ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዛሬ በተካሄደው የበርሊን ማራቶን በሁለቱም ፆታ ድል ቀናቸው

ወንዶቹ አትሌቶች ከ1 እስከ 3 ተከታትለው ሲገቡ ሴቶቹ ደግሞ 1ኛ እና 2ኛ ወጥተዋል። ማራቶኑን በወንዶች፣ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፤ በሴቶች ደግሞ አሸቴ በከሬ አሸንፈዋል።

በወንዶቹ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ2:01:41 1ኛ ሆኖ በመግባት በማራቶን ታሪክ ሁለተኛውን ምርጥ ሰዓት አስመዝግቧል። የማራቶኑን ሪከርድ ለመስበርም 2 ሰከንድ ብቻ ወደ ኋላ ቀርቷል።

አትሌት ብርሃኑ ለገሰ በ2:02:48 ቀነኒሳን ተከትሎ ሲገባ፣ አትሌት ሲሳይ ለማ ደግሞ በ2:03:36 3ኛ ሆኖ ጨርሷል።

በሴቶች አትሌት አሸቴ በከሬ 2:20:14 በመግባት ማራቶኑን ስታሸንፍ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ማሬ ዲባባ ደግሞ በ2:20:22 2ኛ ወጥታለች።

በዮናስ በድሉ/EBC

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.