የዶ/ር አቢይ ምርጫ – ኢትዮጵያ ወይም ሞት (ከአባዊርቱ)

ይህን ጉዳይ እንደዋዛ መመልከት ዋጋ ያስከፍላል። እስካሁን በታላቅ እምነትና ጽናት የአቢይን መደመር ፍልስፍና ከልብ በመቀበል አብረን ቆመናል። ለአገር ስንልም ነው። እኔ በተወለድኩበት ዘመን የዚህ ጎሳ የዚያ ጎሳ ሳንባባል ለአንዲት አረንጉዋዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ቆስለናል፣ ሞተናልም። የማውቃት ኢትዮጵያ ገጽታዋ እንደ ዛሬ ሳይጠፋ፣ የአማራውም፣ የኩሎውም፣ የቤንሻንጉሉም፣ የዖሮሞውም ጥቃት የራሴ ነው  እያልን ነግበኔ እንዲሉ በጽናት ኖረናል። ዛሬ እነዚህ ከሀድያን ወያኔዎች ባመጡብን ጣጣ እንኩዋንስ ስለ ሌላው ነገድ ማውራትና መፋለም ቀርቶ፣ ስለየራሳችንም በቅጡ መፋለም እስኪያዳግተን ድረስ የዱርዬዎችና ጥጋበኞች መፈንጫ ሆነናል። ስዩም ተሾመ ያነሳው ጉዳይ አይምሮን ይኮረኩራል። እውነት ነው፣ አቢይ አህመድ እውነት እንደሚያወሩት የኢትዮጵያ ጉዳይ ይበልጥቦት ከሆነ፣ ይህን ጁዋር ተብዬን ሆነ “እማድቤትዎ” ሆነው ኢትዮጵያን ሊያማስሉልን የተወተፉትን ከሀድያን ወጥ አማሳዮች ባደባባይ ያጋልጡና የወታደር ሞት ይሙቱ። የኢትዮጵያ አምላክ ከሰኔ 16ቱም መአት ፣ ያውም ከ መጥፎ አሙዋማት አትርፎዋታልና፣ ለዚያውም ያኔ ገና  ምንም ሳይሰሩ አሁንም ይታደጎታል። ባይሳካልዎ እንኩዋ ኢትዮጵያን መታደጉ ስምዎ በወርቅ ተጽፎ እነዲቦራ ዝንተአለም እየተወደሱ ይኖራሉ። ይህው ነው። ዛሬ ቀናትን ወስዶ በትእግስት በስብሰባና በምልጃ የሚሆን ጉዳይ አይደለም። ቁርጥ ያለ በቲቪ ዳይሬክቲቭ የሚሰጡበት ወቅት ላይ ነን።
አቢይ ሆይ!
ምን ይምጣ ከዚህ በላይ? ባለፈው እስክንድርን የኮነነው ተጻራሪ ባላደራ መንግስት አቅዶ ነው በነታከለ ላይ ብለን ቁምስቅሉን ስናሳየው አልነበረም? ያውም የመናገሻ ከተማ ተጻራሪ? ዛሬ ይህ ጁዋር የሚሉት ወሮበላ ተጻራሪ የኢትዮጵያ መንግስት ነኝ እያለም አይደለም እንዴ እጉያዎ ስር ቁጭ ብሎ፣? እንዴት ይህ ሊሆን ይችላል? ደሞስ እነሺመልስ አብዲሳ “ወንድሜን የነካ እኔን ነካ ” አይነት መላ የሌለው አነጋገር ካንድ ክፍለሀገር አስተዳዳሪ እንደምን ተፈቀደለት? አይናችን፣ ጆሯችን እያየና እየሰማ እንደምን ጠቅላይ አቃቤህግ ይህን ሰው ሊያሞካሽ ይዳዳዋል? እንዴት ነው ነገሩ? በግፍ ያለቁት ጋሞዎች፣ አማሮች ዖሮሞዎች ወገን አይደሉምን? ወይስ ምን የሚሉት ነው የርሶ ዝምታ? አብረዎት የሚቆሙና የሚሰዉ ሚሊዮኖች ህዝብና የቀድሞ ወታደሮች አለን እኮ። አንዳንዶቻችን ጉልበቱ እንኩዋ ቢዝል ጽናቱና አይምሯችን እንዳልዛለ ላረጋግጥልዎ እወዳለሁ። ገና ለገና ብተነፍስ ብዙ ሰው አስጨርሳለሁ ብለው ሰግተው ከሆነ አሁንም እያለቀ ነው ሰው፣ ለነገሩ አንድም ይሁን ሺህ በስጋ ከሚሞተው በስጋትና ጭንቀት ከሚሞተው ሚሊዮን ህዝብ አይሻልምና ቁርጥ ያለ መመርያ እንጠብቃለን። ለመሆኑ  ይህ በዖሮምያ እየዞሩ ምክክር ምን የሚሉት ነው? ወቅቱም አይደለም። እነዚህ በግልጽ “አቢይ ነፍጠኛ፣ ” እያለ ዱላ የሚያቀባብልሎት ነገ ምን እንደደገሰልዎ መረዳቱ አይከብድም። ስለሆነም መፍትሄ የሚሆነውን ልምከርዎ ፣ መቼስ መካሪዎ በዛና እያስጨነቀኝም ቢሆን፣ ለነገሩ ለራሴው ጤንነት ከመስጋትም ነው።
፩) ይለይለት፣ አዎ ይለይለት። ከ ፣28 አመታት በሁዋላ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አርገዋልና ለይቶ ከኢትዮጵያ ጋር በግልጽ ለይተው ይውጡ። እንዴት? ደቡብን፣ ሙስጠፌን፣ አፋሮችን፣ ጋምቤላዎችን፣ አማሮቹን ይዘው የጨቀየውን ኢሀዴግን እርግፍ አርገው ቀድመው ያሰቡትን “አንድነት ሀይል”  ፓርቲ በፍጥነት ያቁዋቁሙ። በግልጽ ወያኔን በአደባባይ ያሰናብቱ። ሀቀኞቹን የትግራይ ልጆች ያካትቱ። ከዚህ ቀደምም ብዬ ነበር። ወያኔዎቹ የ አልትራ ኮንሰርቨቲቭ ፓርቲአቸውን ታቅፈው እዛው ሰሜን ይቀመጡ። በሳቴላይት ሸንጎ ይሳተፉ። ዳግም ወደመሃል አገር ድርሽ እንዳይሉ ብቻ።
፪) ኦዴፓን ከዖነግ አጸዳለሁ ብለው በጭራሽ አያስቡ። አይሆንም ። ያ ጉዳይ የሞተው ለማ መከላከያ የገቡ ቀን ነው። ይህ ሽመልስ የሚሉት ልጅ ልቡ ሸፍቱዋል በነ ጁዋር ቱልቱላ። መስሎት ነው እንጂ ዖሮምያ ብሎ ሀገር ዘበት ነው። ዖሮምያ ያለችው በነ ጁዋርና ጭፍሮቹ፣ በነ ዳውድና መሰሎቹ  አይምሮ እንጂ በዖሮምያ ምድር ውስጥ የሚኖር እንኩዋንስ ሌላው ወገን ቀርቶ ከአብራኩ የወጣሁት ደሀ ዖሮሞ ህሊና ውስጥ የለችም። እነዚህ ተማርን  ባይ “የምሁራን” ነውጠኞች ይቺን ሀቅ አጥተውት ሳይሆን እርስዎን ጥላሸት ለመቀባትና አቅጣጫዎን ሊያስቱ ነው። ጁዋር ቦዘኔን ፍሪዳ እያበላ ያውም ያስገደላቸው ምስኪኖች አፈር ሳይለብሱ አልጀዚራን ስለራሱ ገናናነት እንዳስወራ አልሰሙ ይሆን? አፈላልገው ይስሙት
፫) ትግስታችን ተሙዋጡዋል ብለው እንዳይሉ ከእንግዲህ አደራ። ከተሙዋጠጠ ሰንበትበት ብሏልና። ቆራጥ እርምጃ ይውሰዱ። በቃ
፬) ግድየሎትም የቀድሞ መኮንኖችን ያማክሩ። እነ እከሌ ብዬ ባደባባይ ባልነግሮትም አይጠፋዎትም።
በመጨረሻ፣ ሁሌም የሚጠሩት የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳዎ። ቀናውንም ያሳይዎ። አንዱ የዖነግ አንጋች “የኢትዮጵያ አምላክ የምትለው የተለየ ነው እንዴ የኢትዮጵያ?” ብሎኝም ነበር። የኢትዮጵያ ታሪክ 150 አመታት ብቻ ነው ብሎ ለተጋተን ገልቱ ሌላ ምንስ ሊያውቅ  ይችላል? ሌላው ቢቀር የልብ ልብ የሰጡዋቸው ሰላቶዎች እንኩዋ ያመኑት በትንሹዋ ፩ ሺህ አመት ሀገረ እግዚአብሄር መሆኑዋን  አላጤኑትም። ይህ ኢትዮጵያን ከውስጥ የማፍረስ ሴራም ይከሽፋል። ይብላኝ ለልጆቻቸው ምን አውርሰው እንደሚሰናበቱ። ማፈርያ ሁላ።
አባዊርቱ ነኝ
የቀድሞው መኮንን፣ ዛሬም በተጠንቀቅ ያለ
“መለዮ”! ብያለሁ ኮለኔል አቢይ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.