አቤል ኤፍሬም በደረሠበት ድብደባ ኩላሊቱ ተጎድቶ ምንሊክ ሆስፒታል ገብቷል፡፡

በትላንትናው እለት በገዢው ፓርቲ የደህንነት ሀይሎች ተይዞ ወደማዕከላዊ ተወስዶ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲው አቤል ኤፍሬም ማዕከላዊ በሚገኙ የገዢው ፓርቲ ደህንነቶች ከትላንት ከቀኑ 5 ሠዓት ጀምሮ እስከ እኩለሌሊት በተፈፀመበት ከፍተኛ ድብደባ ኩላሊቱ በመጎዳቱ ዛሬ ጠዋት 11 ሠዓት ላይ ወደምንሊክ ሆስፒታል እንደተወሰደ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አቤል ከመያዙ ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በማስተማር ላይ የሚገኙ 13 መምህራን በፖሊስ ተይዘው በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን አቤል ማዕከላዊ በገባበት ቀንም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኙ መምህራንን በህቡዕ እንደምታደራጅ ደርሰንበታል የተባለ ሲሆን አቤል ስለጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የገለፀ ሲሆን ብሔሩን ሲጠየቅ ብሔሬ ኢትዮጵያዊ ነው ማለቱ ያናደዳቸው የደህንነት ሀይሎች መታወቂያውን በመቀበል ብሔሩን ለማጣራት ሲሞክሩ ብሔር የሚለው ስፍራ ላይ ምንም ብሄር አለመጠቀሱን ተመልክተው ተያዥ በሚለው ስፍራ ላይ ግን ታማኝ በየነ የሚል ፅሁፍ በማግኘታቸው ለድብደባ እንደተዳረገ ለማወቅ ተችሏል፡፡


ሌሊቱን በሙሉ ያለምግብ እና ውሃ ሲደበድቡት ያደሩት የደህንነት ሀይሎች የአቤልን መድከም ሲረዱ ምንሊክ ሆስፒታል የወሰዱት ሲሆን በስፍራው የነበሩ ሠዎች እንደገለፁልኝ ከሆነ አቤል ሆስፒታል ሲደርስ በድብደባ ብዛት ኩላሊቲ እንዳበጠ እና የለበሰው ልብስ ከጥቅም ውጪ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
‪#‎ኤርሚያስ_አለማየሁ‬

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.