ጥጋበኛ ከርከሮ የነፍጠኛ ጎጆ ይታከካል: (ሰለሞን ይመኑ)

የአማራ ሀገሩ የት ነው? የህወኃት እና ኦዴፓ ፀረ-አማራ ጥምረት መቸ ጀመረ?
(ነፍጠኛ ለሚሉን ባንዳ፣ጠባብ፣ዘረኛ እንላቸዋለን ሰፍሪ ለሚሉን ደግሞ መጤ እንላቸዋለን)

የህወኃትን ትርክት እየተጋተ ያደገው አቶ ሽመልስ በግልፅ የተናገረው የነፍጠኛ ትርክት በሁሉም የኦሮሞ ጽንፎች ዘንድ እኩል አስተሳሰብ ላይ የሰረፀ ነው። ሽመልስ የተናገረውን ፀረ አማራና ፀረ ኢ/ያ ትርክት በሚዲያ ታግዞ OMN በሚባል የግብፅ እና አብዛኛው የአረብ ሀገራት ድጋፍ የተቋቋመ ጣቢያ ጋዲሳ ራባ ዶሪ በሚል ፕሮግራም በየቀኑ ፀጋዬ አራርሳ፣ ህዝቅኤል ጋቢሳና ጀዋርን ጨምሮ ለአመታት በግልፅ ሲሰብኩ ነበር፡፡ ይህን ፕሮግራም ኦዴፓ ውስጥ ያሉ አብዛኛው ፀረ-አማራና ፀረ-ኢ/ያ የሆኑ ድኩማን በግልፅ ይደግፉታል:: በኢ/ያ  ታሪክ ውስጥ ሀገሪቱን ወደ አንድ እንዳትመጣ ያደረጋት ነገር ቢኖር የኦሮሞ ፖለቲከኞች ፖለቲካን የተረዱበት መንገድ ከፖለቲካ ሳይንስ አስተምህሮ እጅጉን የወጣ መሆኑ ነው፡፡

ለመሆኑ የሽመልስ ቃል አጠቃቀም ገብቶት ነው ወይስ በህወኃት መጠመቁ ነው፡፡ ለመሆኑ ይህ መናገር የተሳነው ሰውየ ዘሎ የነፍጠኛን ጉዳይ መንካቱ ምን ያተርፋል?  ነፍጠኝነት ክብር ነው ነፍጠኝነት የትም ሀገር ነበር ይኖራልም። የኢ /ያ ህዝብ ሁሉ ነፍጠኛ ነው።  አማራም ነፍጠኛ ነው ነፍጠኛ ማለት (ጠመንጃ በአማርኛ ሰዋሰው ስም ነው።ነፍጥ ወይም የጦር መሳሪያ ማለት ነው።ነፍጠኝነትም =ነፍጠኛ መሆን፣ወታደርነት) ሲሆን በእንግሊዝኛውም Musketeer= a person equipped with weapon,gunman,sniper,armed individual,superb shooter, a person carrying weapons,fusilier,shooter. (ነፍጠኛ ማለት የጦር መሣሪያ የታጠቀ ማለት ነው) ከዚህ በተረፈም ይህ ስም በአውሮፓ ምድር የዘመናዊ መሳሪያ ታጣቂዎች ስም ነበር።
A Musketeer(French:mousquetaire) was a type of soldier equipped with a musket. Musketeers were an important part of early modern armies. Particularly in Europe and the West, as they normally comprised the majority of their infantry. The musketeer was a precursor to the rifleman. Muskets were replaced by rifles in most western armies during the mid 1850s.The traditional designation of “musketeer” for an infantry private survived in the imperial German Army until World War l. እንግዲህ እናም ነፍጠኛ የሚለውን ይህን ሃሣብ ወያኔ የአማራን ህዝብ የሚያሸንፍበት እና የህዝቡን ሞራል የሚጎዳበት የታሪክ ቁስል በማጣቱ በተሳሳተ መንገድ ቃላትን በማጉደፍ ሲጠቀምበት የቆየ ቢሆንም ሰሞኑንም አቶ ሽመልስ አዲስ አበባን ሲገልጽ በአማራ ነፍጠኞች እንደተያዘች አዲስ ትርክት ሰማን ለመሆኑ አዲስ አበባ የተቆረቆረችው መቸ ነው? ኦሮሞ ኢሬቻን ማክበር መቸ ነው የተከለከለው የሚለውን እንኳ አለማወቁ በጣም ያሳዝናል፡፡
ስር የሰደደው ጥላቻና የአማራን ህዝብ በተለያዩ ዘርፎች በማዳከም ከፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ የማግለሉን ማኒፌስቶ ወያኔ በግልጽ በማእከላዊ ኮሚቴ ውይይት ተይዞ ግምገማ የሚደረግበትና መጨረሻም ታላቅ የፖለቲካዊ ስኬት መሆኑን በግልጽ ነብሰ በላዎቹ የወያኔ ባለስልጣናት አማራንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን እንዳይነሳ አድርገን ቀብረነዋል ቢሉም ዛሬም ለወይኔ እንቅልፍ ማን እንደነሳው ጠንቅቆ በማወቁ ይህን ማኒፌስቶውን በአክራሪ የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኞች በኩል በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥለውበታል፡፡
ኢትዮጵያ የምትባለውን ሃገር እንደ ሃገር ለመገንባትና ጠብቆ ለማቆየት የአማራው ህዝብ ከሌሎች ኢ/ያውያን ጋር በመሆን ያበረከተው አስተዋጾ ይህ ነው ብሎ ለመዘርዘር በጣም ከባድ ነው፡፡
በቀላሉ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ብርቅየና ድንቅየ የታሪክ ቅርሶች ከመጠበብ ጅምሮ በሃገሪቱ ሉዓላዊነት ላይ የተቃጡ ወረራዎችን ደሙን አፍሥሶ አጥንቱን ከስክሶ ይችን ሃገር ከጠላት ሃይል በመጠበቅ የአሁኗን ዳር ድንበርና ግዛት እንዲኖራት በሁሉም አቅጣጫ ታሪክ የሰራ ህዝብ ነው፡፡
በተለይ ከአጼ ልብነ ድንግል እና አጼ ሚናስ ሞት በሗላ አጼ ሰርጸ ድንግል ያለ እረፍት በኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫ ከአማራውና ከሌላው ህዝብ ጋር እየተዘዋወሩ በግራኝ ጦርነት ምክንያት ከኢትዮጵያ የተለየውን ግዛት በማስመለስ ከፍተኛ ስራ የሰራ ሲሆን በተለይም ምጽዋን በያዘው በቱርኩ ባሻና ከሱ ጋር በተደረበው በባህረ ነጋሽ ይስሃቅ ላይ የተገኘው ድል ምጽዋ ድረስ የነበረውን የኢትዮጵያ ድንበር ለማስጠበቅና እንዲሁም ከዛም በሗላ የመጀመሪያውን የኢጣሊያን ወረራ በ1888 በመመከት ደረጃም አማራው ከሌሎቹ ጋር ሁኖ ከፍተኛ አስተዋጾ አበርክቷል፡፡
በሃገሪቱ ውስጥ የሰፈነውን ህግና ስርአት እንዲሁም ዘመናዊ የአስተዳደር ስርአተ በማስፈን ደረጃም ግንባር ቀደም በመሆን ብዙ የአማራ ልሂቃን በዘመናዊ የመንግስት መዋቅር ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ አድረገዋል፡፡
በአጠቃላይ ኢትዮጵያን የመምራት ሀላፊነት ከ12ኛው ክ\ዘመን ጅምሮ ከአክሱም ወደ ዛጉኤ ከዛም በአጼ ይኩኖ አምላክ ዘመን ወደ አማራው ህዝብ ከተዛወረ በሗላ  ኢትዮጵያን ባጋጠሟት ታላላቅ ወረራዎች ማለትም በውጭ ጠላቶች በተደገፈውና ከውስጥ በተነሳው የግራኝ አህመድ ወረራና እንዲሁም ከኢጣሊያ ሁለት ግዜ በተሰነዘሩበት ወረራዎች ወቅት አማራው በፍታውራሪነት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ከፍተኛ ተጋድሎ ፈጽሞ ግዛቱንም በትንሹ እስከ የመን፣ቀይባህር፣ሶማሊያ፣ጅቡቲ ድረስ እንደነበርም የሚታወቅ ነበር፡፡ ይህን ጉዳይ ወደ ጎን በመተው የዘመኑ ፖለቲከኞች ግን አማራውን ለማጥፋትና የፖለቲካ ማታገያ በማድረግ በጠላትነት ፈርጀው ብዙ የወንጀል ድርጊቶች ፈፅመውበታል፡፡ በህወኃት ሲፈጸም የነበረው ፀረ-አማራ ሴራ ዛሬም በኦሮሞ ፅንፈኞች የበለጠ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ሁለቱም የፖለቲካ ሊህቃን የፖለቲካ እቅዳቸው የተመሰረተው አማራውን እንደ ህዝብ እንዳይቆምና በመሠረታት ሀገር ላይ እንደ ህዝብ እንዳይታይ ብዙ ሴራዎች የተፈፀሙ ሲሆን እነዚህ ድርጊቶችም በዓለምአቀፉም ሆነ በሀገራችን የተቀመጠውን የዘር ማጥፋት የወንጀል ድርጊት ሀሣብ የሚያሟሉ ናቸው፡፡
       በአማራው ላይ የተፈጸሙ የጥፋት ተንኮሎች
ፀረ-አማራ ትርክት.፩
*****************
የኦሮሞ መስፍፍት በ16ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የመጣ ሲሆን ከደቡበ ወደ መሃል ሃገር መስፍፍታቸውም ኢትዮጵያ የደቡብ ምእራብና ምስራቅ ክፍላተ ሀገሮቿን እንድታጣ ተደርጋለች፡፡ በነዚህ ክፍላተ ሀገራት ይኖሩ የነበሩ የሲዳማ አማራዎችም  በጭካኔ የተገደሉ ሲሆን የተረፉት አማራዎችም ቋንቋቸው፣ባህላቸው፣ስማቸውና ታሪካቸው ጠፍቶ በሃይል በኦሮሞ ተተክቷል፡፡አሁን ያለው የኦሮሞ ህዝብ ሰፍሮባቸው የሚገኙት መሬቶች ኦሮሞ ከመምጣቱ በፊት ባዶ መሬት አልነበሩም፡፡አማራ እና ጉራጌ እንዲሁም ሌሎችም የጠፉ የህብረተሰብ ክፍሎች ሰፍረውበት ነበር፡፡ኦሮሞ ከመጣ ግን ሙሉ በሙሉ ተገደሉ ባንልም ነገር ግን በሃይል ተገደው ኦሮሞነትን የተቀበሉ ናቸው፡፡
 ዛሬ ኦሮሞዎች የሰፈሩባቸው ምስራቅ ደቡብና ምእራብ ሽዋ፣ሀረርጌ፣አርሲ፣ባሌ፣ወለጋ፣ኢሉባቡር፣ጅማና አካባቢውም ባዶ መሬት አልነበሩም እንዴውም የአማራው ይዞታዎች የነበሩና በሃይል ወደ ኦሮሞነት የተቀየሩ ሲሆኑ የአማርኛ ቋንቋን እንዳይናገሩ ሙሉ በሙሉ ተገደው የኦሮሞኛ ተናጋሪ የሆኑ አማራዎች ሁነው እያለ በተበድለናል የኦነግ የፖለቲካ ስልታዊ የሃሰት ትርክት (በቅርቡ ሌንጮ ባቲ ይህን እውነታ በሚዲያ ተናግሮታል) መሰረት አማራውንና ሌላውን ጎሳዎች ቋንቋ በማጥፍት ረገድ ከፍተኛ ስራ ከተሰራ በሗላ በወቅቱ የነበሩ መሪዎች ጫና አሳድረውብናል የሚል የተዛባ ትርክት ይዘው አሁን ድረስ አማራው ላይ ድጋሚ ፍጅት እየፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ ይህን የዘር ማጥፋት የወንጀል ድርጊት የፈፀሙ ሰዎችም ዛሬ ላይ በሀገሪቱ ውስጥ ገብተው የነፃነት አየር አግኝተዋል፡፡ ነባሩንና ሀገር መስራቹን የአማራ ህዝብም የኦሮሞ አክራሪዎች መጤ ሲሉ መጥራታቸው አሁን የጀመረ ሳይሆን ከኦነግ የፖለቲካ ትርክትና ህዝቡን የሌላ ሀገር ሰው ስሜት እንዲኖረው በማድረግ ለጥቃት እንዲጋለጡ ማድረግ ሲሆን ይህንም ባለፉት 40 ዓመታት ውጤታማ በሆነ መንገድ ሰርተውበት ነፍሰጡር እናቶች ሳይቀሩ የታረዱበትን ታሪክ ማየት ይቻላል፡፡
በኦሮሞ መስፋፋት ወቅት ከፍተኛ ጉዳት በአማራው ላይ የተፈጸመ ሲሆን ለምሳሌ ያህል ጎማ ሚባለው አካባቢ በጥንት ግዜ የሲዳማ አማራ የሚባሉ ነባር አማራዎች ይኖሩ ነበር፡፡ በኦሮሞ መስፋፋት ወቅትም ሙሉ በሙሉ ተገድለዋል፡፡
የኦሮሞ መስፋፋት በአጠቃላይ በአማራው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረስ ጀምሮ የአማርኛ ቋንቋ እንኳን በነገስታቱ ዘመን የመንግስት ቋንቋ ሲሆን በኦሮሞዎች ወረራና ጥላቻ ምክንያት አማርኛ ተናጋሪዎችን ሲገድሉ ስለነበር በጭራሽ ቋንቋው በአማርኛ ተናጋሪዎች እንኳ ተግባራዊ ሊሆን አልቻለም እንኳንስ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ጋር ይቅርና፡፡ነገር ግን እውነታው ይሄ ሁኖ እያለ በተገላቢጦሽ ያለፉት መንግስታት ቋንቋችን እንዳንጠቀም ከፍተኛ ጫና ተደረገብን በሚል የፈጠራ ትርክት በማስወራት እውነታውን በማዛባት የተዋጣላቸው ሲሆን በምኒልክ ግዜም ቢሆን በኦሮሞ ማንነትና ህልውና ላይ ምንም አይነት የከፋ ግድያ ያልተፈጸመ ቢሆንም ተፈጸመ ቢባል እንኳን የኦሮሞ መስፍፍት በአማራዎች እና በሌሎች አማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ከፈጸሙት ፍጅት ጋር የሚወዳደር አይደለም፡፡ምክንያቱም በአጼ ምኒሊክ ዘመቻ ግዜ ከሁሉ የባሰ ኦሮሞዎች በሚኖሩበት አካባቢ የተደረጉ ጦርነቶች አልነበሩም፡፡ ኦሮሞዎችም ወራሪ ነበሩ እንጅ አልተወረሩም፡፡ በኦሮሞዎች ላይም ከፍተኛ ጉዳት የነበረውና የደረሰውም ጅማ አባጅፋር የተካፈለበት በከፋ ንጉሰ ነገስት ዘመቻ መንግስት ነበር በከፋው ንጉስና በጅማ ኦባጅፋር ጦርነት ወቅት ብዙ ኦሮሞዎች አልቀዋል:: ይህን ታሪክ ግን የኦሮሞ ብሔርተኞችና ኦነግ አይነግሩህም፡፡
ይህን የተሳሳተ ትርክት ለማሳካትም ኦነግና ወያኔ ህዝቡ ከጎናቸው እንዲቆምና የድሮ የአማራ ነገስታት በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት በኦሮሞዎች ላይ ከፍተኛ በደል ፈጽመዋል በሚል በሃሰት የቀረበውን ትርክት የአሁኑ ዘመን የኦሮሞ ማህበረሰብ ሙሉ በሙሉ በመቀበል አማራን በአንደኛ ጠላትነት ፈርጆ በመነሳት ብዙ እልቂቶችን አይተናል፡፡
እውነታው ግን፦
-በአስተዳደር ረገድ ከአጼ ይኩኖ አምላክ ጀምሮ ያለውን የኢትዮጵያ መንግስታዊ መዋቅር ብንመለከት በሲቪልም ሆነ በጦር መስክ የጎሳ ልዩነት አናይም፡፡ በአመራር ደረጃም እንኳን ሲታይ ባለፉት 117 አመታት ከአጼ ቴዎድሮስ እስከ ጀኔራል ተፈራ ባንቲ የነበሩትን የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔሮች ስናይ 43.9% ወደ አማራው፣41% ወደ ኦሮሞው፣ 15.1% ወደ ትግሬው ጎሳዎች የሚያደላ እንደነበር በኢትዮጵያ ጥናት የታወቀው ምሁር ክርስቶፈር ክላፉም ባደረገው ጥናት(political Economy of Ethiopia P.221_231) በግልጽ ተቀምጦ እያለ የአሁን ግዜ አክራሪ ኦሮሞዎችና ኦነጋውያን የተጎድተናል የሃሰት ትርክት በመያዝ ስልጣን ይዞ አማራውን ለማጥፍት የሚሯሯጡ እንደሆኑ ማሳያው ስልጣን በተራችን ካልያዝን በሚል ሃሣብ አሁን ያለውን ከህወኃት የበላይነት ወደ ኦሮሞ የስልጣን የበላይነት ተሸጋግረናል፡፡ በግልጽ በኦነግ መሪነት የተጨፈጨፍት አማራዎች ቁጥር ብዙ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል In its 1993 World Report, Human Rights Watch, on page 8 of ‘ Africa Watch በግልጽ እንደተዘገበው ኦነግ በአርባጉጉ 154 አማራዎችን በግልጽ የገደለ ሲሆን፣ በዛው ዓመትም 46 ንጹሃን አማራዎችን ደም አፍሧል፡፡In July and August 1992 በኦፒዲዮና ኦነግ የጋራ ጥምረት የተቀሰቀሰው ረብሻ  በሚያዚ አጋማሽ ላይ 150 በላይ ንጹሃን አማራዎች ደም በበደኖ በከንቱ ፈሶ ቀርቷል፡፡ የዚህ የወንጀል ድርጊት ፈፃሚዎችም ዛሬ ላይ ከሆቴል ሆቴል ጥበቃ እየተደረገላቸው በአሁኑ የኦሮሞ መንግስት በፌሽታ ይኖራሉ፡፡
        ፀረ-አማራ ትርክት፪
       *****************
   አጼ ዮኋንስ ከድርቡሾች ጋር ባደረጉት ጦርነት ሲሞቱ ከግራኝ አህመድ ወረራ ወዲህ በኢትዮጵያ ላይ የበላይ ጠባቂ በማቆም የሃገሪቱን ነጻነትና አንድነት በረቀቀ ዘዴ ለማጥፍት በኢጣሊያ መንግስት የታቀደው ሴራ የአድዋን ጦርነት አስከተለ አጼ ምኒልክም በ1888 ዓ.ም በድል አሸነፉ፡፡ከአጼ ዮኋንስ ሞት በሗላ በአጼ ምኒሊክ እልህ፣ቂምና በቀል ያደረባቸው የትግራይ ባንዳዎች ከጣሊያን ጦር ጋር በመስራት ጣሊያንን ድል ያደረገው የአማራ ጦር ነው በማለት የሃሰት ትርክት በመንዛት የምኒሊክ ጦር ከኢትዮጵያ ህዝብ የተውጣጣ መሆኑ እየታወቀ ጣሊያን የሁለተኛውን ወራራ በ1928 ሲፈጽም ከ40 አመት በሗላ በተጠና መንገድ መጥቶ በጋዝ መርዝና በቦምብ ብዙ አማራዎችና ሌሎችም ጀግኖች አልቀዋል፡፡ ከወቅቱ የትግራይ ባንዳዎች ውስጥም ዜናዊ አስረስ(የሟቹ ጠ/ሚ መለስ አባት) ፣ባሻህ ወልዱ (የትግራይ ክልል መሪ የነበረው የአባይ ወልዱ አባት ) ፣ የአባይ ፀሀየ፣ ስዩም መስፍንና የገብረ ጽዮን አባቶች ባንዳዎች እንደነበሩ አቶ ገ/መድህን አርአያ ከSBS ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ነግረውናል።
የአድዋ ጦርነት ጋር ተያይዞም አጼ ምኒልክን ከአማራው ጋር በማገናኘት አጼ ምኒልክ ሆን ተብሎ የጣሊያን ጦር ሸሽቶ ኤርትራ ላይ ሲደርስ የተመለሱት ኤርትራን ለማስወረር ነው የሚል የጣሊያን ባንዳዎች የትግራይ ሰዎች በአማራውና በኤርትራውያን ላይ ከፍተኛ የሆን ጥላቻ እንዲፈጠር በማድረግ የኤርትራ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር ከህውሃት ጋር በመሆን በአማራው ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ እውነታው ግን አጼ ምኒልክ በጊዜው አገር ውስጥ በነበረው የጸጥታ ሁናቴና በጣሊያን በኩልም ኤርትራን ለመከላከል በተደረገው ዝግጀት ምክንያት እንዲሁም አድዋ በዘመተው ጦር መዳከምና ስንቅ ማለቅ ምክንያት ጦርነቱን ቀጥለው ጣሊያኖችን ከኤርትራ ማስወጣት አልቻሉም፡፡ ነገር ግን ኤርትራን አጼ ምኒሊክ ለጣሊያን ቅኝ ተገዥ አድርገዋታል  የሚለው ሃሰት የፈጠራ ወሬና የትግራይ ነገስታቱን ታሪክ ለመሸፈን እንጅ ኤርትራ በአዋጅና በግልጽ በጣሊያን ቅኝ ግዛት ስር የወደቀችው ከአድዋ ጦርነት ከ 6 ዓመት  በፊት እ . ኤ .አ በ 1\1\1890 በአጼ ዮሗንስ ዘመነ መንግስት ግዜ ነበር፡፡ በዚህ የሃሰት ትርክት የተነሳው ወያኔና ሻቢያ በአማራው ላይ ከፍተኛ ፍጅት ፈጽመዋል፡፡ ይህም ከኦነግ ቀጥሎ ህወኃትና ሻቢያም የፖለቲካ ማዕከላቸውና መነሻቸው አማራውና አፄ ምኒልክ ናቸው የዚህ ትርክት መሰረቱ በዝቅተኛነት ስሜት የናወዙ ፖለቲካን የማይረዱ ፖለቲከኞች ስላሉን ነው፡፡ በነገራችን ላይ ሶስቱም ድርጅቶች ይህን ፀረ-አማራ ትርክት በጋራ ተነጋግረው የነደፉት ሊያታግል የሚችል ሌላ ሃሣብ ስለሌላቸውና ባላቸው ፀረ-አማራ አቋም ነው።
         ፀረ-አማራ ትርክት.፫
       ******************
 ከ1974-1991 የደርግ ወታደራዊ መንግስትም ቢሆን በአማራ ወጣቶችና ምሁራን ላይ በቀይሽብር ስም ይህ ነው የማይባል እልቂት በመከሰቱ የትውልድ ክፍተት ፈጥሮ አልፏል፡፡ ደርግ ብዙ የአማራ ምሁራንና ወጣቶችን ከገደለ በሗላ መሬት ላራሹ ዓዋጅ በማውጣትም አማራዎችን የፊውዳል ስርአት ተከታይ በማለት የነበራቸውን መሬት በመቀማትና የመሬት ሽግሽግ በማለትም ብዙ ገበሬዎችን መሬት በመቀማት ጎዳና መውደቃቸው ሳያንስ የደርግ ወታደራዊ ሃይል የታጠቁ አማራዎችን ትምክህተኛና ነፍጠኛ በማለት በሃይል የጦር መሳሪያቸውን እንዲነጠቁ ተደርገዋል፡፡ እውነታው ይህ ሁኖ እያለ መንግስቱ ሃይለማሪያም በኤርትራና ትግራይ ላይም ተመሳሳይ በአማራዎች ላይ እንደፈጸመው ግፍ እኩል መፈጸሙ እየታወቀ ከአማራው ህዝብ እንደተሰነዘረ በማስመሰል ሻቢያና ወያኔ በአማራው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጥቃት ፈጽመዋል፡፡
       ፀረ-አማራ ትርክት.፬ 
      ******************
የፋሽስት ወያኔ የሃሰት ትርክትም ተመሳሳይ ሲሆን የአማራን ጥላቻ በግልጽ የያዘ ማንፌስቶ ይዞ የመጣ ሲሆን የወያኔ መስራቹ ገ\መድህን አርአያ በ12/31/2011 ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅም የወያኔን ፀረ-አማራነት እንዲህ እንደሚል አስረድተዋል፦
”… ትግራይ ነፃ አገር የነበረች ሉዓላዊነትዋ ተከብራ በነፃ ትኖር የነበረች አገር በአፄ ሚኒሊክ ተወራ የአማራው ቅኝ አገዛዝ ሆነች። ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት ነች፡፡ ይሄ የወያኔ ማኒፌስቶ ነው። ዋናው ሕገ ደንብ ነው… ስለዚህ ትግራይ ከአማራው ቅኝ ገዢ እጅ አስወጥተን የትግራይን ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ መንግስት መመስረት አለብን የሚል ነው፡፡ሁለተኛ፣ሶስተኛ አማራ የሚባል የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው። ጠላት ብቻ ሳይሆን የትግራይ ሕዝብ ጠላት ጠላት ነው። ስለዚህ አማራን መምታት ፤ ማጥፋት ፤ አለብን። አማራ ካልጠፋ ፤ አማራ ካልተደበደበ ከዚህ መሬት ካልተነቀለ ትግራይ በነፃ ልትኖር አትችልም። ለምንፈጥረውም መንግስት እንቅፋት የሚሆንብን አማራ ነው የሚል ነበር።” የዚህ ማኒፌስቶ ዋናው ፀሀፊዎች አረጋዊ በርሄ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስዩም መስፍን፣መለስ ዜናዊና አባይ ፀሃየ ሲሆኑ ይህን ስራ የሰሩ በግልፅ የዘር ማጥፋት ድርጊትን በፖሊሲ ደረጃ የቀረጹ ሰዎች ዛሬም አሉ፡፡
ወያኔዎች አማራውን ክፉና ሰይጣናዊ በማስመሰል የሚሰሩት የማዋረድ ድርጊት ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ በ 1980ዎቹና 1990ዎቹ አካባቢ ያ ሁሉ እልቂት ከመከሰቱ በፊት ሲያደርጉት ከነበረው ዘመቻ ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ነው፡፡ ለዚህም ከወያኔ የሰነድ ማስረጃ በተጨማሪ በአካል ተንኮሉ ሲጠነሰስ ከነበረው ከገ\መድህን አርአያ በላይ ማስረጃ የለም፡፡
ወያኔ ለዚህ ማንፊስቶው ተግባራዊነቱም ከጫካ ትግል ጀምሮ ወደ ስልጣን እስኪመጣ ድረስ የብዙ አማራዎችን ደም ያፈሰሰ ሲሆን በሽግግር መንግስቱም ወቅት አማራ የለም በህገ መንግስቱም የማርቀቅ ሂደት አይሳተፍም ከተባለ በሗላ እንደገና ኢህዴንን ወደ ብአዴን በመቀየር ወያኔ ኤርትራውያንን ትግሬዎችን እና እንዲሁም የሌላ ብሔር ተወላጆችን የአማራው የይስሙላ ተወካይ አድርጎ በማሰብ ወያኔ የትግራይ ፍሽስቶች ስልጣንና ሃብት የሚይዙበትን መንገድ ማመቻቸት በሚችሉበት መንገድ ከሰሩ በኋላ የአማራውን ሰፍፊ ለም መሬቶች በወሎ እና በትግራይ እንዲሁም በአፍርና በቤንሻንጉል በኩል የነበሩ ይዞታዎችን በማጥበብ አማራውን የማጥፍት ሴራቸውን የገፉበት ሲሆን ከላይ በኦሮሞ ወረራ ያጣውን ግዛቱን ከማጥበብ ጀምሮ አሁን ያለበትን ነባር መሬቶቹን እና የአባቶቹን ርስት አጥቶ መተንፈሻ አየር አጥቶ በህይወት ያለውም በወያኔ የተለያዩ አማራውን በሚያፍኑ ህጎች ተተብትቦ በየማሰቃያ ካምፖች በእስርና በእንግልት ብዙ አመታትን አሳልፏል ዛሬም ተመሳሳይ ድርጊቶች በኦሮሞ ፅንፈኞች እየተፈፀሙ ይገኛሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በህገ መንግስቱም በግልጽ የአማራውን ይዞታ በፊደራሊዝም ስም ከፍፍሎ ከመውሰድ በተጨማሪ የፌደራሊዝም ስርአቱ መነሻ ሃሳቡ የአማራው ጨቋኝ ገዥዎች በሌሎች ብሔሮች ላይ ያደረሱትን በደልና ጭቆና ለማስተካከል የረቀቀ ህገ መንግስት እንደሆነ አድርጎ በማቅረብ አማራው በሌሎች ብሔሮችም እንዲጠላ ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል፡፡
ከወያኔ ሞት የተረፈውን አማራም በህይወት እንዳይኖር በኢኮኖሚ፣በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዳይኖረው ተደርጎ በከፍ የድህነት ደረጃ እንደሚገኝ  እና በትምህርት በጤና እንዲሁም በሁሉም ተቋማት በአፍሪካም የመጨረሻው ድህነት ውስጥ የሚገኘው የአማራ ክልል እንደሆነ የአፍሪካ ሪፖርት የዓለም ባንክን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ይህ በወያኔ ዘመን የተፈፀመው ሁሉ ድርጊቶች ዛሬም ላይ በጎንደር፣ በለገጣፎ በሰበታ፣ በወልቃይት፧ በሸዋ፧በራያ፧ ወዘተ ቀጥሏል፡፡
የነፍጠኛ አማራ ትርክት ፭
*********************
ህወኃት የብአዴን እና ኦፒዲዮ ከፍተኛ አመራሮችን ለህዝብ የሚወግኑ ሲመጡ የብአዴን አመራሮችን የነፍጠኛና ትምክህተኛ አመለካከት የኦፒዲዮ አመራሮችን ጠባብና ዘረኛ አመለካከት በሚል የዳቦ ስም ሲገመግማቸው ነበር፡፡ ዛሬ ያ ሁሉ አልፎ ጠባቡ በነፍጠኛው የትግል ውጤት ቤተ መንግስት ሲገባ የህወኃትን መስመር በመያዝ ከህወኃት የበለጥኩ ፀረ -አማራ እኔ ነኝ በማለት መስቀል አደባባይ ሲፎክር መንጌ በዛ መድረክ ላይ የወረወረው በጠርሙስ የሞላ ደም እንዴት እንዳላስመጣ ገርሞኛል፡፡
ከላይ እንደጠቀስኩት የኦሮሞ አክራሪዎችና ተስፋፊ ብሔርተኞች ከህወኃት ሰዎች ጋር ያላቸው ፀረ-አማራ አቋም አንድ ሲሆን ምናልባትም የሚፎካካሩት እኔ የበለጠ ፀረ- አማራ ነኝ በሚል መገለጫዎቻቸው ነው። ይህን ጥምረት የተረዱ ቁርጠኛ የህዝብ አመራሮችም በተቀነባበረ ሴራ እንዴት እንደተገደሉ የአቶ ሽመልስ ንግግር ግልፅ ይመስለኛል፡፡ ( የኦፒዲዮ አመራሮች አማራውን ነፍጠኛ በማለት እንዴት ከኦሮሚያ አካባቢዎች እንዲሰደዱ ያደረጉበትን በምክር ቤቱ ቀርቦ የረቀቀውን የዞን 13ትን ስፍት ለመደንገግ የወጣውን መመሪያ የኦፒዲዮ ሰዎች የፈፀሙትን ግልፅ የዘር ማጥፋት ድብቅ የሰነድ ሴራ ለህዝብ የማቀርብ ይሆናል)፡፡
በነገራችን ላይ በዓለም የፖለቲካ ታሪክም ሆነ በኢ /ያ ነባራዊ ሁኔታ የነፍጠኛ ስርዓት የሚባል የፖለቲካ ስርዓት የለም፡፡ የመንግስት ስርዓተ ውቅር ግልፅና ተመሳሳይ ነው። ስርዓት የሚባለው የሚመራበትና የሚተዳደርበት ህግና ደንብ እንዲሁም የፖለቲካ አይዲዎሎች ያለው እንጅ አክራሪ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እንደሚሉት የሰፈር ወግ አይደለም፡፡ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ለኢ/ያ ካደረጉላት ይልቅ ያደረጉባት መጥፎ ሁኔታዎች ብዙ ናቸው፡፡ ሀገር ወዳዶች ሲገነቧት የኦሮሞ ፖለቲከኞች ከውጭ መንግስት ጋር እየሆነ ሲያደሟት ነበር፡፡ አሁንም የባሰ ነው።  ለምሳሌ ያህል ከ1964-1970 የነበረውን የባሌ የገበሬዎች ዓመፅ ተኩሶ በጥይት መጥቶ መሮጥ የሚባለውን ስልት ተጠቅመው በወታደራዊ ካምፖችና የፖሊስ ጣቢያዎች ላይ መንግስትን ሲቃወሙ የነበሩ የኦሮሞ አማፂ ቡድን አመራሮች የመሳሪያ ድጋፍ እስከ 1969 ያገኙ የነበሩት ከሶማሊ መንግስት ነበር። የሶማሊ መንግስትም ታላቋን ሶማሊያ ለመመስረት እንደ ስትራቴጂ አጋር ወስዶ ኢ/ያን ሲያተራምስ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የዚህ እቅድ ፈፃሚዎች ነበሩ፡፡
ለዚህ የኦሮሞ አማፂ ቡድን ኢ/ያን የማተራመስ ስራ ሲሰራ ይሰጠው የነበረው የጦር መሣሪያና ወታደራዊ ድጋፍ የተቋረጠው በ1969 የሙሀመድ ሲያድ ባሬን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ ነው። የኦሮሞ አማፂ ቡድኑ በደቡብ ምስራቅ ኢ/ያን የማተራመስ እቅዱ በሲያድ ባሬ ውሣኔ ከሶማሊ መንግስት ሲባረሩ አቅም በማጣቱ ከቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ጋር ስምምነት ፈጥረው ከቆዩ በኋላ በ1973 ኦነግን መሰረቱ፡፡ ኦነግ በ1974 እና በ1976 ከመንግስት ጋር ጦርነት ሲከፍት ነፍጠኛ አማራ ነው በሚል ትርክት በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ አማራዎች ላይ በግልፅ የዘር ጭፍጨፍ ፈጽሟል፡፡
እነዚህ ሀገርን ሲወጉ የነበሩ ፖለቲከኞች ትላንት ከጠላት ጋር ሁነው ያደሟትን ሀገር ግን ጠብቆ ያቆያቸው ነፍጠኛው ነው፡፡ የኢ/ያ ህዝብ ከጠላት ጋር ሲዋጋ የቆየው በነፍጡ(በመሳሪያው) ነው። ያም ነፍጠኝነት ይባላል ይሄም ክብር ስለሆነ ነፍጠኛ ለሚሉን ባንዳ እንላቸዋለንና ልብ ይስጣችሁ፡፡

3 COMMENTS

  1. ሃገሪቱ የት እየሄደች ነው ብሎ ፌዘኛውን ቢጠይቀው “የት እሄዳለሁ ብለህ ነው የተሳፈርከው” አለው ይባላል። ሃገሪቱን የገደሉና በመግደል ያሉ የዘር ፓለቲከኞች ናቸው። የተሰረዘውን የእሁድ ስብሰባ በመፍራት የኦሮሞ ባለስልጣኖች የአዲስ አበባን መግቢይ በፍተሻና በመዝጋት ሲያተራምሱ፤ በጎሃጽዪናን በደጅን ደግሞ ሰውን ለስቃይና ለመከራ በመዳረግ መንገድ ዘግተው እንደነበር ተዘግቧል። የእኛ ነን ባለተራ ፓለቲከኞች ሃገሪቱን በማተራመስ የኦሮሚያ ካርታ በፊስቡክ ለቀዋል። እንደ አቶ በቀለ ገርባ ያለው የጠባብ ብሄርተኛ መሪ ስለ ሃገራቸው ቆዳ ስፋት ሲያወራ ለሰማው በእውነት ይህ ሰው ተምሮአል? በከፍተኛ ተቋማትስ ገብተው በእነዚህ መሰል ሰዎች እጅ የሚማሩ ፍትህ ያገኛሉ ብሎ መገመት ይቻላል? አይቻልም። የሃገሪቷን በሞራልና በዘር ፓለቲካ መላሸቅ በቅርብ በእህቴ ላይ ከደረሰው ልጥቀስ።
    እህቴ ለጉዳይ ወደ አንድ መ/ቤት ትሄዳለች። ስትገባ ፊት ለፊት “የፊንፊኔ ከተማ” የሚል ካርታ ተሰቅሎ ታያለች። ባለስልጣኑም ተቀምጭ በማለት የመጣችበትን ከተረዳ በህዋላ እሺ ችግር የለም ከሰሞኑ ይሰራልሻል አላት። አመስግና ልትወጣ ስትል ማታ ከስራ ውጭ የት እንገናኝ ይላታል። እንደ እድል ሆኖ እህቴን ያየ ሁሉ እንደ ወሎ ፈረስ ሊጋልባት የማይፈልግ የለም። እኔም አልፎ አልፎ በዚህ ዙሪያ ላይ እቀልዳታለሁ። ግን ቁም ነገረኛ እና ባለትዳር የ 3 ልጆች እናት ናት። አይመቸኝም ብላ ተሰናብታ ወጣችና ጉዳዪን ለእኔ ነገረችኝ። እንዴ ባለትዳር የ 3 ልጆች እናት ይል የለ ማመልከቻው? አዎ፤ እነርሱ ታዲያ ምን ገደዳቸው፤ የሃገሪቱ ችግር እኮ ሞራላዊ መላሸቅም ጭምር ነው በማለት ፊቷን ጠቆር አድርጋ ነገሩን ዘጋችው። ያልቅልሻል የተባለውም ሥራ ሳይሰራ ቀረ። እርሷም አልተገኘች።
    ዛሬ ነፍጠኛ እያሉ የሚያላዝኑት የኦሮሞ ፓለቲከኞች ለኦሮሞ ህዝብ የሰረቱ አንድም ነገር የለም። እድሜ ለአረቦች፤ ለኤርትራ እና በሃይማኖት ስም ተጨቁነናል በማለታቸው በጀርመን በአሜሪካ በስዊድንና በኖርዌ አይዞአችሁ እኛ መጥለያ እንሰጣችሁሃለን እያሉ ጥቂቶችን ከማበልጸጋቸው ሌላ ለሰፊው የኦሮሞ ህዝብ የሆነለት እዚህ ግባ የሚባል ነገር የለም። ልክ እንደ ወያኔ ህዝቡ በስሙ መነገጃ ሆኖአል። ካልፈው ተምሮ የማይታረም የፓለቲካ ክምችት የተቃመሰው በተንኮል በመሆኑ ዛሬም ህዝባችን ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ያተራምሱታል። አይ ሃገር። እንዲህም ብሎ መደመር የለ። በመቀሌ ከውጭ ዲፕሎማቶች ጋር በመነጋገር ለመገንጠል ዝግጅት ላይ ናቸው። በተሰራጨው የኦሮሚያ ካርታ መሰረት ደግሞ “ኦሮሚያ” ሃገር ልትሆን ነው። ወቸው ጉድ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል አሉ። ዶጋ አመድ ለመሆን ካልሆነ በስተቀር ጭራሽ መገነጣጠሉ ለሃገሪቱ እንደማይበጅ ከአሁኑ የታወቀ ነው። ሃገሪቱን እሳት ለኩሰው እነርሱ መጠጊያ ወደ ሰጧቸው ሃገሮች በመሮጥ ራሳቸውን ሊደብቁ ነው። የወስላታ መንጋ። በሃበሻው የሰጣ ገባ እና የግብግብ ፓለቲካ ውስጥ ለህዝብ የቆመ መንግሥት ተፈጥሮ አያውቅም። በህዝብ ስም የሚነግድ እንጂ። ችግሩ ለውጥ የተባለውም ከበፊቱ የከፋና የከረፋ መሆኑ ነው።
    የመሰዳደብ ፓለቲካ፤ በባንዲራ፤ በቋንቋ፤ በዘር፤ በሃይማኖት ስንሸራከት አለሙ ሁሉ ጥሎን ሄደ። እነ ጋና (አክራ) 60 ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ አስገራሚ ነገር እየሰሩ ነው። ጎረቤት ሃገር ኬኒያ በዘር ቢዋቀሩ አንድ ቀን አያድሩም። የሃበሻው ልብ ግን ድንጋይ ነው። በህብረት መክሮ በግል ተሾልኮ ሌላውን ለሞት የሚዳርግ ጽንፈኛ ልብ። ሰው ነፍጠኛ መባሉ ስድብ አይደለም። ባያውቁት ነው እንጂ ነፍጠኞች ለሃገር የተፋለሙ፤ ወገንን የሚያቅፉ፤ ለእኔ ከማለት ይልቅ ለእኛን ያስቀደሙ ነበሩ። ግን በሃገራችን የሞተላት ሳይሆን የገደላት ስለሚበላ እውነት ከተራቡት ጋር አብራ ሞታለች። አሁንም በተለያዪ የሃገራችን ክፍሎች ዘርና ጎሳን ቋንቋና ሃይማኖትን ሳይመረኮዙ የቆሙ ጥቂት ወገኖቻችን በፓለቲካ አሻጥር አፈር ለብሰዋል፤ በህይወት ያሉትም እንደ ድር አውሬ በድንጋጤና በፍርሃት እየኖሩ ነው። ታዲያ ዝም ብሎ አካኪ ዘራፍ ቢሉት ወንድምና እህትን ገድሎ መፎከር ብቻ ነው የሚሆነው። በእብሪት የተቀጣጠለ እሳት የሚበላው ሁሉን ነው። ጎበዝ እናስተውል!!

  2. በእጅህ ነፍጥ ለመያዝ ትመኛለህ፣ ጭንቅላትህ ግን በንፍጥ ነው የተሞላው! የጀርመን ናዚዎች ለፈጸሙት ጀኖሳይድ ተጸጽተው ይቅርታ በመጠየቅ ካሳም እየከፈሉ ነው ያሉት። ያንተ አይነቱ ንፍጣም ግን፣ በኦሮሞና በሌሎች የደቡብ ህዝቦች ላይ ከምኒሊክ ጀምሮ እስከዛሬ በነፍጥ እየተካሄደ ላለው የዘር ጭፍጨፋ እንኳን ይቅርታ ሊጠይቅ ታሪኩንም ክዶ፣ የተበደሉት ህዝቦች ታሪካቸውን በመዘገባቸው በተገላብጦሽ ይቅርታ ካላላችሁኝ እያለ ያቅራራል!! ይህን ምን ይሉታል?? ድንቁርና ወይስ ወሰን የለሽ ብልግና??

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.