የ ጀሃዲስት ጃዋር ሞሃመድ እና የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሚስጥሩ ምንድን ነው?

በሚገርም ሁኔታ ጭንቅላቴ ላይ የሚመላለስው ጥያቄ እና መልስ ያጣሁለት ጃዋር የሚባለውን ግለሰብ ጠ/ሚው እንደሚሰበር ብርጭቆ በእንክብካቤ ሊይዝ የቻለበት ምክንያት እና እስክንድር ሰላማዊ ትግል እንዳያደርግ እግር በእግር እየተከታተለ እሚያደናቅፍበት ምክንያት ነው።

ትእግስት እስከምን ድረስ ነው? ምንም በማያጠራጥር መልኩ አሁን ያለው ጠ/ሚ የራሱን ገፅታ እየገነባ ነው። ህዝብ እንደ ቅጠል እየረገፈ ፣ ሰው ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ መስራት የህልም ቅዠት እየሆነ ፣ በምትኖርበት ክልል የራስህን ሃይማኖት ማምለክ አለመቻል ደረጃ ከደረስክ መሪ የለም ማለት ነው።

ለህዝብ የሚጨነቅ አመራር ለውጥ የተባለው ድራማ መስመሩን በሳተበት ማግስት የማያዳግም እርምጃ ይወስድ ነበር this is a fact. አንድ ተራ አክቲቪስት እንደ ባለስልጣን እየጠበክ እና ከለላ እያረክ ተራው ንፁህ ግለሰብ ሲሞት እሱን ሰበብ እያረክ የሰላም ኮንፈረንስ እና መግለጫ በሚል እርባና ቢስ ነገር በጀቱን ምትፈጀው ከሆነ ለህዝቡ አልቆምክም ስለዚህ የራስህን ገፅታ መገንባት ላይ ነህ ብለን እንደመድማለን። እና ሰውየው እንደሞዴሊስት አተዘዋወርክ ፎቶ መነሳትህን አቁም እና እርምጃ ውሰድ ለህዝቡ አትጨነቅ ግን እንደው ለራስህ በጣም ስለምትጨነቅ ልምከርህ ዛሬ ዝም ብለህ ያለፍከው እሳት ነገ እራስህን ያቃጥልሃል።

ይሄ ፖስት በሰውየው ፍቅር ለተቃጠላችሁት አይመለከትም ይለፋችሁ።
#Not_my_PM

2 COMMENTS

 1. ይህን “ምስጢር” ለመረዳት በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ፍቅር መንደድን ይጠይቃል ይመስለኛል። ሁሉ ጠያቂ ከሆነ፣ ሁሉ ፈራጅ ከሆነና መፍትሄውን እኛው ካላመጣን ጠ/ሚሩ እኮ ባለው ሁኔታ መፍትሄ ያሉትን እየተገበሩ መሰለኝ። እንደኔ ሁሉም የኢትዮጵያ ጉዳይ እንቅልፍ የነሳው ሁሉ ፣
  መፍትሄ ፩
  መፍትሄ ፪
  መፍትሄ ፫
  እያለ ያቅርብ። እንኩዋንስ አይምሮው የሚሰራ ጤናው ወገን እነወያኔም በዚች ሰአትና ደቂቃ በጠ/ሚሩ ፍቅር የሚነድ ሰው እንደሌለ አውቀውት በኢሞሽናችን እየተጫወቱ ነው። ለዚህም ነው ከአንጋቾቻቸው ዖነጎች ጋር ሆነው ሰውዬውን ከህዝብ የባሰ ሪፍቱን እያሰፉልን ያሉት። እንደምን ይህን ማየት አቃታችሁ ወገኖች? ከአንድ ታዬ ደንደአ በቀር ከኦዲፓ ይህን ጁዋርን ባደባባይ ያወገዘ ሰምታችሁዋል? አንድም አልሰማሁም። እናም እንኩዋን ከሌላው ወገን ከራሳቸውም በፍቅር የነደደ አለመኖሩን አመላካች ነው። ምናለ ሰውዬው የሆነ እማይፈራገጡበት ቅርቃር ገብተዋል ብለን በበጎ አስበን ሆነም አልሆነም የሚወጡበትን መንገዱን ብናሳያቸው? በጣም ከጠላናቸው ደሞ፣ የሰሞኑ ስራቸውም የሚያስወድድም የለውምና፣ የባሰ ባናቀጣጥለው እሳቱን ለማለት ነው።

 2. ምስጢሩ ቀላል ነው፣
  ጃዋር ነባራዊውን የፖሊቲካ ሂደት በሳይንሳዊ መንገድ ይተነትናል። ሳይንሳዊ ትንታኔ ደግሞ ተፈጥሮአዊ እና ህብረተሰባዊ ህግጋት እና ትስስሮችን መርምሮና ጨምቆ ማውጣትን ይጠይቃል። ይህ ደግሞ ምሁራዊ ችሎታ የሚጠይቅና ተፈጥሮ ለሰው ልጆች የለገሰችውን የማሰብ ነጻነትን ያለገደብ መጠቀምን የሚያካትት ነው። ስለሆነም ነው የማሰብ ነጻነት በማንኛውም ህግ የማይገደብ የሰው ልጆች መሰረታዊ መብት ነው የሚባለው፣ ከገባችሁ!
  እንግዲህ፣ ጃዋር ሞሃመድን ‘ስቀሉት፣ ግረፉት’ የምትሉት የአዕምሮውን የማሰብ ችሎታና የመናገር መብቱን ስለተጠቀመ ነው። ይህ ደግሞ በዛሬ ጊዜ የሚያስከስሰውና የሚያሰቅለው በመካከለኛው ክፍለ ዘመን (13ኛው መ ክ ዘ) አስተሳሰብ ላይ ደርቀው በቀሩት ‘ሃበሻ’ ወይም በፈረንጆቹ Abyssinia በሚትባል የፊውዳል ቅሪቶች በበዙባት ሃገር ብቻ ነው! ያኔ እነ ጋሊልዖ ጋለሊ በጥናት ደርሰውበት፣ ምድራችን የዩኒቨርሱ ማዕከል አይደለችም ስላሉ በቄሶች እንደተከሰሱት ማለት ነው።
  በዚያ ጎን፣ የናንተው ሊቀ ሊቃናት እስክንድር፣ ምንም ሳይንሳዊም ሆነ መለኮታዊ ምክንያት ሳያቀርብ፣ “የአዲስ አበቤዎች ንጉሥና አፈቀላጤም እኔ ነኝ፣ ከኔ ሌላ ለማንም አትታዘዙ” የሚል ነው። ይህ ደግሞ፣ ምንም እንኳ በስም ፌደራላዊ በሆነችና 7ኛው ንጉሠ ነገስት በ9 ክልሎች ከፋፍሎ ጠቅላይ እንደራሴዎችን በዘፈቀደ በሚሾምባት ሃገር እኔም ንጉሥ ልሁን የሚል መነሳቱ የማይቀር ቢሆንም፣ ለጊዜው ፍጹማዊውን ንጉሡን መዳፈር ስለሆነ ቦታ አይኖረውም!
  ባጭሩ፣ ሁለቱ፣ ማለትም ጃዋርና እስክንድር በሁለት የተለያዩ ክፍለ ዘመናት አስተሳሰብ ውስጥ ያሉ ስለሆነ ማነጻጸር አይቻልም። ባይሆን፣ ከ13ኛ መቶ ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ ራሳችሁን በፍጥነት ለማላቀቅ ይቻላችሁ ዘንድ፣ ተፈጥሮ/አምላክ የለገሳችሁን የማስተዋልና የማመዛዘን ችሎታ ካለ መርምራችሁ ግማሹን እንኳ እንድትጠቀሙበት በጽኑ እመክራለሁ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.