የትግራይ ክልል አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደ አማራ ክልል አንደማይልክ አስታወቀ

የትግራይ ክልል አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪችን አማራ ክልል ወደሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች አልክም አለ።

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ገ/መስቀል ካሕሳይ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፡ “ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ወደ ሚሰነዘሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እና ኃላፊነት ወደማይወስድ ክልል አዲስ ተማሪዎችን ላለመላክ የክልሉ አቋም ነው” ብለዋል።

“አማራ ክልል የተመደቡት 600 ተማሪዎች እንደማይሄዱ ለሚመለከተው የፌደራል መንግሥት አሳውቀናል። ይህ የክልሉ አቋም ነው” ሲሉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ዘንድሮ፤ በትግራይ ክልል የዩኒቨሲቲ መግብያ ፈተና ወስደው ማለፍ የቻሉ የተማሪዎች ቁጥር ከ9000 በላይ መሆኑን የጠቀሱ ኃላፊው፤ ወደ አማራ ክልል ተመድበው የነበሩ ተማሪዎች ከ2000 በላይ እንደነበረ እና ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግስት አካላት ጋር በተደረገው ውይይት ወደ 600 ዝቅ እንዲል መደረጉን ተናግረዋል።

“ከአንድ ወር ተኩል በላይ የክልሉ መንግሥት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሲወያይ ቆይቷል። የተቀሩ 600 ተማሪዎችን ሌላ ቦታ እንዲመደቡ ይሰራል። ይህ የማይሆን ከሆነ ግን የትግራይ ክልል ሌላ አማራጭ ይፈልጋል እንጂ ተማሪዎቹን ወደዛ አይልክም” ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በዩኒቨርሲቲ አመዳደብ ስርዓት መሰረት ከአንድ ክልል አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል 40 በመቶ የሚሆኑት በክልላቸው የተቀሩት 60 በመቶ ደግሞ ሌላ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይመደቡ እንደነበረ የሚያስታውሱት ኃላፊው፤ “ብሔርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በበዙበት ወቅት ይህ ተቀይሮ 10 በመቶ በክልላቸው 90 በመቶ ደግሞ ወደ ሌላ ክልል እንዲላኩ መደረጉ አግባብ አይደለም” ብለዋል በሰጡት መግለጫ።

ይህ እንዲስተካከል ከፌደራል እና ከሌሎች አካላት ጋር ውይይት መደረጉን እና 20 በመቶ በክልላቸው 80 በመቶ ደግሞ ከክልል ውጪ እንዲመደቡ መወሰኑን ጨምረው ተናግረዋል።

የትምህርት ቢሮው ኃላፊ ገ/መስቀል ካሕሳይ ትግራይ ክልል ወደሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የሚመጡ ተማሪዎች “ምንም አይነት የደህንነት ችግር አይገጥማቸውም” ብለዋል።

የትምህርት ቢሮ ኃላፊው ሁለተኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ በሆኑ ተማሪዎች ዙሪያ ያሉት ነገር የለም

BBC Amharic

2 thoughts on “የትግራይ ክልል አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደ አማራ ክልል አንደማይልክ አስታወቀ

  1. አይ ወያኔ እውነትም ዘረኛ። ራሱ በዘረኝነት መርዝ ሃገሪቱን ማጥ ውስጥ ከቶ አሁን እንደገና ተመልሶ የትግራይ ተማሪዎችን ወደ አማራ የትምህርት ተቋሟት አልክም ማለቱ የቱን ያህል የጨለማ ፓለቲካ እንደሚከተል ያመላክታል። የወያኔ ዲሞክራሲ አፍንጫው ላይ ነው። እንደ ድር አራዊት በዘሩና በዙሪያው ብቻ የሚያነፈንፍ። የትግራይ ተማሪዎችን ወደ ሌላ የትምህርት ተቋማት መላክ እኮ የማእከላዊ መንግሥት ሥራ እንጂ ወያኔ ያሰመረው የክልል ውሳኔ አይደለም። ግን ጎብዝ ዝም እንበል። የዚህ ድርጅት የሮም አወዳደቅ እየተፋጠነ ነው። በአንድ በኩል ተከበናል ታጠቁ እያለ ለትግራይ ህዝብ ጥሪ ሲያቀርብ፤ በሌላ በኩል ምርጫ በጊዜው ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ ይለናል። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማሪያም በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ እንዳሉት እነዚህን ጉዶች ሰብስቦ አንድ እስርቤት መክተቱ ለትግራይ ህዝብና ለቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ እፎይታ ነበር። ግን የመደመሩ ህሳቤ ገዳይና ተገዳይን የጨፈለቀ በመሆኑ ልበቢሱ ወያኔ አሁንም እሳት እየጫረ እና እያስጫረ ህዝባችንን ያጋድላል።
    በመሰረቱ የትግራይ ተማሪዎች ወደ አማራ ክልል የትምህርት ተቋማት አይሄድም የሚለው ለሁለት ነገር ነው። ሀ. እርሱ በለኮሰው እሳት ጦርነት ላይ ያለ ክልል በመሆኑ ለ. የአማራ ክልል ተወላጆች ወደ መቀሌ እንዳይመጡበትና የጠ/ሚ አብይን የመደመር አጀንዳ ከኦነግ ወስላቶች ጋር ሆኖ ለማፈራረስ እንደሆነ ህጻን ልጅ ያውቀዋል። በእውነት የትግራይ ልጆች መስዋዕትነት ሃገር ለማፍረስ ነበርን? ሞታቸው ሰው በዘሩ እንዲሰለፍ ነውን? አይ ሃገር። ይህን ጉድ ሳያዪ በየበረሃው ለሃገር አንድነትና ድንበር የወደቁ፤ በወታደሩ መንጋ በደርግ በግፍ የተረሸኑ፤ ወያኔ 27 ዓመት እያፈነ አፈር የመለሰባቸው ሁሉ አሁን ሃገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ሳያዪ ማረፋቸው ተመስገን ያሰኛል። አሁን ያለንበት ጊዜ ከመሳፍንት ዘመን የከፋ፤ የንጉሱን ዘመን ያስናፈቀ፤ እንዲያውም አንዳዶች እንደሚሉት የደርግ ጊዜ በመጣ የሚያሰኝ ነው። ሰው በሃገሩ ሁለተኛና ሶስተኛ ዜጋ የሚሆንባት፤ ውጣ ውጪልኝ፤ አትምጣ አልመጣም የሚባልበት ፓለቲካ። ተስፋ ያስቆርጣል። ግን እኮ የለም ተስፋ አንቆርጥም። “አንድ ጊዜ ኢትዮጵያዊ ሆነን ተወልደናል እና” አቤ ጉበኛ – አልወለድም። ወቸው ጉ አንሰማው የለ፤ የትግራይ ልጆች አማራ ወደ አሉ የትምህርት ተቋማት አንልክም? የትግራይ ህዝብ ይህን ቡድን ዝም ብሎ ይመለከታል? ማጥፋት አለባቸው። ኢትዮጵያ ከትግራይ ተነጥላ ኖራ አታውቅም። ምን አይነት ጉዶች ናቸው እነዚህ ከትግራይ የበቀሉ አውሬዎች? ሰው በ 21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ቆሞ በድንጋይ ዘመን ፓለቲካ ይመራል? ሃገር ሲያረጅ ጃርት ያበቅላል ይሉሃል እንደዚህ ነው። የሙታን ጥርቅም። ለአጭር ዘመን የሰዎችን ተስፋ የሚያጨልም የዘር ፓለቲከኛ። የሰው ልጆች መብትና ነጻነት መጋኞች። አምላክ ያጥፋችሁ!

  2. Comment:
    Comment:
    bzu amara temariwech betelegn wolega balu universitiwoch, burehora ena tgrai universitiwoch yetemedebu amnam zendrom qlhiedum mkniyatum ashebari oromo ena woyanie amara temariwechn sigel slayu new. Tmhrt aquartew quch blewal yechalu begl keflew yimaralu.
    Gin woyanie adgrat aksum meqelie universitowoch amara temariwechn chefchifo atefawn slefera tgrie temariwoch amara kilil aymedebubgn blo liela kilil asmedbual. Amara temariwochm yih edel yisetachew. Adlo new tgriewochun medbo amaran embi maletu.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.