አንድነት ፓርክ ከነገ ጀምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለጎብኚዎች ክፍት ይደረጋል

እስክንድር ፍሬው/VOA
በኢትዮጵያ ታላቁ ቤተመንግሥት የተገነባው አንድነት ፓርክ የኢትዮጵያና የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ከጥቂት ቀናት በኋላም ለሕዝብ ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።

ከሕዝብ ርቆ የቆየው ታላቁ ቤተመንግሥት ለጉብኝት ክፍት መደረጉ፤ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የተጀመረው ለውጥ ተምሳሌት መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ዘርፍ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናግረዋል።

https://www.facebook.com/voaamharic/videos/2533720920026333/

ከዳግማዊ አፄ ምኒሊክ እስከ ዛሬው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያሉት መሪዎች ኢትዮጵያን ከ130 ዓመታት በላይ ለሆነ ጊዜ ያስተዳደሩትም ከዚሁ ቤተ መንግሥት ነው።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.