ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በማሸነፋቸው የጅማ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች የተሰማቸውን ደስታ በሰልፍ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 02፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚ በመሆናቸው የጅማ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች የተሰማቸውን ደስታ በሰልፍ ገለፁ።

ነዋሪዎቹ ዛሬ ጠዋት ከ12 ሰዓት ጀምሮ የተለያዩ የድጋፍ መልክት ያዘሉ ባነሮችን በመያዝ ነው በጅማ ስታዲየም በመገኘት ድጋፋቸውን የገለፁት።

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ መኪዩ መሀመድ ሀገሪቷ ከሁለት አመት በፊት የነበረችበትን ሁኔታ በማስታወስ አሁን የመጣውን ለውጥ ለማሳካት ሁሉም ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሀኪም ሙሉ በበኩላቸው ለዶክተር አብይ የኖቤል የሰላም ሽልማት ሲሰጥ ሰላማችንን እንድንጠብቅ ለኛም ትልቅ ሀላፊነት እንደተሰጠን ልናስብ ይገባል ብለዋል።

በሰልፉ ላይ የተገኙት አቶ ሌንጮ ባቲ በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያመጡትን ስኬት በማንሳት፥ ከዚህ በኋላ መወቃቀስ አቁመን አገራችንን ወደ ፊት ለማራመድ እንነሳ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በሙክታር ጠሃ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.