ሁለተኛው “ጠቅላይ ሚኒስትር” ጃዋር መሐመድ ወይም አቡባካር አል-ባግህዳዲ ለፍርድ እንዳይቀርብ!

ለፍርድ መቅረብ ያለባቸው ጃዋር መሐመድና የጥፋት አጋሮቹ ኦነጋውያን ሣይሆኑ በነርሱ ትዕዛዝ የተገደሉ የንፁሃኑ ቤተሰቦች ናቸው። ሟቾች ለገዳዮቹም ካሣ መክፈል አለባቸው። በእንሠሶች እርሻና በእንሠሦች የመግባቢያ ሠነድ የምንዳኝበት የእንሠሦች ዐመፅ ሐገረ – ኢትዮጵያ ውስጥ እየተተገበረ በመሆኑ የመንግስት ቅርፃችን “የጎሣ ፌደራሊዝም””፣ ርዕዮቱ የጎሣ ፓለቲካ ሕጋዊ መስፈርታቸው ‘ወንጀልን በማመሳሰል መቅጣት’ እና ‘የዝምድና የጅምላ ቅጣት’ (‘Crime by Asdociation & Kin Punishment’) ይፈቅዳሉና!

ሕገ – ወጥነት ሕግን ሽሮ ሥርዓተ-አልበኝነት “ሕግ” ሲሆንና ሕግ አስፈፃሚዎችና አስከባሪዎች ከሕገ-ወጥ ነብሰገዳዮች ማለትም ከነጃዋር መሐመድ ጋር በፍቅር ሲወድቁና (Stockholm Syndrome) ፍትህ ለንፁሃን ሲነፈግ ባየን ጊዜ ወንጀለኛ ነብሰገዳዮችን ለቀው ንፁሃን ተጠቂ ዜጎችን “ለፍርድ” እንዲያቀርቡ መጠየቅ ጀመርን!

‘ሁሉም እንሠሦች እኩል ናቸው። አንዳንዶቹ እንሠሦች ከሌሎቹ የበለጠ እኩልነት አላቸው’! ጃዋርና ኦነጋውያንም እንደዚሁ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.