አቶ ክርስቲያን ታደለ ጨምሮ በሌሎች የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)አባላትና አመራሮች ላይ የቅድመ ክስ ምርመራ የምስክሮችን ቃል ለመስማት ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠ

አማራ ሚዲያ ማዕከል /አሚማ
ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

ከሰኔ 15ቱ የአማራ ሕዝብ መሪዎች እና የአገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮነኖች ላይ ከተፈፀመው ግድያ ጋር በተያያዘ ጠርጥሬያቸዋለሁ በሚል በፖሊስ ተይዘው ላለፉት ከአራት ወራት በላይ በእስር ላይ የሚገኙትና ሌሎች የፓለቲከኛና የኅሊና እስረኞች ሲፈቱ አቃቤ ህግ እንድትፈቱ አልፈረመም በሚል ሳይፈቱ የቀሩት፦
️1ኛ) ክርስቲያን ታደለ የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
️2ኛ) በለጠ ካሳ የአብን ፅሕፈት ቤት ኃላፊ
3ኛ) አስጠራው ከበደ የአብን አባል
️4ኛ) ሲሳይ አልታሰብ የአብን ብሔራዊ ም/ቤት አባል
5ኛ) ፋንታሁን ሞላ የአብን አባል
6ኛ) አማረ ካሴ የአብን የአዲስ አበባ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
7ኛ) አየለ አስማረ የአብን አባል
ቅድመ ምርመራ ክስ ተከፍቶባቸው ዛሬ ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ምየፌድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር።

በዛሬው ችሎት አቃቤ ሕግ የቅድመ ክስ ምርመራ የምስክሮችን ቃል ለማሰማት የነበረ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ከመደበኛ ክስ በፊት የቅድመ ክስ ምርመራ ምስክሮችን መሰማት ተቃውመው ክርክር አድርገዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ የቅድመ ክስ ምርመራ ምስክሮች ሊሰሙ አይገባም የሚለውን ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው በኩል ያቀረቡትን ተቃውሞ ውድቅ በማድረግ ምስክሮችን ለመስማት ለመጭው ረዕቡ ማለትም ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።

መረጃው የፍኖተ አብን ነው።

1 COMMENT

  1. Comment:
    shibr fetari yeoromo shumoch ena onegoch, tgrie woyanien chemro maygenagn mkniyat fetro amaran matqatun tenkrew eyeserubet mehonun yih kebeqi belay mereja new.
    Amara bertteh enezihn telatochihn demss.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.