራ ለማስደረግ፥ በዚያም ዘለዓለማዊ በረከት ለማግኘት እግዚአብሔር ዕድሉን እንዲሰጣቸው እየተማጸኑ የሚኖሩ ምዕመናን እጅግ ብዙ ናቸው። የመጨረሻ ድኃ የተባለው እንኳ፡ ለእግዚአብሔር ቤት ማስሠሪያ ከተጠየቀ፡ የሚሰጠው አጥቶ አያውቅም።

ይኽ ለ7500 ዓመታት በኢትዮጵያ የቀጠለው ትውፊት ነው እንግዲህ፡ ዛሬ፡ ጠቅላዩን “በአፍንጫቸው ሥር” ያለፋቸው። እርሳቸው በራሳቸው ተነሳሽነት ቤተ ክርስቲያን ለመትከል ጥያቄ የማያቀርቡ ቢኾን፡ እግዚአብሔር የፖለቲካውን ማዕበል ተጠቅሞ ፈተናቸው። ወደቁ!! ተ-ፈ-ጠ-ፈ-ጡ!! አበስኩ ገበርኩ!

በኢትዮጵያ ታሪክ፡ “የቤተክርስቲያን ወዳጅ ነኝ” ብሎ፡ “ንጉሥ ሆይ ምን ነካህ? ቤተክርስቲያን ሥራ እንጂ!?” ተብሎ እስኪጠየቅ የጠበቀ መሪ የለም። እንደነመንግሥቱና መለስ ዜናዊ ሃይማኖት የለሽ ቢጤ ከኾነ ደግሞ፡ ጥያቄው ሲጀመርም አይቀርብለትም። ዶ/ር ዐቢይ ግን፡ በገዛ እጅ” የቤተክርስቲያን ወዳጅ ነኝ” ብለው ራሳቸውን ካቀረቡ በኋላ፡ በተግባር እንዲያሳዩ እግዚአብሔር ጠይቆ ቢፈትናቸው፡ ዛሬ “ወግድልኝ” ብለውታል።

ዐቢቹ?! ምን ነካዎት?! ቤተክርስቲያን ለመሥራት እኮ የግድ ካህን እስኪገድሉ መጠበቅ የለቦትም?! እንደሥርዓቱማ፡ እንደቅዱስ ዳዊት እግዚአብሔርን ለምነው፥ ነቢያት ካህናትን ደጅ ጠንተው፥ “የአምላክን ቤት ልሠራ ተፈቅዶልኛል ወይ” ብለው ሊጠይቁ ይገባዎት ነበር። “የእግዚአብሔር ወዳጅ ነኝ” የሚል ኹሉ የሚቀርብለት ፈተና ለእግዚአብሔር መሰዊያ መሥራት ነው፤ ጥንት ለሚቃጠል መስዋዕት፥ ዛሬ ደግሞ ለሐዲስ ኪዳን መስዋዕት።

ከዚህ ውጭ ታድያ ከቤተክርስቲያን ጋር ተባብረው ሊሠሩ የሚያስቡት ሥራ ምንድነበር? ኮብል ስቶን? አይ ሥርዓተ መንግሥት አለማወቅ!

ማሳደሱንስ ቤተመንግሥትዎን አሳደሱ፤ የእግዚአብሔር ቤትስ!? ዳዊት እርሱ ባማረ ቤተመንግሥት ተቀምጦ የእግዚአብሔር ታቦት በድንኳን መንከራተቷ እጅግ ይከነክነው ነበር። ንጉሥ ማለት እንዲህ ነው። እግዚአብሔር ሰማይ ዙፋኑ፥ ምድርም የእግሩ መረገጫ ሲኾን፡ ሊፈትነን ግን በመካከላችን በሚገኘው ቤቱ ይመጣብናል። ታሪከ ነገሥትን፥ መጽሓፈ ነገሥትን፣ ክብረ ነገሥትን፣ ፍትሓ ነገሥትን… ወዘተ እያነበቡ ቢያድጉ ኖሮ የዛሬውን ፈተና ያልፉት ነበር። ማኪያቬሊን ሲያነብቡ ስለኖሩ ተፈጥፍጠውታል!

ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ኾነው ወድቀዋል!
ፕሮቴስታንት ቢኾኑም የፈተናው ጥያቄ ከዘመን ዘመን አንድ ዓይነት ነው! የኢትዮጵያ ሥርዓተ መንግሥት ዘለዓለማዊ፣ ያዕቆባዊት፣ መልከጼዴቃዊት ሥርዓት ነች። ያገኘችውን ኹሉ እንደልቧ ትፈትነዋለች፥ ማንነቱን ትገልጥበታለችም! ፌዴራሊዝም ቢሏት ዲሞክራሲ፥ ካፒታሊዝም ቢሏት ቴክኖክራሲ፡ እሷ እቴ፥ ግድ የላትም!

በመጽሐፍ ቅዱስ፡ እያንዳንዱ የእሥራኤል ንጉሥና መስፍን፡ ታሪኩ ሲጻፍ፡ ልቡ ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት እንደነበረና ቤተ መቅደስና መሰዊያዎችን አስመልክቶ ምን ዓይነት አቋም እንደወሰደ ትኩረት ተሰጥቶት ተጽፏል- በመንፈስ ቅዱስ መሪነት።

ስለዚህ፡ ታሪክ ፀሓፊዎች፡ ስለዐቢይ ሲጽፉ፡ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በኢትዮጵያ ከተነሱ መሪዎች፡ ቤተ-እግዚአብሔርን እንዲሠሩ፡ ባልተለመደ መልኩ፡ በአባቶች ጥያቄ ቀርቦላቸው “እምቢኝ” ያሉ የመጀመሪያው መሪ እንደኾኑ መጥቀስ ይኖርባቸዋል። በእግዚአብሔር ፊት የዶ/ር ዐቢይ ቋሚና ዘለዓለማዊ ማንነት ይኼ ነው።
አለመታደል ነው!

5 COMMENTS

 1. Some activists like Girma Kassa, Eskinder Nega, the arogant and rude Girma Seifu, Ermias Legesse (the chameleon) and associates may scheme certain plan to agitates violence in Finfinne. They may try everything under the sky to fulfill their political ambitions. But it is futile. Now we are in the era of Qerroo. There is no more Finfinne which you used to gallop as it pleased you. Besides that Finfinne is not an island which can stands by itself. It depends in all aspects of life on Oromia.

  Don’t dream unrealistic wishes! You cannot change certain natural things. For example,  you should have to accept the reality that Finfinne is an integral part of Oromia. No miracle will change this reality. All the residents of Finfinne have to even prepare themselves, in order to pay compensation for the uprooted Oromo from Finfinne in the last 130 years.

  The Ethiopian peoples have been suffering from man-made political syndrome of a century old which was created by greedy politicians all the times so far. All these politicians have never cared about collective and individual rights. That is why we are still struggling against all sorts of odd ideologies,  mentalities and thinking. The century old struggles of the peoples in Ethiopia have produced most of the political organizations like TPLF, OLF, ONLF, SLF and EPLF. No one of them were created by default or by accident.

  The current ethnic federal structure of Ethiopia is the political arrangements which were mainly constructed and promoted by the beloved Oromo intellectuals and OLF leaders like Gelassa Dilbo,  Lenchoo Lataa,  Dima Nagawo and others. The TPLF has accepted it by making few modification. The TPLF tried to implement it at least nominally after banning the OLF, in order to win the hearts of the Oromo nation. Therefore, the main shareholder of this federal arrangement is the OLF, the freedom fighter. Accusing the TPLF in regard of the federal structure is unfair. The TPLF must be accused for shortcomings of the implementation and wrong boundaries.  Thus, this federal structure was not implemented at the free will of the TPLF. It is a fruit of the century old bitter struggles of the Oromo nation and other subjugated nations. Consequently, accepting these federal arrangements is a must for all stockholders. The political merchants like ex-Ginbot 7  and current  EZMa make only noises temporarily which will not last long. Watch out!

 2. This article has no head and tail. Don’t you know Church and state are separate in Ethiopia?

  How can he build a temple for one religion while being a PM? He cannot do that to Orthodox protestant, catholic or islam – period!

  Your comparison to ancient history doesn’t stack up. We are in 2019!

 3. ግርማ ካሳ፤
  ወይ አንድያውን አንተ አማካሪ ብትሆን ይሻል ይሆን?
  ሥራ ካልበዛብክ እና ፈቃደኛ ከሆንክ ማለቴ ነው።

 4. Gamaada እውቀትና ማስተዋል ካንተ ርቋል እጅህ እንጅ አእምሮህ ከድቶሀል ልጅቱና ግርማ ካሳ ለሰብአዊነት ሲቆሙ አንተ ግን ለማታውቀው ለማያውቅህ ዘርህ ወገኔ ነው እኔ ነኝ ጁዋር ነው የሚያውቅለት ብለህ ትዳክራለህ
  ያንተ አይነት ስብስቦች ሊያደርሱ የሚችሉትን ጥፋት ሳስብ ይዘገንነኛል አንተ ግን አስቀድሞ ለማሰብ ስላልታደልክ የጥፋቱ ነዳጅ ሁነህ በር ትተህ ትሰራለህ።
  ማሰብን ለሰው ማስተማር ከባድ ነው በተለይም ጥላቻ በተባለው በሽታ ከተለከፈ።

 5. gaaammaddaa,
  the street bully in a rage trying to intimidate every passers by to hand over their wallet to you or else, you will shoot them. so we all have to submit to olf or else face the consequences! what that tells me is that you are marching to your own destruction. keep on marching while it is your turn !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.