የመስከረም 4 2012 የኦርቶዶክስ አማኞች ሰልፍ ሊሰረዝ ይችላል ተባለ

የመስከረም 4 ሰላማዊ ሰልፍ መካሄድ አለመካሄዱንም መስከረም 2 በሚኖረው መግለጫ ይረጋገጣል

መስከረም 4 የሚካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመለክተው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት መግለጫ ሰጥተዋል!

መግለጫውን የሰጡት የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በቤተክርስቲያን እየደረሰ ያለውን የመቃጠል፣ የካህናት መገደልና ሌሎች በቤተክርስቲያንቱ ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለማውገዝ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሰልፉን በማስመልከት ዝርዝር መግለጫዎችን በመስከረም 2/2012 ዓ.ም እንደሚሰጥ የገለጹት ኮሚቴዎች፣ የነበራቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ከመንግስት አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሆነና በውይይቱ አጥጋቢ መልስ ካገኙ ሰልፉ ሊቀር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ማህበራቱ የሰላማዊ ሰልፍ መካሄድ አለመካሄዱንም በቀጣይ መስከረም 2 በሚኖረው ድጋሚ መግለጫ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል፡፡በሌላ በኩል ሰልፉ ከኦሮሚያ ክልል ቤተክህነት ምስረታ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ በመጠቆም ከኦሮሚያ ቤተክህነት ምስረታ ጋር በተያያዘ በጉዳዩ ዙሪያ በቅርቡ ሲኖዶሱ የሰጠው መግለጫ በቂ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ሰልፉን ለማዘጋጀት ከባለፈው አንድ ወር ጀምሮ እየተንቀሳቀሱ እንደቆዩም የጠቆሙ ሲሆን፤ የሰልፉ አላማም በሰላማዊ መንገድ በቤተክርስቲያኒቷ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማውገዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የታቀደው ሰልፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሆንና ህዝበ ክርስቲያኑ ከቤተክርስቲያንቷ ጎን እንዲቆሙም ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ: Walta Info

2 COMMENTS

  1. ህዝበ ክርስቲያኑና መላው የለውጡ ሃይል የወያኔን ሴራ የዘነጋ ይመስላል:: የኦሮሚያ ቤተክህነትን መጀመሪያ የደገፈ ከአለቃው መለስ ዜናዊ ጋር የተቀሰፈው ታጋይ ጳውሎስ በዲሲ የትግሪኛ ቅድሴ ሆን ብሎ ሲያስጀምር ነበር:: ዛሬ ደግሞ ዲጂታል ወያኔ አሉላ ሰለሞን የጃዋርን ጀሌ በላይን ተከትሎ ከነመሰል የትግራይ ጳጳሳት ጋር ይህን በማራገብ ላይ ሲሆኑ የመስከረም 4 የተቃውሞ ሰልፍ ዋና ተዋናይም እነሱና ጽንፈኛ የአማራ የጎሳ ፖለቲከኞች ናቸው:: ወገኔ እንንቃ ዶ/ር አብይ ተዋህዶም ኢትዮጲያም አትፈርስም ብሎ የትንቅንቅ ስራ በመስራት ላይ ስለሆነ ለሚወጉት ክፉዎች ጩቤ አናቀብል ተባብረን የኢትዮጲያንም የኣርቶዶክስ ተዋህዶንም አንድነት እንመክት::

  2. ሊደገፍ የሚገባው ሃሳብ፡፡ ህዝብ ንቃ!!!

    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.