የባህርዳር ወጣቶች ላይ የአስለቃሽ ጭስና ድብደባ እንደደረሰባቸው ተገለፀ

የእነ ብርጋዲዬር ጀኔራል ተፈራ ማሞ  የክስ መዝገብ ችሎት ለመከታተል የአቀኑት የአካባቢው ወጣቶች ላይ የአስለቃሽ ጭስና ድብደባ እንደደረሰባቸው ተገለፀ።

አማራ ሚድያ ማዕከል /አሚማ
መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

ዛሬ ባህርዳር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት እነ ብ/ር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጨምሮ 76 ሰዎች እንዲሁም በእነ ስንታየሁ ታከለ መዝገቡ 9 ሰዎችን ጨምሮ በባህርዳር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀጠሮ ችሎት ለመከታተል የባህርዳር ከተማ ነዋሪ ወደ አደባባይ የወጣ ሲሆን ከጣና ሀይቅ ትምህርት ቤት ፣ ከፓሊስ ኮሚሽን እስከ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መንገድ ተዘግቶ ነበር ።

የባህርዳር ወጣትም የህሊና እስረኞ የሆኑት መሪዎቻችን ይፈቱልን አሁን ላይ ያስፈልጉናል እያሉ ድምፅ ሲያሰሙ መቆየታቸውን ምንጮቻችን ገልፁውልናል ።

ችሎት ለመከታተል ያቀኑት ወጣቶች ይፈቱንል የሚል ድምፅ ለምን አሰሙ በማለት ከልዩ ሀይል ጋር በተፈጠረ አለመግባባት የአስለቃሽ ጭስ እና ድብደባ እንደተፈፀመባቸው የአሚማ ምንጫችን ገልፀዋል።

ጉዳያቸውን ሲመለከት የቆየው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ረፋድ ላይ ባስቻለው ችሎት የመርማሪ ቡድኑ የጠየቀውን የተጨማሪ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ በማድረግ ፣ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስም ክስ እንዲመሠርት ትዕዛዝ እንደሰጠ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.