አቶ ተመስገን ጥሩነህ አሁንም የክልሉን የኢኮኖሚ ችግር መፍታት ላይ ነው ትኩረቴ እያሉ ነው? – ማርቆስ አግማስ

አቶተመስገን ጥሩነህ አሁንም የክልሉን የኢኮኖሚ ችግር መፍታት ላይ ነው ትኩረቴ እያሉ ነው? ድልድይ ስራሁ ብለው አጣዬ በህዝብ ላይ የሚተኩሱትን ኦነጎች ወደ መሀል እንዳያሻግሯቸው ፈራሁ። ይህ ህዝብ ጥይት ከሚርከፈከፍበት ወንዙን በዋና ቢሻገር ይሻለዋል።

ክቡር ፕሬዝደንት ወታደራዊ አቅም የሌለው ጠንካራ ህዝብ በአለም ላይ ማንን ያውቁ ይሆን? ኧረ እንዲያውም የሀያላን ሀገሮች የኢኮኖሚ መነሻ ጠንካራ ወታደራዊ ተቋማት መሆኑንስ ሰምተው ይሆን። ወያኔ እንኳን ይሄንን ስለተረዳች የኢኮኖሚው ሞተር ወታደራዊው ሜቴክ እንዲሆን ሞክራ ነበር። ሌብነት ሀሳቧን ህልም አደረገባት እንጂ!

ደህንነትን የማያስቀድም ህዝብ ሽ ህንፃ ቢገነባ ፣ ሽ ፋብሪካ ቢደረድር ነገ በጦርነት ይፈራርሳል። ሴሪያን ያዬ በወታደራዊ የበላይነት አይተዳደርም። ለነገሩ እንዲያው ድከም ቢለኝ እንጂ ዶ/ር አብይ ሲሾምዎት አዴፓን በጦረኝነት ገምግመነዋል የሚል ማደንዘዣ እንደወጋዎት መቼ እረሳሁት። ለማንኛውም ድንገት የሰሞኑ ከበባ አስደንግጦዎት ከሆነ አሁን ውድድሩ የፖለቲካ እንጂ የኢኮኖሚ አይደለምና ህዝቡን እንዳያስበሉት። ለሂሳብ ፈተና ጆኦግራፊ አይጠናም።

ማርቆስ አግማስ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.