በትግራይ ህዝቡ የህወሓቶችን ውክልና ማንሳት ጀመረ!

የቦራሰለዋ ወረዳ ህዝብ “በፌደራል ምክር ቤት፣ ክልል ምክር ቤት የነበሩን ወኪሎች (የህወሓት ተመራጮች) እኛን ሳይሆን ህወሓትን ብቻ እያገለገሉ ሰለሆነ  ውክልናችን አንስተናል” ብለው ኣውጀዋል።  ከዚህ በፊትም የእምባ ስነይቲ ወረዳ ህዝብ ውክልናው እንዳነሳ ይታወቃል። የትግራይ ህዝብ ለለውጥ ተነስቷል!!!!

 

4 COMMENTS

  1. ሲጀመር ሕወሐት መች ለትግራ ሕዝብ ቆመና ።የትግራይ ሕዝብም በነበረዉ ስርአት ምንም የተጠቀመዉ ነገር የለም ።ካድሬዉ ብቻ ነዉ አገሪቱ እንደመዥገር ሲመጣት የነበሩት ።የትግራይም ህዝብም እንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ለዉጥ ያስፈልገዋል ።

  2. As a person from the Tigray region,I always regret about the tremendous sacrifices the Tigrayan poor had to pay for the corrupt,self serving and racist politics of the TPLF. After being forced out of power in the center, the same bloody TPLF leaders are holding Tigray as their last remaining base. They are abusing Tigray as their launching pad to incite conflicts and destabilize the neighboring regions and the country. They have been robbing the country and amassed enough wealth to do so. It may take time but these robbers and fascists will be flushed out of Tigray and face justice. They will have to be held accountable for the heinous crimes they committed in Tigray and the other parts of the country.

  3. የትግራይ ህዝብ በነጻነት ስም ልጆቹን ገብሮ ራሱን ለመከራና ለስደት ዳርጎ ትርፍ ያገኘው ልክ በበረሃ እንደነበረው እስራት፤ ግርፋት፤ ስደት፤ መከራና ረሃብ ነው። ይህ እድል ፈንታ ደግሞ የቀረውን የሃገሪቱን ህዝብ ይመስላል። ለ 27 ዓመታት ምድሪቱን በግፍ አገዛዝ ስር ያሰቃይ የነበረው ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንኳን ሌሎቹን አርነት ሊያወጣ ቀርቶ ለራሱ በባርነት ውስጥ የነበረ እና ያለ ድርቡሽ ድርጅት ነው። በእፍኝ በሚሞሉ ጠበንጃ አንጋቾችና ባለስልጣኖች ሃብትና ንበረት ማካበት የትግራይ ህዝብ በሌላው ወገኑ እንዲጠላ ያደረጉት እነዚህ የፓለቲካ ሾተሌዎች ለራሳቸው የክፉ ቀን መጠጊያ ፍለጋ እንጂ ለትግራይ ህዝብ ገዶአቸው አያውቅም። ቀን ይዘገያል እንጂ ሰው ከሰው እያባሉ ለዘላለም ውሽትና እውነትን እየቀየጡ በማታለል መኖር አይቻልም። የወያኔ የንስሃ አባት አቦይ ስብሃት እንደሚሉት “የተጨቆነ ሰው ሞትን አይፈራም”። ጊዜው በወያኔ ላይ እየጨለመ እንደሆነ የታወቀ ነው። ሃገር እየሸጡ፤ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ጠላቶች ጋር እየተሻረኩ መኖርና መስረቅ ማቆሚያው እየተቃረበ ነው። ከሰሞኑ አንድ ነገር አነበብኩ እና ግርም አለኝ። ትግራይ በመሆናቸው ለታሰሩ የትግራይ ልጆች ፊርማ እያሰባሰቡ ነው ይለናል። ሾተላም ፓለቲካ ይሉሃል ይሄ ነው። የት ነበሩ ወያኔ በወንድ ብልት ላይ የውሃ ጠርሙስ ሲያንጠለጥል፤ ጥፍር በፒንሳ ሲነቅል፤ ሴትና ወንዶችን ሲደፍር፤ ሃገር ቆርሶ ሲሰጥ? የት ነበሩ አባት እናት ልጅ በወያኔ ትዕዛዝ ሲገደሉ? የድር አራዊት ይመስል በዘር ዙሪያ መሰብሰብ የሃበሻው ወልጋዳ ፓለቲካ ሆነና ሁሉም በዘሩና በቋንቋው ተሰላፊ ነው። አይ ሃገር! የትግራይ ህዝብ ወያኔን አክ እንትፍ ካለው ቆይቷል። የትግራይ ህዝብ የታፈነ ህዝብ ነው። በወያኔ ካድሬዎች አፉ የተለጎመ። አሰራራቸው እንደ አልባኒያ የኮሚኒስት ፓርቲ ነው። ሁሉ ነገር የታጠረ። ለመኖር መግደል፤ መዝረፍ፤ ማታለል፤ መዋሽት፤ የውሸት ምስከር መሆን ግድ ነው። ወያኔ አሻጥረኛ ድርጅት ነው። በመርዝ ሰው ገድለው ሃዘን ቤት ቁጭ ብለው የሚያስተሳዝኑ ጉዶች ናቸው። ኢያሱ በርሄን ማን ገደለው? ጄ/ር ሃያሎምን ማን ገደለው? የስለላ ክፍል ሃላፊውን ክንፈን ማን አስገደለው? ገዳይን እየገደለ፤ ለተገዳይ ሃውልት እያቆመ ሰውን በማታለል የቆመ ድርጅት ነው። የትግራይ ህዝብ በአንድ በኩል ደርግ ሰፈራ እያለ ሲያዋክበው በሌላ በኩሉ ደግሞ ወያኔ ኑ ለም መሬት አለ በማለት ጎትቶ ሱዳን ውስጥ ያለቁት የትግራይ ልጆች ደም ይጮሃል። የሚያሳዝነው በረሃብ እንደዚያ እየረገፉ ወያኔ ስንዴና አሽዋ ደርድሮ የውጭ የተራድኦ ድርጅቶችን በማታለል እልፍ ዶላር እንደዛቀበት በህይወት ያሉና ይተከፋፈሉት አሁን ትግራይ የትግራይ ህዝብ እያሉ የሚያደነቁሩን ነውረኞች ያውቁታል።
    ዘመድ አዝማዳቸውን፤ ልጆቻቸውን በውጭና በሃገር ውስጥ የናጠጡ ሃብታሞች አድርገው በትግራይ በክረምቱ የድሃ ቤት የሚያፈርሱ አረመኔዎች ናቸው። የትግራይ ህዝብ ሆ ብሎ በመነሳት እነዚህን ዘመን ያለፈበት የጦርነት ገድል ታምቡር እየመቱ ጀግና ነን የሚሉትን ከውስጡ ሊያስወግዳቸው ይገባል። እስቲ ዶ/ር አረጋዊ ብርሄና ጓደኞቻቸው ለቀብር ሄደው መቀሌ ላይ የሆኑትን አዳምጡ። ይህ ለህዝብ የሚገደው ድርጅት ነው? መርዝ በግድ የሚግት? አይ በዘራቸው እሰር ላይ ላሉ የትግራይ ተወላጆች ፊርማ ማሰባሰብ። የተጨማለቀ ፓለቲካ። በዘር ማጥፋት ወንጀል መከሰስ ያለበት ወያኔ ነው። የትግራይን ህዝብ ለደርግ ቦንብ እና ጥይት እያመቻቸው ያስመታው ወያኔ ነው። ለራሱ ፕሮፓጋንዳ ለመጠቀም። ጥቂቶች ዛሬም በህይወት አሉ። ሊመሰክሩ ይችላሉ። ይበልጦቹ ግን ተለይተውናል። ባጭሩ የሃበሻው ፓለቲካ የውስልትና ፓለቲካ ነው። ለሃገርም ሆነ ለህዝብ ጠቅሞ አያውቅም። ዶ/ር አብይ ብቅ ሲሉ እሰየው ያልነውን ያህል አሁን ደግሞ የኦሮሞ ጊዜ ነው እየተባለን ነው። የወረፋ ፓለቲካ፤ በሰው ደም የሚነግድ፤ ለነገ የማያስብ የሆዳሞች እይታ! የትግራይ ህዝብ ከትህነግ ነጻ ለመውጣት ቆርጦ መነሳት አለበት። በፊርማ ብቻ ወያኔ እሺ ብሎ ምድሪቱ የሰላም አየር እንድትተነፍስ አይፈቅድም። ሃገር አቀፍ የሆነ በእውነትና በመረጃ ላይ የተመረኮዘ እንቅስቃሴ አስፈላጊ ነው። ያለዚያ ወያኔም ሆነ የጊዜው ባለስልጣኖች (ኦሮሞ) አማራም ሆነ ደቡቡ እርስ በርሱ ከመናከስ የሚያድነው ነገር ማንም አይኖርም። ችግሩ የእነርሱ መናከስ ለህዝባችን ጦስ እየሆነ እንጂ እርስ በርሳቸው ቢጠዛጠዙና ቢለይላቸው ማለፊያ ነበር። የሰለቸኝ ስብሰባና መግለጫ ነው። አሁን ማን ይሙት ወያኔ እንደገና መሰብሰብ አለበት? ምን ለመፍጠር? ያዘው ጥለፈው ለማለት፡፤ እሳት ጭሮ እሳት ለማቀበል። ለዚህ ሥራ ጌታቸው አሰፋ እና የወያኔ አፈ ቀላጤ ሌላኛው የግብጽ ሰላይ ጌታቸው ረዳ በቂ ናቸው። ትርኪምርኪ ሁሉ!

  4. ወከባውንና አፈናውን መድፈር እንደሚጀምር ቀደም ብለን ተናገርናል፡፡ እንዳልተመቸው መችታጣና!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.