ሰበር ዜና _ በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ መድሐኒያለም አካባቢ የተደራጁ ራሳቸውን ቄሮ ነን የሚሉ አካላት በአማራ ተወላጆች ቤት ላይ ድብደባ እየፈፀሙ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ስዓት አካባቢ ከስፍራው በስልክ የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በቦሌ ክ/ከተማ ቡልቡላ መድሀኒያለም አካባቢ በርካታ ቄሮዎች የአማራ ተወላጆችን ቤት ድንጋይ በመወርወር ድብደባ እየፈፀሙ በመሆኑ ከፍተኛ ጩኸት መኖሩ ተገልጧል።

ዘግይተውም ቢሆን የአካባቢ የፀጥታ አካላት እየደረሱ ቢሆንም ዋስትና እየሰጡን አይደለም በማለት የነገሩን ምንጮች የሚመለከተው የፀጥታ አካል ወደ ስፍራው ደርሶ የአካባቢውን ህዝብ ሰላምና ደህንነት እንዲያስከብር ጠይቀዋል።

ሌላኛው በቦሌ ክ/ከተማ ከቡልቡላ መድሀኒያለም ጨረቃ ሰፈር አካባቢ መረጃ ያደረሱን ምንጫችን እንደጠቆሙት ቄሮዎች የአማራ ቤትን እየመረጡ በድንጋይና በዱላ እየደበደቡ መሆኑን በመግለፅ ለጊዜው ፖሊሶች ደርሰው ሁለት ጥይት በመተኮስ ለመበተን እየሞከሩ እንደሚገኙና እሳቸውም ከቤታቸው ወጥተው ጫካ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ሌላኛው የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው ከትናንት ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 12 ስዓት ላይ በኦሮሚያ ፖሊሶች ከነ ቪትስ መኪናው የተወሰደው ሾፌር አዲስ ሙሉጌታ እስካሁን አድራሻው አልታወቀም ብለዋል።

ሌላ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ በፖሊሶች ታፍኖ የተወሰደ ሰው መኖሩን የገለፁት ምንጫችን ትናንት ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ብቻ የሚታወቁ 33 የአማራ ወጣቶች
ታስረው ከፍተኛ ድብደባ ከተፈፀመባቸው በኃላ 15ቱ ማታ ሲፈቱ 18ቱ የክፍለ ሀገር መታወቂያ ነው የያዛችሁት በሚል ከቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ ወደ ፍርድ ቤት መወሰዳቸውን ተናግረዋል።

ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ምስል ያለበት ቲሸርት ለብሳ የተገኘች ፈንታነሽ የተባለች የአማራ ወጣቶች ማህበር የጥቅምት 9 ስብሰባ ተሳታፊ በወረዳ 12 በሚገኙ ቄሮዎች ለብሷን ካስወለቁ በኃላ ድብደባ ፈፅመውባታል።

ጌታቸውና አምባው በተባሉ የአማራ ወጣቶች ላይም ሚስማር ባለበት ዱላና በድንጋይ ባደረሱባቸው ከፍተኛ ድብደባ ወደ ሆስፒታል መግባታቸውን ታማኝ ምንጮችን ዋቢ አድርገን መዘገባችን ይታወሳል።

3 thoughts on “ሰበር ዜና _ በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ መድሐኒያለም አካባቢ የተደራጁ ራሳቸውን ቄሮ ነን የሚሉ አካላት በአማራ ተወላጆች ቤት ላይ ድብደባ እየፈፀሙ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ

  1. Comment:
    amara betgrai woyaniena be oromo gentay budnoch lay zariewnu tornet megtm gd yilewal. Odp memetat alebet. Azmach lema megersa new. Redatochu shimels juawor ena dula nachew

  2. Comment:
    amara betgrai woyaniena be oromo gentay budnoch lay zariewnu tornet megtm gd yilewal. Odp memetat alebet. Yeoromon milishia qero yemil sm seto azmachu lema megersa new. Redatochu shimels juawor ena dula nachew

  3. ለማ መገርሳ እንደ እርግብ የዋ ብቻ የሆነው ሓይሌ ፊዳ አይደለም ። እንደ እባብም ልባም እንጂ ። የተግባባን መሰለኝ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.