“አፍራሾችን ማሸነፍ እንጂ መለመንም፤ መለማመጥም አያስፈልግም” – አቶ ዮሐንስ ቧያለው

አቶ ዮሐንስ ቧያለው

አፍራሾች ያው ለማፍረስ የቆሙ ስለሆኑ ምንም አይነት መልዕክት ብንናገር ሊቀበሉን አይችሉም፡፡ እነሱ ይህንን በመግለፃቸውም ብዙ የሚገርም አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሥራቸው ነው፡፡ የተቀጠሩበት፣ የተደራጁበት፣ ከፍተኛ ገንዘብ የሚፈስበት ሥራቸው ስለሆነ፣ ኑሯቸውም ስለሆነ ሰው ኑሮህን ለምን ትኖራለህ አይባልም፡፡

አፍራሾቹን ሳይሆን ያልገባቸው፤ ጥሩ መስሏቸው እነዚህን አፍራሾች የሚተባበሩ፤ አልፎ አልፎ ደግሞ ጥሩ ይሠሩና በበነገታው የሚቀለበሱ፤ የአማራን ትግል ወደ ኋላ የሚመልሱና ብዙ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ ነገር ግን መነሻና መድረሻቸውን የማያውቁ የአማራ አክቲቪስቶች አሉ፡፡ አንዳንዴ ብስለት ያለው ጥሩ ነገር ይፈጥራሉ። ሌላ ጊዜ ደግሞ በሌላ አጀንዳ ተጠልፈው ይላተማሉ፡፡ ከዚህም አልፎ እርስ በርሳቸው ይጋጠማሉ፡፡

እነሱ በተከፋፈሉ ቁጥር ደግሞ ሌላው የተከፋፈለ ይመስላቸዋል፡፡ አጀንዳ የሚሰጣቸውን እየተቀበሉ የሚያናፍሱ ኃይሎች አሉ፡፡ እነዚህ የራሳችን ኃይሎች ስለሆኑ ሊታረሙና በትክክለኛው አቅጣጫ ሊሄዱ ይገባል የሚል አመለካከት አለን። የተደራጀውን አፍራሽ ኃይል ግን ማሸነፍ እንጂ መለመንም፤ መለማመጥም አያስፈልግም፡፡ የተደራጀ የ“ዲጀታል” ሠራዊት ስለሆነ መልክት በማስተላለፍ ማስተካከል አይቻልም፡፡ ስለዚህ በእኛ በኩል ያለው ህዝቡንና የህዝቡን ትግል እንዳይጐዳ ብቻ ነው ትምህርት መስጠት ያለብን፡፡ ትምህርት በመስጠት ረገድ በ“አክቲቪስቶቹ” በእኛም በኩል ድክመት አለ ያንን ማሻሻል አለብን፡፡ ለአፍራሹ ኃይል ግን ያለኝ መልዕክት ተሽሎ መገኘት ብቻ ነው፤ ሌላ ምርጫ የለም፡፡ ውዥንብርና አሉባልታ ደግሞ ለጊዜው እንደጉም ቢሰበሰብም ሃቁ ሲጋለጥ በኖ መጥፋቱ ስለማይቀር ብዙም የሚያስጨንቀን ሊሆን አይገባም፡፡

NB:- እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.