በኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትሩ ሲቪል በመኾኑ በስብሰባው ሱፋቸውን ለብሰው መታደማቸው (ፎቶ መነሳታቸው) አግባብ ነው።

የጄነራል ሳሞራ ፎቶ
የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢትዮጵያ የመከላከያ ባለሥልጣናት ሰሞኑን በአሜሪካ ባደረጉት ስብሰባ ላይ የተወሰደ ፎቶ ነው።
በኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትሩ ሲቪል በመኾኑ እነ ሲራጅ ፈርጌሳ በስብሰባው ሱፋቸውን ለብሰው መታደማቸው (ፎቶ መነሳታቸው) አግባብ ነው። የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹሙ ሳሞራ ዩኑስ እንዲህ ለብሰው የመታየታቸው አግባብነት ግን አልታየኝም። የአሜሪካ የመከላከያ(ወታደራዊ) ባለሥልጣናት በአግባቡ ከነ ማዕረጋቸው ገጭ ባሉበት ሁኔታ፤ ጄነራል ሳሞራ ከታላቅ ወንድሙ ሱፍ ተውሶ የሄደ የልማታዊ አርሶ አደር ሰርግ አጃቢ መስለው መታየታቸው ግር አሰኝቶኝ ነው።
ይባስ ብሎ ሱፉ ሰፍቷቸዋል፣ ረዝሟቸዋልም።መቼም የኃይሌን ተውሰው ሄደው ሊሆን አይችልም። ስጠረጥር ሊሆን የሚችለው እዚያው ዲሲ ሬድዋን ተቃውሞ ከቀመሱባት ሱቅ “ካ’ሁን አሁን ተቃዋሚዎች መጡብኝ” በሚል ሥጋት በደንብ ሳይለኩ በችኮላ ገዝተውት ይሆናል።

Dereje Habtewold

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.