ጃዋር እየዋሸ መሆኑን የተረዳሁት ከደቂቃዎች በፊት ከOMN ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ነው። ሰውየው ግርግር ፈልጓል (የትነበርክ ታደለ)

ጃዋር የፈለገው ይህንን ነው.. በአብይና በኦሮሞ ህዝብ መካከል እሳት መለኮስና አብይን ከስልጣን ማውረድ….

ጃዋር እየዋሸ መሆኑን የተረዳሁት ከደቂቃዎች በፊት ከOMN ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ነው። ሰውየው ግርግር ፈልጓል። በግርግሩ አብይን በደምብ ማስጠላት ይፈልጋል። ብዙ ጊዜ አይታችሁ ከሆነ ጃዋር በጣም በስሜት ካልተሞላ ሀሳቡን ማስተላለፍ አይችልም። እንደ ተማረ ሰው ተረጋግቶ ጥልቅ ህሳብ አመንጭቶ መናገር አይችልም። ስሜቱ መደበላለቅ አለበት፣ መጮህ ይፈልጋል። እንዲህ ላለው ጠባይ ደግሞ ግርግርና ሽብር መኖር አለበት።

ይህን ያልኩት ያለ ምክኒያት አይደለም። በቅድሙ ቃለ መጠይቅ ላይ ሲያወራ የነበረው ለሊት ላይ ተፈጠረ ስላለው የውሸት ትርክቱ ሳይሆን አብይ የኦሮሞን ህዝብ ክዷልና የራሳችንን እርምጃ መጀመር አለብን በማለት ህዝቡን ሲቀሰቅስ ነበር። ጸጉሩን እየነጨ፣ ፊቱን እየመታ፣ እስክሪፕቶ አስር ጊዜ እየወረወረ “ይሄ ትንሽ ሰው ትንሽ ሀሳብ ይዞ ኦሮሞን ሊያስተዳድር አይችልም። ኦሮሞ ታላቅ ህዝብ ነው ትልቅ ሰው ያስፈልገዋል። ይሄ አንዲት ክሊክ (የጣቱን ጥፍር እያሳየ) የምታክል ሰው በዚህ ህዝብ ላይ ልትጫወት አትችልም።.… አሁን ሄዶ ከነፍጠኛ ጋር ተወትፏል በነፍጠኞች ነው የሚመራው።

እኔ የፖለቲካ ሳይንቲስት ነኝ። ብዙ ነገር አውቃለሁ። ደርሶብኝም አይቸዋለሁ። ነፍጠኛን አምነህ መጓዝ ከፈለክ ገደል ትገባለህ። እኔ ከአመታት በፊት አብርያቸው ነበርኩ። ያኔ ኮቴን ይዘው ከኋላዬ እየተከተሉ ያጨበጭቡልኝ ነበር። አንድ ቀን በአልጀዚራ ቀርቤ “እኔ ኦርሞነቴ ይበልጥብኛል” ብዬ ስናገር ጥለውኝ ሸሽተው ጭራሽ ያጠቁኝ ጀመረ። አብይ አሁን የሚያጨበጭቡለት ሁሉ ኦሮሞዎች አይደሉም ነፍጠኞች ናቸው።

አንድ ቀን ግን ይክዱትና አውላላ ሜዳ ላይ ይጥሉታል። ለዚህ ነው መጀመርያ የኦሮሞን ኢንተረስት ማስቀደም የነበረበት። አሁን ያለው አካሄድ ኦሮሞን የናቀና የነፍጠኛን ስርዓት ለመመለስ የሚደረግ ጉዞ ነው።….በዚህ መንገድ ግን የሚሆነውን እናያለን (እዚህ ላይ ያለውን አልጻፍኩትም)……የኦሮሞ ትግል ተበልቷል፣ የኦሮሞ ወጣት ደም በአብይ ለነፍጠኛ ተሽጧል.…(ወዘተ)
እቺ ሀገር በነፍጠኞች ተሞክራለች አልጠቀማትም፣ በወያኔ ተሞክራለች አልጠቀማትም። እስኪ አሁን በኦሮሞ ትሞከርና ደግሞ ይታይ። እስኪ የኦሮሞ አስተዳድር፣ ባህልና ዴሞክራሲ በዚህች ሀገር ይሞከር…ይሄ ነበር መንገዱ….(እያለ ይቀጥላል))

ጃዋር የፈለገው ይህንን ነው። በአብይና በኦሮሞ ህዝብ መካከል እሳት መለኮስና አብይን ከስልጣን ማውረድ፣ በተለይ የኢህአዴግን ውህደት ብሎም የመደመርን ፍልስፍና ማኮላሸት።…ይህን ለማለት ደግሞ በተለመደው የቲቪ ኢንተርቬው ብዙ ተደራሽ እንደማይሆን ያውቀዋል። እናም በሶስት ደቂቃ ማንነቱ ካልታወቀ ሰው ጋር የስልክ ቃለ መጠይቅ ሽብር መንዛትና ቄሮን ማስነሳት።..…ሊገድሉኝ ነው፣ መጡብኝ፣ ተወረርኩ…እያሉ ማጓራት!!!

(የትነበርክ ታደለ)

3 COMMENTS

  1. እኔስ የገረመኝ ጋዜጠኛዉ ስንት ተከፍሎት ነዉ? እስኪ ከስሜነህ ብዙ ይማሩ በዋልታ ቴሌቪዥን ።

  2. Comment: juhar’s father was frmo yemen, as such he is a terrorist as binladen alqaida, he is an agent of egypt against ethiopia. We need to treat him as isis.
    The problem is that odp especially lema megersa and uula gemeda are behind him.

  3. Comment: juhar’s father was from yemen, as such he is a terrorist as binladen alqaida, he is an agent of egypt against ethiopia. We need to treat him as isis.
    The problem is that odp especially lema megersa and dula gemeda are behind him.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.