ጨካኝ ጭካኔን የመረጠበት አንዳች ምክንያት ይኖረው ይሆን?? – መስከረም አበራ

ሰርካለም ፋሲል በምርጫ 97 ከታሰሩት ጋዜጠኞች አንዱ ነች።ሰርካለም ልጁን እስር ቤት ሆና ወልዳ ልጁዋን ለመንከባከብ ዕድል የተነፈጋት የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ናት። ይህን የሁዋላ ታሪክ መልሳ በማስታወስ ልብ/ጄ/ል አሳምነው ጽ/ግን ባለቤት የወቅቱን እስር ጦማሪና የዩኒቨርስቲ መምህር መስከረም ተከታዩን ጽፋለች ። ያንብቡት ሼር ያድርጉት

የወቅቱ “ሰርካለም ፋሲል”
(መስከረም አበራ)

ጭካኔ ያስጨክነኛል! እስከምጨክን ግን ጊዜ እወስዳለሁ፡፡ጨካኝ ጭካኔን የመረጠበት አንዳች ምክንያት ይኖረው ይሆን መጨከን ብቻ መፍትሄ ሆኖ አግኝቶት ይሆን፣ጨካኝ በቆመበት ቦታ ሆኜ ባየው ካልጨከነ የሚበላሽ ነገር ይኖር ይሆን በሚል በጨካኝ ላይም ቢሆን ቶሎ ላለመጨከን ከደመነፍሴ ጋር እሟገታለሁ፡፡ይህን የማደርገው አንዴ ጭካኔ ከገባኝ ለመመለስ ስሜቴ እሽ ስለማይለኝ ነው፡፡ በህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የመጨረሻ ዘመናት በጨካኙ ላይ የመጨከን ደረጃ ላይ ደርሼ ነበር፡፡ይህ ስሜቴ የኢህአዴግ ባለስልጣን ቀርቶ አሽቃባጭ ደጋፊ ሳይ ጭምር ደስ የማይል ስሜት እንዲሰማኝ ያደርገኝ ነበር፡፡ እዚህ ደረጃ ላይ ያደረሰኝ የህወሃት መራሹ መንግስት የተከማቼ ጭካኔ ላይ አንድ ሁለት ቀን በማምነው የቪኦኤ ሬድዮ የሰማኋቸው ታሪኮች ናቸው፡፡
አንደኛው አንድ አባት የሶስት ልጆቻቸው ሬሳ እንደከሰል በማዳበሪያ ተጠቅልሎ በራቸው ላይ እንደቆመላቸው ሲናገሩ የሰማሁት ታሪክ፣ ሁለተኛው በማዕከላዊ የደረሰበት ሰቆቃ በፍርድቤት በሰው መሃል ልብሱን አውልቆ ሃፍረተ ሰውነቱን እስከማሳየት ያደረሰውን ታሳሪ ታሪክ ስሰማ እና ሶስተኛው ብዙዎቻችሁ የምታውቁትን እናትን የልጇ አስከሬን ላይ አስቀምጦ የመደበደቡ ታሪክ ነው፡፡ እነዚህ ታሪኮች ቀድሜ ካነበብኳቸው ጭካኔዎች ጋር ተደምረው ሰው ባልሆኑ ፍጡራን እየተመራን እንደሆነ ይሰማኝ ጀመረና ጥላቻየም ሰውን ሳይን የሆነ አውሬን የምጣላ እስኪመስለኝ ድረስ የመረረ ሆነ፡፡ በአውሬ የመሰልኳቸው ሰው መጥላት ዘና ብየ የምቀበለው ስሜት ስላልሆነ ነው፡፡
ለማንኛውም እነዚሁ ሰዎች ተሸሻልን ብለው፣የባሰባቸውም ከስልጣን ተባረው አዲስ ዘመን የመጣ፣ ጫፍ የወጣ ግፍም አንሰማም የሚል ተስፋ ነበረኝ፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ዛሬም ሰዎች በገፍ ታፍሰው ይታሰራሉ፣ለአንዱ የተፈቀደ ነገር ለሌላው ወንጀል ሆኖ እንትን ቲቪን ለምን መሰረትክ የሚል ነገር መመርመሪያ መስቀለኛ ጥያቄ ሆኖ መጥቷል፡፡ሰው ሊጠይቅ የሄደ ሰው እንኳን ማርያም አመጣችህ ተብሎ በዛው እስርቤት ይዶላል፡፡
ከዚህ ሁሉ ብሶ እያሳዘነኝ ያለው ግን የነፍሰ-ጡሯ የጀነራል አሳምነው ፅጌ ባለቤት የወ/ሮ ደስታ ነገር ነው፡፡ይህች ሴት ከታሰረች ሁለት ወር ሊጠጋት ነው፡፡የትኛውም ፍርድቤት ቀርባ ወንጀሏ ሲነበብ እና ስትከራከር አላየንም፡፡ክስ ተመስርርቶባት ወደ መደበኛ ማረሚያቤት አልተወሰደችም፡፡ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ ታጉራለች፡፡ ከሁሉም በላይ ነፍሰጡር ነች፤የህክምና ክትትል ያስፈልጋታል፣ባሏን ያጣች ሃዘንተኛ በዛ ላይ ነፍሰ-ጡር ሴት ወንጀልሽ ይህ ነው ሳትባል እስርቤት መታጎሯ እጥፍ ድርብ ግፍ ነው፡፡
ከሴት ያልተወለደ የለም፤እናት የሆነ ሴት ሁሉ ደግሞ እርግዝናን እና የስሜቱን ክብደት ያውቀዋል፡፡የሰውን ልጅ ያክል ነገር በሆዷ የያዘች ሴት ስንት ወር ሙሉ ፖሊስ ጣቢያ ያጎሩ ግፈኛ የለውጥ አመራር ተብየ ወንዶች ከሴት የተወለዱ፣በሚስቶቻቸው በኩል እርግዝና ምን እንደሆነ የሚያውቁ ናቸው፤ሴቶቹ የለውጥ አመራር ነን ባዮች ደግሞ በየደረሱበት ስለ ሴት ልጅ መብት የሚቀባጥሩ፣ልጅ አርግዞ መውለድም እንዴት ያለ ጫና ያለው ነገር እንደሆነ የሚያውቁ ናቸው፡፡ግን ሁሉም የዚች ምስኪን ሴት ነፍስ አያሳስባቸውም፡፡ለአልጀዚራ ዶክመንተሪ ቃል ለማሳመር የምትለፋዋ ወ/ሮ መዓዛም ይህን ሳታውቅ ቀርታ አይደለም፡፡የግለሰብ ጉዳይ አይመለከታትም እንዳይባል ስለ ግለሰብ ሴት እስረኞች ያላትን ተቆርቋሪነት በአልጀዚራ ስታወራ አይቻለሁ፡፡ይህች ሴት ግን ነገስታት በክፉ አይን ስላዩዋት ብቻ ጆሮ ዳባ ትባላለች፡፡ይህን የመሰለ ጭካኔ የሚያስጨክን ሃገራዊ ፋይዳ ያለው ምክንያት የላቸውም-ተራ ጥላቻ እና ቂም በቀል እንጅ!
አንድም እናት በወሊድ እንዳትሞት የሚፈልጉት የጠላታቸው ሚስት እስካልሆነች ድረስ ነው፡፡ይህች ሴት ግን በሚታመነውም በማይታመነውም ስሙን ሲያክፋፉት ምን ያህል እንደሚጠሉት የሚሳያሳብቅባቸው የጀነራል አሳምነው ሚስት ነች! ስለዚህ አንድም እናት እንዳትሞት ከሚባልላቸው ሴቶች ውስጥ አይደለችም ፤ቢሻት ትሙት! ይህች ሴት በህወሃት መራሹ ዘመን እስርቤት አርግዛ እስርቤት ስትዎልድ ከሞት አፋፍ የተመለሰችውን ሰርካለም ፋሲልን የምትመስል የተረኛ አምባገነን መከረኛ ነች፡፡ፈጣሪ አብሯት ይሁን እንጅ ምን ይባላል?
በጣም የሚያሳዝነው ይህች ሴት ይህን ሁሉ መከራ የምታየው የአሳምነው ሚስት ስለሆነች ብቻ ነው፡፡ እንጅ የሰራችው ወንጀል ቢኖር አንቀፅ ተጠቅሶባት ስትከሰስ እንሰማ ነበር፡፡ይህ ጭካኔ የኢህአዴግ ሰዎችን አረመኔነት ፣ተበቃይነት እና ግብዝነት የሚያሳይ ነገር ነው፡፡ ነገሩ እነዚህ ባለጊዜዎች ምን ያህል ጀነራል አሳምነውን ይጠሉት እንደነበረም ያሳያል፡፡የፈለገ ቢጠሉት አሁን እሱ ሚስቱ መታሰሯን አውቆ የሚያዝንም መፈታቷን ሰምቶ የሚደሰት ሰውም አይደለም-ከአፈር በታች የሆነ በድን እንጅ! ነገሩ ሁሉ ሬሳ መበቀል ድረስ የሚሄድ ኢህአዴጋዊ ክፋት ነው፡፡ ከዚህ ሌላ አንድ ምስኪን ነፍሰጡር ሴት የሚጠሉት ሰው ሚስት ስለሆነች ብቻ አስሮ ማንገላታት ምን ይባላል?የዚች ሴት ጉዳይ የዛሬ ሳምንት በጋዜጣ ወጥቶ ስመለከት ቢያንስ የልጅቷን ሮሮ ሰምተው አንድ ነገር ያደርጉ ይሆናል በሚል ነበር ቀናትን የጠበቅኩት፡፡ግን ነገስታት ልባቸው ይራራ ዘንድ ተራ ሰው አይደሉምና በጭካኔያቸው ላይ ተመቻችተው ተኝተዋል፡፡ይህ የሰው የማይመስል ጭካኔ ኢህአዴግ የሚባል ወትሮም አስቀያሚነቱ የሚታየኝ ፓርቲ ምን ቢኳኩሉት የማያምር የአውሬዎች ስብስብ መሆኑን ይናገራል!

3 COMMENTS

 1. ይህ ህሊናን ሰርጾ የሚገባ መልእክት እነዚህ አውሬዎች ዘንድ ደርሶ ወደ ሰውነት ካልለወጣቸው ከጄነራል አሳምነው ሚስት በላይ ለራሴ እና ላገሬ ፈራሁ። ሰዎቹ የጭካኔ ውድድር የያዙ ይመስላል።

 2. ጉልቻ ቢለወጥ ወጥ አያጣፍጥም እንዲሉ የህዝባችን ሃበሳ ዛሬም በእሳት መርመርመጥ ሆኗል። እንካና እንካቹሁ በበዛበት የሃበሻው ምድር ሰው ዘሩና ቋንቋውን ተገን አርጎ መኖሪያ ሲፈልግ ማየት ተስፋ ያስቆርጣል። ከሰሞኑ ቅዳሴና ሌላውም ነገራችን ሁሉ በኦሮምኛ ቋንቋ ይሁን ብሎም ኦሮምኛ የሃገሪቱ ብሄራዊ ቋንቋ ይሁን የሚሉን የፓለቲካ አተሎች ኢትዮጵያዊነትን የጠሉ የሃገራቸውን ፊደል ተጠይፈው በተውሶ የላቲን ፊደል ሰውን ሲያጨናንቁ የኖሩ የሙታን ክምር ናቸው። ትብስን በትባስ እየተካን ሃገራችንን በማፍረክረክ ልክ እንደ መሳፍንቱ ዘመን ይህ ድንበሬና ክልሌ ነው ሌላው ይህን አልፎ መኖርና መስራት አይችልም ሲንል ከጫካ አራዊት ያልተለየን በድኖች መሆናችን አይታየንም።
  በመሰረቱ ግፍ በሃገሪቱ መዝነብ ከጀመረ ቆየ። ችግሩ ያቆማል ስንል ዶፍ እየሆነ መምጣቱ ነው። ምሳሌ ልስጥ … ካነበብኩት (እውነተኛ ታሪክ) …
  ጎንደር አዲስ ዘመን ከተማ 1974 እንደ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር – ሳይታሰብ ጥይት እንደ በረዶ ይዘንባል. በድምጽ ማጉያ የደርግ ካድሬ የሆናችሁ፤ የቀበሌ መሪዎች የወጣት መሪዎች እጃቹሁን በሰላም እንድትሰጡ ትጠየቃላችሁ አለና … ይህ የኢህአሰ ድምጽ ነው ብሎ ጸጥ አለ። የሞተው ሞቶ የተያዘው ተይዞ ከተማዋ ከአራት ሰአት በህዋላ ሰላም ነው ሲባል የደርግ ወታደሮች ከተማ ገቡና ሰውን ሁሉ እያግበሰበሱ ሲያስሩ ከታሰሩት መካከል አንዷ ነፍሰ ጡር ሴት ነበረች። ከከተማው ማዶ የወንዝ ጠርዙን ተከትሎ በተሰራው የአውራጃው ዋና ከተማ እስር ቤት ሁሉም ተወሰዱና ታሰሩ። ብዙም ሳይቆይ ምርመራ ተጀምሮ ሴቷ ምጥ ያዛት እና በድላ ውስጥ እያለች ልጇን ወለደቸው። ይህ ታሪክ ሲፈለግ የሚገኝ፤ በመረጃ የተደገፈ እንጂ ምናዋቢ አይደለም። የሃገራችን መከራ የጀመረው ጥይትና ቡጢን የልዪነታችን መፍቻ ማድረግ ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ ነው። የደርግ፤ የወያኔ እና አሁን ደግሞ የኦሮሞ ዘረኞች በምድራችን ላይ የሚያደርሱት ግፍ ማቆሚያ የሌለው ለመሆኑ ተግባራቸው ያስረዳል። አፍራሽን አፍራሽ እየተካው ከመከራ ወደ ባሰ መከራ የሚሸጋገረው የሃበሻው ህይወት የሚታመሰው እናውቅልሃለን፤ ተምረናል በምንለው በእኛ ነው። የሰው ስብዕናችን በመሟጠጡ በሌላው ላይ የምናደርሰው ግፍ አይሰማንም። ያለ በቂ መረጃ ሰውን ማሰር፤ መግደል፤ ሰርቶ እንደመኖር ሌላውን አሳዶና ቤትና ንብረቱን ዘርፎ መክበር እንደ ባህል የተወሰደባት ሃገር ናት። የጄ/አሳምነው ጉዳይ የፈጠራ ክስ ለመሆኑ ማረጋገጫው መንግስት ምንም መረጃ አለማቅረቡ ነው። በፓለቲካ እይታ ልዪነት በጥይት ተፋልመው ይሆናል። መፈንቅለ መንግስት ነው ብሎ ማሰብ ግን ጅልነት ነው። “በመንደር ውስጥ መፈንቅለ መንግስት አይደረግም”! በዚሁ ሳቢያ የጄ/አሳምነው ባለቤት መታገቷ የሚያመላክተው አንድ ነገር ነው። የአብይ መንግሥትና በዙሪያው የከበቡት የኦሮሞ አክራሪ ጥላቻቸው በአማራ ህዝብና በኢትዮጵያዊነት ላይ መሆኑን ነው። በውጭና በሃገር ቤት የሚኖሩ ኦሮሞዎች የሚጠቀሙበት ቃል “ባለተራና ባለጊዜ” እኛ ነን ነው። ወቸው ጉድ ስልጣን በወረፋ፤ በሌላው ላይ ሰቆቃ ለማድረስ። አታድርስ ነው። ብንጮህ የሚሰማን፤ ብናለቅስ እንባችን የሚያብስና አይዞን የሚል የጠፋበት የዘር ሰካራሞች የሚራወጡባት ሃገር። በእህቶቻችን ላይ በወያኔና ከወያኔው ጆንያ ሳይታሰብ አፈትልኮ በመውጣት ባለጊዜ የሆነው የኦሮሞ የፓለቲካ ስብስብ የሚያደርሰውን ግፍ መግታት ይኖርበታል። እስከመቼ ነው ከአንድ ግፈኛ መንግሥት ወደሌላው ግፈኛ ስንተላለፍ የምንኖረው? አይ ጊዜ… በውቀቱ ስዪም በአንድ ወቅት ከቋጠራት ግጥም ልጥቀስና ይብቃኝ።
  እንደ ጫጩት መንጋ
  በጭልፊት ዋርካ ሥር እንደተበተነ
  አቅማችን ጋሻችን ጩኸት ብቻ ሆነ።

 3. Be ware of Fake democracy in Ethiopia!!
  We were faked to believe change for democracy was coming to this country. That EPRDF/TPLF evil was gone or will go for good. The prime minster was thought as a God-send. That the country will rise to its greatness through unity form the ashes of tribal strife, deprivation, genocide, displacement.
  Now it is clear. The prime minster may be the fake human face of OPDO (on scratch OLF) to beguile unity loving people while the gang working on oromo extremist agenda. The change government looked silently at the cold blooded killing and destruction of properties of non sidama people by mob group called Ejeto in Sidama. They said they will kill and destroy, the fake government heard but sent its troop after destruction and killing. It was complacent at least for short time. Remember the millions of internal discplacments? Oromos opening war on many fronts? Gada spreading all over, irecha coming to addis? the condominium issue, the house destruction, the ID issues….
  Now Birtukan is telling us her office is going to do referendum. Lot other southern zones are asking the same. We are not sure what the implication of this to the whole country let alone southern region. Ja-war, Gabisa, arasa, garba all are out like venomous snake cobra spitting venom out hate and destruction . They have unruly mob called QERO behind them they don’t care about responsibility. Because the dog will bite if they whistle! Wait Ja-war in one hate speech encouraged Ejeto, the Sidama issue will be addressed by FORCE if not by… Following his hate speech that could dis-stabilize the country people died and lost property/their entire life. Wait! the change government has bodyguards to keep him safe from his acts!
  Not even single Ethiopian civil group considered legal action against this mob leader! He seems the de-facto shadow oromia and perhaps leader of oromization of Ethiopia by force.
  So now it is clear EPRDF/TPLF is not dead. TPLF is working to try its chance one more time-to save the constitution and the ethnic Federation one more time!!. All the million cadres are still at work. The cadres are brain washed morons who don’t understand the value of a country except their party agenda. The wine and the containing bag are the same old stuff. The prime minster is generation EPRDF/TPLF. Thought, raised and lived in the principle of ethnic federation. Where is the change we all were emotional about?
  Ok, it was the turn of TPLF and southern to run the machinery; now is Oromo’s turn by EPRDF/TPLF principle. Next should be Amhara/ADP turn to turn wind mill. Hope they do run the mill well when they get their turn! Or is it going to go like that?….
  We were told there was coup in Amhara region?! who is running the court issue for the people languishing in prison there and in addis related to this? ADP? A joke! why should they be keeping a pregnant woman in prison this long with out due process? Or the long hand of OPDO government running the proceedings?
  We needed independent commission to fact check the issue of the so called coup. I don’t think the public will be allowed to know the truth.
  The PM should be judged by his actions but not by his belief or words. Nice words. But I doubt Ethiopians believe they are heading to where they were expecting to head.
  It is a joke and risky to run election in short time in this ethnically fragmented, dis-stabilized country, where ethnic lords/leaders/activists are stronger than the central force. Unless it is respected the TPLF/EPRDF agenda/law
  Real Ethiopians, don’t ever think Ethiopia can not be broken in to chao like Somalia. The attempt for fragmentation of the Orthodox church is actually half way journey in such venture.
  The source of evil Zenawi with then Butros of Egypt, allowed Eritrea go swiftly after all that many Ethiopians died making the country land locked.
  Is there position party in Ethiopia now? No one saying loud anything of national interest? Including the strife of the Orthodox church
  Is Dr Berhanu silenced by the good friend of the prime minster but enemy of Ethiopia, Wodi Isayas or he became aligned with OLF/Gada as some Amhara extremist describe him?
  Amazing time.
  I am doubting we will be able to achieve democracy while the Oromo and Tigre Extremists are out there in force spreading hate and hell bent to achieve ethnic segregation. Perhaps, like Egypt, the nation savior may be a military hero who will rise catch these evils by tail again bring to justice for their actions and lead the country in principle

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.