የቦይንግ የገንዘብ ድጋፍ ፈንድ ለላየን ኤር በረራ 610 እና ኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 302 አደጋ

የቦይንግ የገንዘብ ድጋፍ ፈንድ ስራውን የሚጀምረው መስከረም 24 ነው፡፡

(ችካጎ- መስከረም 23/2019) ሁለቱ የቦይንግ ገንዘብ ድጋፍ ፈንድና ሀላፊዎች ኬኔት አር. ፋይንበርግና ካሚሊ ኤስ. ቢሮስ እንዳስታወቁት በላየር ኤር በረራ 610 እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 302 ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦች በአስቸኳይ $50 ሚሊየን ዶላር እንዲሰጥ ወስነዋል – ይህም ከመስከረም 24 ጀምሮ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

የቦይንግ ኩባንያ ሊቀመንበር፣ ፕሬዝዳንትና ከፍተኛ ስራ አስፈጻሚ ዴኒስ ሙሊንበርግ እንዳሉት “በቅርቡ በቦይንግ 737 ማክስ ላይ የደረሰው አሰቃቂ ክስተት በቦይንግ ያለነውን ሁሉ ያሳዘነና ለተሳፋሪ ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙላ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን፡፡” “የዚህ ፈንድ መከፈትም ተጎጂ ቤተሰቦችን ለመርዳት የምናደርገው ዋና እርምጃ ነው፡፡ ይህንን ጥረት በመምራት ኬን ፌይንበርግ እና ካሚሊ ቢሮስ ላበረከቱት የላቀ ተግባር እናመሰግናለን፡፡”

የቦይንግ የገንዘብ ድጋፍ ፈንዱ 50 ሚሊየን ዶላር ከ 100 ሚሊየን ዶላሩ ላይ የሚነሳ ሆኖ ይህም ቦይንግ በዚ አሰቃቂ አደጋ ተጎጂ ለሆኑ ቤተሰቦችና ማህበረሰብ ፍላጎቶች የሚያውለው ነው፡፡ ተጨማሪው የ 50 ሚሊየንድ ዶላር ፈንድ ለማህበረሰቡ ትምህርትና ኢኮኖሚ ማሳደግ የሚውል ይሆናል፡፡ ቦይንግ እነዚህን የተለያዩ ፍላጎቶች ለማሟላት ከአካባቢያዊ መንግስታዊና ለትርፍ ካልተቋቋሙ ድርጅቶች ጋር በጋራ ይሰራል፡፡

ከዚህ የመጀመሪያ ድጋፍ በተጨማሪ፣ የቦይንግ ሠራተኞችና ጡረተኞች በበጎ ፈቃደኝነት መዋጮ ለማድረግ የሚያስችላቸው አንድ የቦይንግ ድጋፍ ፈንድ የበጎ አድራጎት ፈንድ ለማቋቋም ከዓለም-አቀፍ ተፅእኖ (ግሎባል ኢምፓክት) ጋር በመተባበር ይሰራል፡፡ እስካሁን ጉዳት ለደረሰባቸው ማህበረሰቦች ከ 750,000 ዶላር በላይ ወጪ አድርጓል፡፡

የሰራተኞችና ጡረታ ወጪዎች ልገሳ ተቀባይነት አግኝቷል – እንዲሁም ቦይንግ በተዋጣው ልክ አስተዋጽኦ ያደርጋል – እስከ 2019 መጨረሻ ድረስ ለተጎጂ ማህበረሰቦች ውስጥ ዘላቂ ለውጥ የሚፈጥሩ ታዋቂ፣ የተረጋገጠ፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ድጋፍን ይደረጋል፡፡ በተለይም ፈንዱ በትምህርት እና በኢኮኖሚ ማጎልበት ላይ ያተኮሩ ፕሮግራሞችን ይደግፋል፡፡ ሁሉም የተቀባዮች ድርጅቶች በግሎባል ኢምፓክት እና በቦይንግ የሚመራ አጠቃላይ የፍትህ ትጋት አካሄድ ተለይተው ይታወቃሉ፡፡

በቦይንግ የገንዘብ ድጋፍ ፈንድ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች መቅረብ ያለበቸው ለፊንበርግ የሕግ ቢሮ፣ ተቀበቀይ ኤሚ ሪስ Amy@weisspublicaffairs.com  ወይም በ 202-203-0448 ላይ ነው፡፡ የበተለጠ መረጃ በሚከተለው ድረገጽ ላይ ይገኛል፡ BoeingFinancialAssistanceFund.com፡፡

ስለ ቦይንግ ኩባንያ

ቦይን በአለማቀፍ ደረጃ ትልቅ የኤሮስፔስ ኩባንያ ሲሆን ግንባር ቀደም የጀቶችና የመከላከያ እንዲሁም የስፔስና የደህንነት ሲስተም አምራች ነው፡፡ እንደ ከፍተኛ የዩ.ኤስ ላኪ፣ ኩባንያው በ 150 ሀገራት ላሉ አየር መንገዶችና ለዩ.ኤስ እንዲሁም ወዳጅ ሀገራት ድጋፍ ያደርጋል፡፡ የቦይንግ ምርቶችና በስፋት የሚቀርቡ አገልግሎቶቹ የንግድና ወታደራዊ አውሮፕላኖች፣ ሳተላይቶች፣ መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክና መከላከያ ሲስተሞች፣ የማስወንጨፊያ ሲስተሞች፣ የላቀ መረጃና የመገናኛ ሲስተሞች፣ እንዲሁም ብቃትን መሰረት ያደረገ ሎጀስቲክና ስልጠናን ይሰጣል፡፡

www.boeing.com

ሚዲያ ማግኛ:
ሜሮፋ ኮሚኒኬሽን
ሼሊ ስታማቲአዲስ፡ shellys@meropa.co.za
ዊሊያም ስሞክ፡ williams@meropa.co.za

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.