በአፋር ክልል ርዕሰ መዲና ሰመራን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎችን በተመለከተ ከሰልፉ አስተባባሪዎች የተላከ የተጠቃለለ የአቋም መግለጫ

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ጥቅምት 6 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

ከሰሞኑ በአፋር ክልል ከጅቡቲ ድንበር ጥሰው ወደ አፋምቦ ከባድ መሳሪያ የታጠቁ አካላት በንፁሀን የአፋር አርብቶ አደሮች ላይ የፈፀሙትን አሰቃቂ ጥቃትና የመከላከያ ሚኒስትር የሰጠውን መግለጫ በመቃወም የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችን በተመለከተ የተሰጠ የአቋም መግለጫ ደርሶናል!

“ላለፉት አስር ወራት በምስራቃዊው የኢትዬጵያ ክፍል የነበረው ሁኔታ ለኢትዬጵያ ብሎም ለአፍሪካ ቀንድ ትልቅ ምልዕክት ሲያስተላልፍ ቆይቷል።

መልዕክቱ በብሔር ስም ድንበር ተሸጋሪ የሆነ የሽብር እንቅስቃሴ መጀመሩንና ተፅዕኖው ከኢትዬጵያ አልፎ ለአፍሪካ ቀንድ የሚትረፍ ጦስ እንዳለው በግልፅ ሲታይ ቆይቷል።

ከጅቡቲ እስከ ሱማሌላንድ፣ ከጅግጅጋ እስከ መቋድሾ በተለያየ መልኩ የሚሳተፉበት ወረራ በክልላችን ላይ ሲቃጣ፣ የቀጠናው ሰላም ለማድፈረስ ለሚፈልጉ ኃይሎች በር ሲከፈት የፌዴራል መንግስት እንዝህላልነት ብዙ ዋጋ አስከፍሎናል።

ሆኖም ግን የአፋር ክልል እንደ ወትሮው ሁሉ የኢትዬጵያ የድንበር ጠባቂነቱን ሚና በሚገባ ከመወጣት ውጭ የአገር ህልውና አደጋ ላይ ሊጥል ወደ ሚችል እርምጃ ከመውስድ ታቅቦ ቆይቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዳሜ ቀን ኦብኖ ላይ ዘመናዊ መሳሪያዎችን በታጠቁ በውጭና በውስጥ ኃይሎች በተደረገው ጭፍጨፋ በሚድያ በማውገዛችን ብቻ የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት አሳፋሪ የሆነ መግለጫ አውጥቶብናል።

ህዝባችን እንደማንኛውም የኢትዬጵያ ዜጎች ጥበቃ ባይደረግለትም እንኳ ሊላገጥበት አይገባም። የአፋር ህዝብ እየሰራ ያለው የአገር መከላከያ መስራት የነበረበት ሉዓላዊነት የማስከበር ስራ ነው።

ለዚህ ተጋባራቸው ሊሸለሙ እንጅ
ሊሸማቀቁ አይገባም። ድሮም ለአገርና ለድንበር ለምንከፍለው መስዋዕትነት ሌላ ቀርቶ ምስጋና ከማንም አካል ፈልገን አናውቅም። ወደ ፊትም አንፈልግም።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የአፋር ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለው የዘር ማጥፋት ሙከራ እንደ ተራ የውሃና የግጦሽ ግጭት አድርጎ ማቅረብ በፉፁም ተቀባይነት አይኖረውም።

በመሆኑም

1.ለጦርነቱ በር ከፋች የሆነው አፋርና የሱማሌ ክልል የወሰን ማካለል ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለህዝቡ ይፋ መደረግ አለበት። ከዛ ውጭ ባልሆነ ሁኔታ የሚደረገው ማንኛውም የእርቅ ሙከራ ተቀባይነት የለውም።

2. የአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ ከውጭም ከውስጥም እየተቃጣ ባለው የሽብር ተግባር ላይ የተሳተፉ አካላት በሙሉ ለህግ መቅረብ አለባቸው።

3.የአገር መከላከያ ሰራዊት ላወጣው መግለጫ ይቅርታ ጠይቆ ለክስተቱ በሚመጥን መልኩ እርምት መስጠት አለበት። በአሸባሪዎች ላይ እርመጃ መውሰድ አለበት። ያ ካልሆነ ግን አገርቷን ወደ አለማረገጋት የሚከት መሆኑ መታወቅ አለበት።”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.