ጠ/ሚ አብይ ከጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ጋር ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ – መስከረም አበራ

ጠ/ሚ አብይ ከጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ጋር ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ አዳመጥኩት፡፡ግሩም ነበር!ጋዜጠኛዋ ወ/ሮ መዓዛ ብሩ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች እንደተለመደው በሳል እና ሰፋ አድርጎ ለመናገር የሚመቹ እና የሚጋብዙ ነበሩ፡፡ከጠ/ሚው ተፈጥሮ የምወድላቸው ለህዝብ ቀረብ የማለት ሰዋዊነት ለጠያቂ ጋዜጠኛም ምቾት መስጠቱ አይቀርም፡፡”መደብ ላይ እየተኛሁ፣ኩራዝ የሚበራበት ቤት ውስጥ ያደግኩ ነኝ” ሲሉ አድማጭ ከእኛ እንደ አንዱ እንጅ ከሰማይ ዱብ ብለው ዙፋን ላይ ያረፉ አለመሆናውን ይረዳል፤ይህ አይነቱ ሰው ሰው የሚል ነገር ከመሪ አንደበት ሲወጣ አንዳች ህዝብን እና መሪን የሚያቀራርብ መስህብ አለው፡፡የቀድሞው ጠ/ሚ ከሰው ይልቅ ለእግዜር የመቅረብ ሁኔታ ከእለታት አንድ ቀን ለጥያቄ ፊታቸው የሚኮለኮሉ ጋዜጠኞችን እጅ ሲያንቀጠቅጥ፣ቃላትን ሲሰባብር፣ትንፋሽ ሲቆራርጥ ተመልክቼ አውቃለሁና ጠ/ሚ አብይ ከጋዜጠኛ ጋር ሲገናኙ የሚያሳዩት ሰዋዊ ትህትና ከትልቅነት የምመዘግብላቸው ማንነታቸው ነው፡፡

ከሸገር ጋር በነበራቸው ረዘም ያለ ቆይታ ካነሷቸው ሃሳቦች የመደመር ፍልስፍናቸውን በተመለከተ ያቀረቡት ሃተታ በዚሁ ፍልስፍና ዙሪያ የነበረኝን ግርታ በመጠኑ ያቃለለ ነው፡፡ መደመር የሚለው አመት ሙሉ ሾላ በድፍን ሆኖ የኖረ ነገር መፍታታቱ ደግ ነው፡፡ በፍልስፍናው ዙሪያ ይታተማል ያሉትን መፅሃፍ ለማንበብም ጉጉ ነኝ፡፡ በመደመር ፍልስፍናቸው ውስጥ ትብብር እና ውድድርን እንዴት አብሮ ማስኬድ እንደሚቻል በአዞው እና በወፏ መስለው ያነሱትን ጭብጥ የበለጠ ወድጄዋለሁ፡፡የተጠናወተን በሁሉነገር በብሄረሰባችን አንፃር የመወዳደር አባዜ በቀላሉ ይለቀናል ብየ ለመገመት ቢቸግረኝም ይህ ፍልስፍና ሲብራራ፣መፅሃፍ ሆኖ ሲመጣ የሚያቀለው ችግር ቀላል አይሆንም፡፡ ከሁሉም በላይ ከባህር ማዶ ፍልስፍና “shop” ለማድረግ ዘምቢል ይዘን ከምንባዝን እንደ ሁኔታችን፣በችግራችን ልክ እና ተፈጥሮ በተሰፋ ሃገር በቀል ፍልስፍና ደግሞ ከፖለቲካችን ደዌ የምንፈወስ ከሆነ መሞከሩ አይከፋም፡፡

የሃገሪቱ ጠ/ሚ በመሆናቸው ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚሰሩ፣ኦሮሞም ለብቻው በተለየ ሁኔታ እንዳይጎዳ እንደታገሉ፣በተለየ ሁኔታ እንዲጠቀምም እንደማይሰሩ የተናገሩት ንግግር ለጆሮ ቢጥምም በተግባር ከሚታየው ጋር ግን አይገጥምም፡፡ ሊቀመንበር ሆነው የሚመሩት ፓርቲ በአዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅም ይገባኛል፤ልዩ ጥቅሜ ደግሞ አዲስ አበባን ፊንፊኔ ብሎ የኦሮሞ ግዛት ማድረግ ነው ሲል ልዩ ጥቅም ከማለት አልፎ ጠቅልሎ የመውሰድ ትግል እንደሚያደርግ መግለጫ አውጥቶ በታከለ ዑማ በኩል ከሚያደርገው ርብርብ ጋር አይገጥምም፡፡እንደ እኔ ላለ ቃል ከተግባር ጋር ማመሳከር ለሚወድ ዜጋ ይህች ንግግር መኮስኮሷ አይቀሬ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ከአብይ አለፍ ብሎ ኦህዴድ ላይ ትኩረት ማድረጉ ደግ እንደሆነ አውቃለሁና ጠ/ሚውን በግል ልከሳቸው አልሻም፡፡ ለምን ቢባል ኦህዴድ ውስጥ ያለው የኦነግ መንፈስ፣በአጠቃላይ በኦሮሞ ብሄርተኛው ጎራ ያለው የማይጠረቃ የኬኛ ጥያቄ፣የኦህዴድም ከዚህ የማይጠረቃ ጥያቄ አለመዋጀት ጠ/ሚው የሚፈልጉትን ብቻ ሳይሆን የማይፈልጉትን የመናገር የመስራት ውድድር ውስጥ እንደሚከታቸው አላጣውም፡፡ ዋናው ለጥያቄ ግን አስከመቼ እንዲህ ሆነው ይዘልቁታል የሚለው ነው!
ጠ/ሚው ሃገራቸውን የሚወዱበትን ውድ የገለፁበት መንገድ ልቤን ነክቶታል፡፡ኢትዮጵያን በጣም ከሚወዱ ዜጎች አንዱ እንደሆኑ ገልፀው ስለ ኢትዮጵያ ሲሆን እንደሌላ ጊዜ ጠንከር ብሎ መቆም እስኪቸግራቸው ድረስ ስለኢትዮጵያ ሲሆን ስስ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡ እንዲህ ሲሉ እኔን እኔን መስለውኝ ነው መሰለኝ ምን እያሉ እንደሆነ በደንብ ተረድቻለሁ! እንዲህ የሚል ጠ/ሚ በማኘታችንም ደስተኛ ነኝ፡፡ ይህን ያሉት አብይ ነገ ሌላ ጥፋት ሊያጠፉ ይችላሉ ግን ከዚህ ኢትዮጵያን ከመውደዳቸው ከፍታ እስካልወረዱ ድረስ ከነቃርሚያው ተስፋ እንዳደርግ ያደርጉኛል፡፡

ባለቤታቸውን ከእናታቸው ጋር እያናፀሩ የገለፁበት መንገድ፣በተለይ ቀዳማዊት እመቤቷ በመጠን መኖርን የሚውቁ ቀጥብ ግን ደግሞ ሃይለኛ ሴት መሆናቸውን የገለፁበት መንገድ ወ/ሮ ዝናሽ “Shopping” ከሚያበዙ የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች ወገን አለመሆናቸውን ያሳያል፤ይህም መልካም ነው! ሃይለኝነቱም አይጠላም፤ሴት ሃይለኛ ካልሆነች ይህን የወንድ አለም እንዴት ትዘልቀዋለች?😀 በስተመጨረሻም ጠ/ሚው ለጥበብ ቀረብ ያለች ነፍስ እንዳለቻቸው ግጥም አብዝተው እንደሚወዱ የሚያደንቋቸውን ገጣሚያንን በመዘርዘር ተናግረዋል፡፡ ጥበብን መውደድ ሃገርን የመረዳት መንገድ ነው-በጥበብ በር ገብቶ የማይፈተሸ የህይወት ገፅ የለምና!

4 COMMENTS

 1. Lady,

  Your objective is not dealing with the interview, but it is about disowning the Oromo people its own capital city Finfinne. The Oromo people are not calming Bahir Dar, Mekele or Awasa. The Oromo reclaim only their own city in which they become alien since the Menlik era. The Oromo living in Awasa will never deny the ownership of the Sidama people concerning the Awasa city.

  Whether  you like it or not, the owner of Finfinne is the great Oromo nation. The social, economic and political right’s of its residents will be fully respected. The thesis of greedy  politicians cannot change historical facts. One of the hard dying Anti-Oromo individuals are the so called Eskinder Nega,  Ermias Legesse (the chameleon) and the ignorant Reyot Alemu. They  are toxic and hatemongers. 

  Finfinne is not an island and cannot stand by itself. It depends in all aspects on Oromia. Mind you: Without Oromia no Finfinne! Without the whole Oromia including Finfinne there will be no Ethiopia. Thus, it is your choice to live with this great nation in peace or to face unnecessary confrontation. Your noises can not change the truth of ownership and natural rights of the Oromo nation.

  You are new comers to the region. Read the following short piece: According to Dr. Eduard Glaser, a renowned Austrian epigraphist and historian, Habeshas were originally from Southeastern Yemen who lived east of the Hadhramaut kingdom in the modern district of Mahra. He believed the etymology of Habesha must have derived from the Mahri language which means “gatherers” (as in gatherers of incense). He asserted that the Mahrites and their language should be regarded as the descendants of the people and speech of ancient Habeshas.

  The demands of the Oromo people are the ownership of the city itself and the development of afaan Oromoo and Oromo culture in the city. Of course the basic human rights and all social, cultural and economic rights of the residents of the Finfinne city will be respected at the individual and group levels fully. Beyond that the self rule of the city will be respected. But it should not contradict itself with the interests of the Oromo nation. The main problem is not about the rights of the residents in Finfinne but about Oromo phobia. Some stone minded individuals hate the Oromo people ever day.

  Ethiopia cannot go back to the old era. Nobody can impose it’s hagemoy more in Oromia. The integrity of Oromia including Finfinnee will be untouchable. The Oromo nation has been fighting injustice and subjugation in it’s homeland, Oromia in order to regain it’s human dignity as one of the great nations of East Africa.You can keep crying and insulting. But it will not bring back the inhuman eras of the rotten and eradicated systems. They have gone for good and will not came back again.

 2. This guy keeps talking any talk for his own imagined satisfaction , not a talk based on the very tough reality on the ground .
  He is a very articulated but unfortunately voracious and unsubstantiated way.
  He knows very well the very poor psychology of not only the people but also very sadly the educated section of the general population.
  Try to carefully observe how the very uncontrolled excitement of the interviewer, Meaza Biru sounds so shallow and infantile . She sounds totally lost with the very “fascinating “ story telling ability of the PM to the extent of losing her focused and substantive question about so many horrible things that have characterized the last more than one year of the the so-called democratic reform by the same if not much worse ruling front led by OPD of the PM’ s party.
  I hate to say but I have to say that we must be extremely worried about how the country can move forward with all these kinds of very infantile and hypocritical way of thinking .

  Did you listen very carefully when the PM tried to convince the people and disgustinglyeconomists that the country will be at the level of developed countries and the very long time of the culture of poverty will be history within a dozen of years ? I do not know if there is any disingenuous and highly misleading political personality than this type .

 3. መስከረም አበራ በፅሁፍሽ ውስጥ ሀቀኝነትና ሚዛናዊነት ግልፅ ብሎ ይታያል:: እንዳንቺ ያለ ፀሀፊ ተቃውሞ ስታቀርቢ ተአማኒነትና ክብር ይኖርሻል:: ቃለመጠይቁን ሰምቼአለሁ ያቀረብሽ ፅሁፍ እውነተኛና አሳማኝ ነው

 4. ታርሞ የተለጠፈ
  ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ
  “ከጠ/ሚው ተፈጥሮ የምወድላቸው ለህዝብ ቀረብ የማለት ሰዋዊነት” ብለሻል

  ወ/ሮ መሰረት ይህ ፋሺሰት ድርጅቶች ሁሉ ሊቀመንበር የሆነ መሪ “እስር ቤት ውስጥ በሐዘን ላይ ያለችውን ነብሰጡር የሚያሰቃይ ጨካኝ ሰው “መደብ ላይ እየተኛሁ፣ኩራዝ የሚበራበት ቤት ውስጥ ያደግኩ ነኝ” ስላለ አንቺ ለህዝብ ቀረብ ያለ ሰዋዊነት” ብለሽ እንዴት እንዲህ ያለ ትልቅ ሽልማት ለማሞገስ በቃሽ? ያውም ከወራት በፊት ነብሰጡር የሚያሰቃይ ጨካኝ እያልሽ የከሰስሺውን ሰው በሚደሰኩሮው አጭበርባሪ ቃላት እና ቃለ መጠይቅ እንዴት ተሎ ተሸወደሽ “ሰዋዊ” አልሽው?!!!

  እንዲህም ብለሻል፦
  “ለጠያቂ ጋዜጠኛም ምቾት መስጠቱ አይቀርም፡፡”መደብ ላይ እየተኛሁ፣ኩራዝ የሚበራበት ቤት ውስጥ ያደግኩ ነኝ” ሲሉ አድማጭ ከእኛ እንደ አንዱ እንጅ ከሰማይ ዱብ ብለው ዙፋን ላይ ያረፉ አለመሆናውን ይረዳል፤ይህ አይነቱ ሰው ሰው የሚል ነገር ከመሪ አንደበት ሲወጣ አንዳች ህዝብን እና መሪን የሚያቀራርብ መስህብ አለው፡፡”
  አይ ወ/ሮ መሰረት! ኢትዮጵያውያን እንኳን ”መደብ ላይ እየተኛሁ፣ኩራዝ የሚበራበት ቤት ውስጥ ያደግኩ ነኝ” የሚል “መስህብ” (የምትይው) ቀርቶ “ኢትዮጵያ” የሚል ቃል “እግዚአብሔር” የሚል ቃል የሚናገር ሁሉ እግሩ ላይ የሚነጠፍ ተላላ ሕዝብ መሆኑን እንዴት አጥተሺው ነው አሁን ይህንን ማጭበርበሪያ ቃላት እንደ ቁም ነገር ቆጥረሽ ሕዝብ እና መሪ ያሚያቀራርብ መስሕብ ብለሽ ገለጽሺው? ወያኔዎች ከገበሬው ጋር ምን መስለው ይኖሩ አንደነበር እነ መለስ ዜና ሲገልጹት የነበረውን የጫካ አኗኗር ከአብይ የመደብ እና የኩራዝ ኑሮ ለኢትዮጵያውያን የመስህቡ ልዩነት ጨዋታ ምን ልዩነት አለው ብለሽ ነው? ነገሩ ያለው ስራ ላይ የሚታየው እንጂ ለምሳሌ “መደብ ላይ እየተኙ” ጅማ ላይ ያደጉት ኮለኔል መንግሥቱስ አለሉሽ አይደል? ራሳቸው የገለጹትን አታስታውሺም? ግን ያ መደብ ሥራ ላይ ሲተረጎም ምን አስከተለ?

  ቀጥለሺም፦
  “በዚህ ረገድ ከአብይ አለፍ ብሎ ኦህዴድ ላይ ትኩረት ማድረጉ ደግ እንደሆነ አውቃለሁና ጠ/ሚውን በግል ልከሳቸው አልሻም፡፡”

  ይህ ሰው ኦሕዴድ የተባለ የኣማራን ሕዝብ ዘር በማጥፋት ተጠያቂ የሆነን ድርጅት መሪ ከሆነ መሪው ድርጅቱን ካልተቆጣጠረ ኦሕዴድ በራሱ የሚዋልል መልሕቅ የሌለው “ፋሉል” (አናርኪ/ሥርዓተ አልባ) ድርጅት ነውና ትኩረት የሚደረገው በመሪው እንጂ በጭፍረቹ ላይ ማትኮር በምን ዘዴ ነው የምትለውጪው። ለነገሩ የሚከተለው ርዕዮት እንጂ ጭፍሮቹ ከኪሳቸው ያወጡት አሰራር አይደልም። ድርጅቱ ፋሺሰት ነው እና ፋሺዝምነ ለመለወጥ መታገል ብትይ ይሻላል። ያም ካልሆነ ትኩረቱ ደግሞ በመሪው ላይ ነው መደረግ ያለበት።
  የሚገርመው ደግሞ ያ የአንዳርጋቸው ጽጌን የማቆጳጰሲሽን ባህሪሽን በአብይ ላይ ተመልሶ ሲመጣብሽ አንዲህ ብለሻል

  “እንዲህ የሚል ጠ/ሚ በማግኘታችንም ደስተኛ ነኝ።”

  አንቺ ሁሉም ያስድስትሻል። አንዳርጋቸውም ያስደስትሻል። ስትገለባበጪ መክረምሽ ነው። እባክሽ አንዳርጋቸውን የሚያክል አደገኛ ጸረ አማራ፤ ባንዳ “ዋሾ!!!!”የሆነውን ሰው አትካቢብን ብለን ስንጮህ አንዲት ካንቺ የባሰች “እየሩሳሌም” የተባለች ወጣት አንዳርጋቸው ጫማ ስር እየተደፋች ስታስቸግር የነበረች ሴት ጋር አብራችሁ አንዳርጋቸውን ስታቆለጳፕሱት ከርመሽ አሁን ያንን መስመርሺን ትንሽ ወጣ ብለሽ አብይን የመሰለ ስርዓተ አልባው፤ጨካኝ፤ አታላይና “ትልቁ ዋሾ” (ይግራኝ አሕመድ ታናሽ) ስትቀወሚው ደስ ብሎን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ባጭበርባሪ ቃላት አብይ ደለለሽ እና ፋሺሰታዊነቱን ሰርዘሽ “ሰዋዊነቱን” መቀበል ጀመርሽ። ጸሐፊዎች ምን ብናደርጋችሁ ይሻላችሁ ይሆን?

  “ከዚህ ኢትዮጵያን ከመውደዳቸው ከፍታ እስካልወረዱ ድረስ ከነቃርሚያው ተስፋ እንዳደርግ ያደርጉኛል፡፡”
  ይህ እማ ያንቺ የተለየ ባሕሪ አይደለም ኢትዮጵያውያን የምንጠቃበት አስቸጋሪ ባሕሪ ነው። ለዚህም ማስረጃ ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለ ማርያም ያሉትን ላንቺ የሚስማማ ንግግር ላቸው። እንዲህ ይላሉ “”የኢትዮጵያ ዕድልዋ መቸም ይኸው ነው፡ መታለል እና በከንቱ ማለቅ።” አንቺም የዚህ ሰለባ ነሽ። እባካችሁ በቃላት እየተሰዋደችሁ ሕዝቡንም የባሰ ግራ አታጋቡት።
  አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.