በተከሰተው ሁከት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በጥፋቱ ተሣታፊ የሆኑ ሰዎች በሕግ ተጠያቂነታቸው መረጋገጥ አለበት” የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

በተከሰተው ሁከት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በጥፋቱ ተሣታፊ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በሕግ ተጠያቂነታቸው መረጋገጥ እንዳለበት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ በወቅታዊ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል፤ የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

በወቅታዊ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ

በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ እና ተሃድሶ እርምጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ተጨባጭ ውጤቶች እንዳስገኘ ሁሉ ውስብስብ ተግዳሮቶችም እየገጠሙት ይገኛል፡፡ በተለይ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በተቀሰቀሰው ውዝግብ እና ሁከት የተሞላ ነውጥ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ከመጥፋቱ፣ የአካል ጉዳት ከመድረሱ፣ ንብረት ከመውደሙ እና የሰዎች መደበኛ ኑሮ እና ሰላማዊ ሕይወት ከመረበሹ በተጨማሪ፤ የህግ በላይነትን በእጅጉ የተፈታተነ እና መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶችን ከፍተኛ አደጋ እና ስጋት ላይ የጣለ እጅግ አሳሳቢ ክስተት ነበር፡፡

በዚህ ሁከት ምክንያት ከሚዲያዎች ዘገባ መሰረት እስከ አሁን ባለው መረጃ ከ70 – 80 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አስር ያህሉ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት በጥይት ተመተው የሞቱ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሰዎች በሁከቱ ተሳተፉ ሰዎች እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ በግፍ እና ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በዱላ በድንጋይ እና በስለት ተደብድበው እንዲሁም በእሳት ተቃጥለው ተገድለዋል፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ የአካል እና የሥነ ልቦና ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በሚሊዮኖች የሚገመት የግለሰቦች፣ የሕዝብና የአገር ንብረት ወድሟል፡፡ እንዲሁም የሃይማኖት ተቋማት ሆን ተብሎ በተፈጸመ ጥቃት ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡

አሁን ባለው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ማናቸውም ዓይነት ቅሬታ ወይም ጥያቄ በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ሊቀርብ የሚችልበት ምቹ ሁኔታ መኖሩ ይታመናል፡፡ ለዚህ ውዝግብ መነሻ በሆነው ጉዳይ ላይ በሰላማዊ መንገድ ሃሳባቸውን ለመግለጽ የሚሹ ሰዎች ቢኖሩም ሁከት የቀሰቀሱ፣ የፈጸሙ እና ያስፈጸሙ እንዲሁም ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ድጋፍ የሰጡ ሰዎች መኖራቸው ግን አይካድም፡፡

ማናቸውንም ዓይነት ቅሬታና ጥያቄ በአመፅ እና በእልቂት ማስፈራሪያ ለማስፈፀም የታየው ተግባር እና የአስከተለው ጉዳት የሕግ የበላይነትን፣ የአገር ሰላም እና ሥርዓትን በአደባባይ በመገዳደር እና በመጣስ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ቀውስ ያስከተለ በመሆኑ በየደረጃው በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ በጥፋቱ ተሣታፊ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በሕግ ተጠያቂነታቸው መረጋገጥ አለበት፡፡

ይህን ጥፋት የፈፀሙ እና ወይም የጥፋቱን ተግባር እንደ መልካም ሥራ ያወደሱ ሰዎች ሁሉ በዱላ እና በስለት ተደብድበው በእሳት ተቃጥለው የተገደሉ ሰዎችና ቤተሰቦቻቸውን ለአፍታ እንኳን በእራሣቸውና በቤተሰቦቻቸው ተክተው አለማሰባቸው የደረሰውን ጉዳት ይበልጥ መሪር አድርጐታል፡፡ የድርጊቱ ተሳታፊዎች በደረሰው ጥፋት ማዘን መፀፀት እና ለሕግ የበላይነት መከበር የመተባበር ኃላፊነት እና ግዴታ አለባቸው፡፡

መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና አጥፊዎችን በሕግ ፊት ለማቅረብ ሳያወላውል እንደሚሠራ መግለጹ ተገቢ ሲሆን፤ ይህ የመንግስት ኃላፊነት እና ተግባር በስልታዊ የምርመራ ሥራ እና በሕጋዊ ሥርዓት በአፋጣኝ በሥራ ላይ ሊውል ይገባል፡፡
ከዚህ በመቀጠል ለሚደረገው የወንጀል ምርመራ ሥራ ማንኛውም ሰው በመተባበር እና ውጤቱን በትዕግስት በመጠባበቅ፣ በየአካባቢው የተጐዱ ሰዎችንና ቤተሰቦችን በማጽናናት በመደገፍ እና በመጠገን፤ እንዲሁም የመንግሥት፣ የፖለቲካ እና የልዩ ልዩ ቡድኖች መሪዎች የፖለቲካ ውጥረቱን ከሚያባብሱ ቆስቋሽ ንግግሮች እና ድርጊቶች እራሳቸውን በመቆጠብ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን እና ሰብዓዊ መብቶች ሁሉ እንዲከበሩ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ እና ይህን የመሰለ ጥፋት ዳግም እንዳይፈጸም የሚመለከታቸው አካሎች ሁሎ በከፍተኛ ኃላፊነት ስሜት ሊሰሩ ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
ጥቅምት 18 ቀን 2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ

2 COMMENTS

  1. ህግ እንዲያስከበር ሃላፊነት የተሰጠው መለዪ ለብሶ በፌደራልና በክልል የተደራጀው እኮ ነው የዘረፋውና የወንጀሉ ተባባሪ። እንዴት አድርጎ ነው ቀበሮን የደሮ ጠባቂ ማድረግ የሚቻለው? እየሰማንና እያየን ያለነው በኦሮሞነት ስም ሌላውን ወገን የማጥቃትና የማሰቃየት ዘመቻ ነው። ጠ/ሚሩ እልፍ ከሆነው አንድ ዲስኩራቸው ላይ ” ኦሮሞ ሲገዛ ነው አሁን አይሆንም የምትሉት? ኦሮሞ ማስተዳደር አይችልም ማለት ነው?” በማለት ስላቂያዊ ጥያቄ አንስተው ነበር። እንዴ በግልጽ እኮ ጠ/ሚሩን የኦሮሞን ህዝብ አይወክልም፤ የአማራ ቅጥረኛ ነው። እንዲያውም እንደ ጫቱ ፕሮፌሰር ህዝቄል ያለው ደግሞ ጭራሹኑ ኦዴፓ የኦሮሞ ህዝብ የሚወክል ድርጅት አይደለም እያሉን ነው። እጅግ የገማ አስተሳሰብ ያላቸው የኦሮሞ ጽንፈኞች ደግሞ አማራ ሚስቱን አቅፎ እያደረ ለኦሮሞ ህዝብ ማሰብ አይችልም ነው የሚሉን። ወያኔን በዘዴ አሽቀንጥረው ኦሮሞዎቹ የጊዜው አለቃ ከሆኑ ወዲህ በአፋቸው ማር እያዘነቡ ሥራቸው ጽልመታዊ መሆኑን የየቀኑ ድርጊታቸው ያሳየናል። መንገድ መዝጋት፤ በአዲስ አበባ ኮንዶሚኒየም ለአመታት ጠብቀውና ገንዘብ አጠራቅመው የደረሳቸውን አትገቡም በማለት ለኦሮሞ ሚዲያና ለሌሎች ማከፋፈል፤ በጎሃጽዪን መንገድ በመዝጋት ሰው ወደ አሰበው እንዳይደርስ ማድረግ። ለከፍተኛ ትምህርት ተቋሟት ጉዞ የጀመሩ በመንገዱ መዘጋት ዘግይተው ሲደርሱ የመመዝገቢያ ጊዜው አልፏል ወደ መጣችሁበት ተመለሱ እየተባሉ ስንቶች በረንዳ አዳሪ ሆነዋል። በከፋ መልኩ የሰው አንገት እንደ እንስሳ የሚቆርጥ የእብድ ስብስብ በምድሪቱ ላይ ሲራወጥ እያየን ነው። በኦሮሞ ነጻነት ፈላጊዎች ምክንያት በምድሪቱ በፊትም ሆነ ዛሬ የሚሰራው ግፍ ሰማይ ደርሷል። መሪ የለም። ህግ አስከባሪ የለም። የብቀላን ፓለቲካ ሌላ የዘረኞች በቃይ ቡድን ተክቶታል። እስኪ በቅርቡ ከአዲስ አበባ ፓሊስ እስር ቤት ከ 40 ቀናት እስራት በህዋላ የተፈቱት የተናገሩትን አዳምጡ። ህግ አለ በምድሪቱ? ለውጥ አለ በሃገሪቱ? ትላንትም ስቃይ ዛሬም ሰቆቃ። የኦሮሞ ፓለቲከኞች ሰላም ሰላም ቢሉ ምንም አያምናቸውም። ውሸት ነው። የእነርሱ ጠላት ያው ወያኔና ሻቢያ ለዘመናት ሲለፉት እንደነበረው ሁሉ አማራና የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ናቸው። ሁለቱን ማጥፋት ለእነርሱ አማራጭ የለውም። ጥላቸው አሁን በመሬት ላይ ካለው ነገር ሳይሆን በፈጠራ ታሪክ ላይ ነው። የኦሮሞ ፓለቲከኞች የሚፈልጉት አንድ ነገር ብቻ ነው። ሃገርን መገነጣጠል። ኦሮሚያን መፍጠር እና በዚያው የህልም ዓለም ውስጥ መኖር። ለዚህ ተግባራቸው ገና ብዙ ሃበሳ በህዝባችን ላይ ያደርሳሉ።
    ጠ/ሚሩና በዙሪያቸው ያሉ የኦሮሞ ባለስልጣኖች ጭራሽ በሃሳብ አይስማሙም። ጠ/ሚሩ የሚያቀርቡትን ሃሳብ የሚያጣጥሉ፤ አንድ ትዕዛዝ ሲሰጥ የማያስፈጽሙ ናቸው። ዶ/ር አብይ በሚስቱ ምክንያት ኦሮሞ አይደለም። ለኦሮሞ ህዝብ አያስብም ብለው የሚከራከሩ ሙሁራን ያሉበት የፓለቲካ አሻሮ ነው የኦሮሞ ብሄርተኝነት። አሁን በቅርቡም በጃዋር ኡኡታ ተንጋግቶ የወጣው ሰው ለኦሮሞ በአዲስ አበባ መሬት እየታደለ ነው ተብሎ ከየስፍራው በመኪና እየተጫነ የመጣ ነው። ለዚህም አቀናባሪዎች አሉት። ዋናው የግርግሩ መንስኤ ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩን የኖቬል ሽልማት ለማጠልሸትና አይገባውም የሚለውን የኦሮሞና የወያኔ ሃሳብ ለማጠናከር ነው። የምቀኞች ምድር! ሰው በከፍታ ማማ ላይ ቆሞ ሲታይ እሳት ከሥር የሚያነድ የጉድ ትውልድ። ታዲያ ለኦሮሞ ቆንጨራና ጠበንጃ አንጋች ግርግር መፍትሄ ራስን ማስታጠቅና መከላከል እንጂ ፍትህ አለ ብሎ እጅ መስጠት እንደ ከብት ያሳርዳል። ይህን ሁሉ መከራ እያደረሱ ለቅሞ እንደመያዝ ሁሌ ጡጦ እየሰጡ ዝም በሉ ማለቱ ጭራሽ ተገቢነት የለውም። የወገኖቻችን አስከሬን ገና ተሰብስቦ አፈር ሳይመለስበት ጃዋር ሰንጋ ጥሎ ህዝቡን ያበላበት ቀን ነው። እንዴት የሰው ልጅ ምግቡ ይዋጥለታል? ጃዋርስ እንዴት ቆሞ ይሄዳል? ግን የወረፋ ፓለቲካ አይደል ጊዜው የእነርሱ ነው። ቀን ሲገለበጥ ጃዋርን አያርገኝ። መኖሪያ የለውም። በሰው ደም እየታጠበ። አጥፊዎቹ በህግ እንዲጠየቁ መጠየቁ መልካም ነው። ግን እኮ የኦሮሞ ፓሊስ እየለቀመ ያለው የወደቀ ሰው ያነሱትን፤ ተው በማለት ግርግሩን ያስቆሙትን እንጂ ሰው ዘቅዝቀው የሚሰቅሉትና የሰውን አንገት የሚቀሉትን አይደለም። መፍትሄው ራስን ከጥቃት እየተከላከሉ መሞት ነው። ሌላው ሁሉ የማይሳካ ተስፋ ነው። ሃገር በዘር ተሰምራ ፓሊሱ መታወቂያ አይቶና ዘሩን ተረድቶ ጥቃት በሚያደርስባት ምድር ላይ የዜግነት መብት አለኝ ብሎ መቆም በግ መሆን ነው። አይሰራም!

  2. Comment: Comment:
    abiy oromo yalhonutn etiopiyawiyan yemiardut asheberi yeoromo budnoch tebabari slehone sltan yilqeq.
    Alemaqef yewenjelegnoch frdbiet yeetiopian guday yimermr.
    Yetebaberut mengstat beetiopia wetader yasemara.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.