“…የሰፋ ሀገር ይዘን፣ ጠቦ መሞት ይብቃን፤…”   (ገጣሚት፥ ህሊና ደሳለኝ)

አይችለው የለ እንጂ – የልባም ትከሻ፣
ከውርደቱ ደጃፍ – ነውሩን ማምለጥ ሲሻ፣
ገርፎ ማሳመን ነው፣ የፈሪ ሰው በትር፣ የሽንታም ሰው ጋሻ።
እንመን ግድ የለም…
ፍትሕ አይታለምም – ሐቁን እየሸሹ፣
የጠፋው እንዲገኝ፣ እስኪ መጀመርያ፣ ይፈተሽ ፈታሹ፤
አቀርቅራ ታዝግም፣ ትጎናበስ እንጂ፣ መሔድ እስኪያድላት፣
ሰብረህ ስታበቃ፣ ‘ምርኩዝ እንቺ’ ብለህ ደርሰህ አትደልላት፤
‘በኔ ብቻ’ በሽታ – ጥበት እየቀጣን፣
በ’ናታችን ርስት፣ ባባታችን መሬት፣ መደገፊያ እያጣን፤
ቁልቁል እያሰቡ – ምንድነው ከፍታ፣
መብት እየነጠቁ – ምንድነው ግዴታ?
እስከ መቼ ተረት – ግዴለም ይነጋል፣
መንገድ እየቀሙ – ምርኩዝ ምን ያደርጋል?
አንተ እንደሁ ልማድህ አለስልሶ መግደል አሳስቆ መግፋት፣
‘ካብኩ’ እያሉ ‘ማቅለል’ ‘ሳምኩ’ እያሉ ‘መትፋት’፣
የበደል ላይ ጀግና – ሬሳ ላይ መዛት፣
መዋረድን ሽሽት – የአሽቃባጭ አፍ መግዛት፤
እየሸሹ ትግል – እየሮጡ ዛቻ፣
በጉንዳን ልቡና – የነብር ዘመቻ፤
የበላ እያሠረ – የቀማ ቢገፈው፣
የሳተ እያረመ – ያጠፋ ቢገርፈው፤
ጀግና ልማዱ ነው፣ ባርያ ሆኖ ታሽቶ፣ ንጉሥ ኾኖ መግዛት፣
እያነሰ ገዝፎ – እየሞተ መብዛት፤
ያ ሽንታም ላመሉ – በሬሳ ይፎክራል፣
ከፈሪ ገዳይ ‘ድል’ – የጀግና ‘ሞት’ ያምራል፤
ይልቅ……
በእኔ ልቅደም ትርክት- የዘር ደዌ አያጥቃን፣
ከጎጥ ቀንበር ፍቱን – ጠቦ መሞት በቃን፤
የጸደይ ወይን ኾኖ – የሐቅ እንባ ቢጥም፣
በድሎ መጀገን – ጀብድ ሆኖ ቢረግጥም፣
የትግላችን ልኩ – ያሳር ደም ቢያስምጥም፣
በሰፋ ሀገር ጠበን – ኢትዮጵያን አንሰጥም!

3 COMMENTS

  1. This ignorant lady tries to sell herself as an enlightened person.

    She is an instrument of the Debtera Daniel Kibret. Finfinne will be cleaned from such filthy minded individuals.

  2. ተንጫንጩ መንጋዎቹ። መልስ ስድብ በእንግሊዝኛ ባባታቸው ቋንቋ አለቀ ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.