ከክርስቲያን ታደለ (ገብርዬ)!! ከግፈኞች እገታ!! (ከእስር ቤት የተላከ መልዕክት)

ብቸኛዉ መፍትሄ ህዝባዊ እምቢተኝነት ስለመሆኑ ፤ይድረስ ለታላቁ የአማራ ህዝብ በሙሉ፤ይድረስ የወያኔን ጥይት ከቄጠማ ቆጥራችሁ ጉርንቦ ለጉርንቦ ተናንቃችሁ የተስፋ ጭላንጭል እና እፎይታ ለኢትዮጵያ ህዝብ እፎይታ ላስገኛችሁ የአማራ ወጣቶ፤
ይደረስ የአገዛዙን የአፓርታይዳዊ ገመና በማጋለጥ የስርዓቱን እርቃን ላስቀራችሁ የአማራ አክቲቪስቶች፤ ይድረስ የህዝባን ጥቃት እንደሬት ለሚመራችሁ፤ ‘’እራስን ከጥቃት መከላከል ተፈጥሮአዊ መብት ነዉ” በሚል መርህ ለምትንቀሳቀሱ የአማራ ፋኖ፤ ይድረስ ለዓማራ የጸጥታ አካላት በሙሉ፤ይድረስ ለአብን አባላት፤ይድረስ የአማራን ህዝብ ነፃ ለማዉጣት ለተደራጃችሁ የአማራ ወጣት ማህበር፤ ይድረስ የአማራነት ብኩርናችሁን በምስር ላልሸጣችሁ በየደረጃዉ ለምትገኙ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፤በዉርደት እና ግዞት ዉስጥ ሰላም እና ደህንነት፤ ክብርና ሞገስ የሉም እና እንዴት ናችሁ ሰላማችሁስ እንዴት ባጀ አልላችሁም፡፡

አስቀድመን እንደተናገርነዉ በወንድሞቻችን ሞት ባራሳችን ሀዘን ድንኳን የፖለቲካ ዝሙት በመፈጸም እንደህዝብ ክብራችንን ዝቅ የሚያደርግ ነዉረኛ ድሪጊት መንግስት የመሆን ኃላፍነት በዉል ባላወቁና በልጠነቀቁ መንጋዎች እየተፈጸመብን ይገኛል፡፡ በምርመራ ሰበብ አማራነታችንን እየጠቀሱ እጅግ አሰነዋሪ እና አሳፋሪ ነገሮች ተብለናል፡፡ እንኳንስ እኛን ሰዎችን “የአማራ መኪና ምኑ ይታመናል፤ገነጣጥላችሁ ፈትሹት“ እስከመባልም የደረሰ ሥርዓት የለሽ በደልን አስተናግደናል፡፡

በሚሊዮን ዶላር ወጭ ወጥቶባቸዉ የሰለጠኑ የመንግስት የልዩ ጥበቃ መኮንኖችን አገር ለሚያተራምስ ግለሰብ አጃቢነት የመደበን መንግስት ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኩል እራሳችንን እንድንጠበቅበት በህጋዊ መንገድ የታጠኩት አንድ ሽጉጥ ግን ለድርሰት የሽብር ክሱ ማስረጃ አድርጎ ለማቅረብ አላፈረም ምክኒያቱም በተረኛ መንጋዎች ዓይን እኛ ደምላሽ ወንድሞቻችንን በሰኔ 15ቱ ድራማ የተነጠቅን ወይ ልቀቅ ወይም ልቀቅ የሚል ልጆቸ የሚል ደጀን ህዝብ የሌለን ነን፡፡ አያዉቁንማ! እንጅማ በሆነዉ ሁሉ ያልተብሰለሰለ እንደህዝብም የደረሰብን አስከፊ ዉርደት የማያርመጠምጠዉ ማን አለ? መላዉ የአማራ ህዝብ ለሀገሩና ለክብሩ መይሳዉን፤እምይን፤ አባኮስትርን፤ አሳምነዉን፤ አስማረ ዳኘን እና ጎቤ መልኬን ወዘተ እንደሆን የሚያዉቀን ያዉቀናል፡፡

የአማራነት ብኩርናቸዉን ለምስር በሸጡ ከንቱዎች እያዩን ነዉ እንዲህ የተዘባበቱብን ፡፡ እኛ ግን ላፍታ እንኳ የማንጠራጠረዉ ደጀን ህዝብ አለን፡፡ ስለልጆቹ ከቶ የማይተኛ አማራ!

ከተረኛ መንጋዎች ፍትህን እንደመለመን ከሞት የበረታ ቅጣት የለም፡፡ በክላሽ ነዉ የሚዋጣል ከሚል ፖሊስ እስከ በግሌም ቢሆን አለቃችሁም የሚል አቃቤ ህግ፤ እናንተማ አሸባሪ ናችሁ መታሰር አለባችሁ ከሚል ዳኛ እስከ የችሎት ንግግራችን በስልክ በቀታ እስከሚከታተል ባለስልጣን አፈና ዉስጥ ሆነን ፍትህን የምንጠባበቅ የፖለቲካ ምንደኞች አይደለንም፡፡

ይልቁንም ታላቁን ህዝባችንን ተስፋ የምናድርግ፤ ያመነዉና የተመካንበት ህዝባችን እኛን ልጆቹን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያንም ከመንጋ ተረኞች ነፃ የማዉጣት አቅምም ችሎታም ያለዉ መሆኑን የተረዳን ነን፡፡ ስለሆን ጥሪዉ የደረሳቸሁ ወገኖች እኛን ከእገታ ለማስለቀቅ ብቻ ሳይሆን ለተሟላ የህዝባችን ነፃነት እና አማራዊ ክብር መመለስ ሁሌም ዝግጁ እንድትሆኑ፤ በሁሉን አቀፍ ህዝባዊ እንቢተኝነትም አፓርታይዳዊ አፈናዉን እንድትታገሉ በሴራ ባጣናቸዉ ወንድሞቻችን ደም ስም እንጠይቃችኋለን፡፡

ህዝባችንን እንዲህ ተዋርዶ ሳያዩ የሞቱ ወንድሞች በእዉነት እድለኞች ናቸዉ፡፡ እንደበግ ተገትተን ከምንታርድ እንደሰዉ በክብር መሞት ፀጋ ነዉ፡፡ ለህዝባችን ታሪክ እና ክብር የሚመጥነዉም አሱ ነዉ፡፡ እነዚህ መንጋዎች ልጆቸን የሚል ህዝብ ፤ ስለአማራዊ ክብሩም እስከሞት የታመነ ወገን እንዳለን ማዎቅ አለባቸዉ፡፡ መንጋዎቹ ባለየን የምንቀጣበት የአምደፅዮን በትር ፤ የጠገበን ማስታገሻ የቴዎድርስ የእሳት ክንድ ዛሬም አብሮን እንደሆነ ማወቅ አለባቸዉ፡፡ ደግሞም የማንጨርሰዉን ብቻ ሳይሆን አሸንፈን በድል የማንደምቅበት ትግል አልጀመርነም ፡፡

የወደቅነዉ ለመነሳት ነዉ! ከዚህ ሁሉ የውርደት ሻለቃ በኋላ ከመራራዉም የዉድቅት አዘቅት በኋላ ጣፋጩን ድል የምናጣጥምበት የማር አምባ አለ፡፡ ማር -አምባ ላይ በድል ያገናኘን!!

እጣፋንታችንን በራሳችን እጆች እንጽፋለን!!

1 COMMENT

  1. በምንም ዓይነት የፓለቲካ ሂሳብ ክርስቲያን ታደለንና ሌሎችን የአብን አመራሮችን በፈጠራ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ስም እስር ቤት ከቶ ሃገርና ህዝብ ለሚያምሰው ለጃዋር ጥበቃ የሚመድብ መንግሥት እውነትን ያውቃል ማለት አይችልም። ጉዳዪ ግን የዘር ፓለቲካ ነው። “የኢህአደግ የቁልቁለት ጉዞ” በተሰኘው መጽሃፉ ላይ ብርሃነ ፅጋብ እንደሚለን ከሆነ ነገሩ የተበላቸው ጠ/ሚ መለስ ከሞቱ በህዋላ ነው። ይህን መጽሃፍ በረጋ መንፈስ ላነበበ ሁሉ ነገር የእቃ እቃ ጫወታ እንደነበር ያመለክታል። ለምሳሌ ያህል የመተካካቱ የፓለቲካ ጫወታ። ግራም ነፈሰ ቀኝ የትላንቱ ትላንት ሆኖ እያለ ዛሬ ደግሞ በወረፋቸው የኦሮሞ የፓለቲካ ወስላቶች ሃገሪቱን ያምሳሉ። በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚፈጸመው ግፍ ለጀሮም ለአይንም የሚቀፍ ነው። ኢ-ሰብአዊነት ትላንትም ዛሬም። አይ ሃገር እንዲህም ብሎ ሃገር የለ። አንዲት በኦሮሞ የፓለቲካ ወጥመድ በጥርጣሬ ተይዛ ከ 78 ቀናት በህዋላ የተለቀቀች እህታችን እንዲህ ትላለች። ሳይታሰብ ጠበንጃ አንጋቾች ከስፍራው ደረሱ እኔም የስራ ሽርጤን አድርጌ ስራ እየሰራሁ ነው። ሳይታሰብ ትፈልጌአልሽ በማለት ያዙኝ እሺ ሽርጤን ላውልቅ ሹራብም ልልበስ ስል አይ ቶሎ ትመለሻለሽ በማለት ለ 3 ቀናት ባዶ መሬት ላይ በጨለማ ቤት ከነሽርጧ ታስራ ቆየት ብሎ ልብስም ምግብም እንደገባላት በእንባ ታወራለች። ይህ ሰውን ያለምንም መረጃ አስሮ እስክናጣራ መረጃ እስክንሰበሰብ ጊዜ ይሰጠን የሚለውን ፓሊስ ራሱን እስርቤት መክተት ነበር። ሰው በጥርጣሬ አይያዝም፤ አይታሰረም። በመረጃ እንጂ። የኦሮሞ ፓለቲከኞች አሰራራቸው ሁሉ እንደ ወያኔና እንደ ደርግ ነው። ያዘው ጥለፈው፤ ግደለው ቅበረው አይነት። የዚህችን እህታችን ገመና አዳምጠው ሃሳብ ከግርጌ ከሰጡት መካከል የአንድ እንዲህ ይላል:: “I hate this Country”. ልክ ነው ያስመርራል። ያበሳጫል። በእስር እያለች ጽንስዋ የወረደው የጄ/ል አሳምነው ጽጌ ሚስት እና እድሜአቸው የገፉ እናትና አባቶች ሳይቀሩ ከባህርዳሩ ግርግር ጋር ተብብር አላቹሁ ተብለው በጨለማ ቤት ውስጥ ናቸው። ጄ/ል አሳምነው በግርግሩ ሰአት አንዲት ጋዘጤኛ ደውላ ስታናግራቸው መፈንቅለ መንግስት እየተባለ ይወራል እንዴት ነው ስትላቸው ይህን ብለዋት ነበር። “በመንደር ውስጥ መፈንቅለ መንግስት ይደረጋል እንዴ?” ያቺ ቃል የመጨረሻ ቃላቸው ትመስለኛል። ዛሬ በባህርዳር በእስር ላይ የሚገኘው በረከት ስምዖን ሃገሪቱ ወደ ከፋ ደረጃ ላይ እየሄደች ነው በማለት በተደጋጋሚ ላቀረቡት ሃሳብ የወያኔ ነባርና ተተኪ አመራሮች ሃሳባቸውን እንዳጣጣሉት ደራሲ ብርሃነ ፅጋብ ያትታል። ዛሬ ግፈኞች በመቀሌ ንጽህ አየር እየተነፈሱ ሌሎች ግን በየምክንያቱ መቃበርና እስር ቤት ወርደዋል። አብሮነት የማይሻ ሸመድማዳ የፓለቲካ ስሌት ለማንም አይጠቅምም። የሞተውን ቁጥር በዘርና በእምነት አስልቶ ማቅረቡም ለማንም አይበጅም። ደግሞስ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞትም ኢትዮጵያዊ በሚል መርህ እመራለሁ ለሚል መሪ የዘር ቆጠራና የእምነት ሰልፍ ለምን ይጠቅማል። ወይስ ብዙ ሰው የሞተው ከኦሮሞ ነው ለማለት ነው? ኦሮሞ ሆነ ሌላ የሰው ነፍስ የሰው ነው። እንባችን የሚፈሰው ለሁሉም ሟች ነው። ሃገሪቷን ጠብቀው ያቆዪን አባቶች ሸሁ ከመስጊዱ፤ ቄሱ ከመቅደሱ ተጠራርተው ጠላትን በመፋለም ነው። ሲሞቱም ይህን ያህል እስላም ያን ያህል ክርስቲያን ሞተ አልተባለም። ጎን ለጎን ተደጋግፈው ነው የወደቁት። የኦሮሞ ጽንፈኞች ድብቅ ሥራቸው ብዙ ነው። አንድ ልጥቀስና ላብቃ በአንድ የትምህርት ተቋም ከሳምንት በፊት የሆነ ነገር። ተማሪው ከአማራ ክልል ኦሮሚያ ወዳለ የትምህርት ተቋም ይመደባል። በስፍራው ይደርሳል፤ ይመዘገባል ትምህርት ይጀምራል። ሲወጣ ሲገባ ግን አራትና አምስት የሆኑ የኦሮሞ ወጣቶች ነገር እየፈለጉ ቆይ ኦሮምኛ እናስተምርሃለን። ቋንቋችን እንደጠላህ አትኖርም። እምቢኝ ስትል ደግሞ የምናረገውን እናውቃለን እያሉ ያስፈራሩታል። ለበላይ ቢናገር ነገሩ ይብሳል። ሊተውት አልቻሉም። ትምህርቱን በመተው ወደ ክልሉ ይመለሳል። ይህ ከሚያልፍ ውሃ የተቀዳ ወሬ አይደለም። እውነት እንጂ! የኦሮሞ ቄሮዎች ሃገር አፍራሽ ናቸው። ጃዋርን የሚከተል ሁሉ እብድና በራሱ ለራሱ ማሰብ የማይችል ስንኩል ሰው ነው። በየስፍራው በተለያየ ክስ በእስር ታጉረው የሚገኙ ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎቻችን ጉዳይም ከጊዜው አለቆቻችን የፓለቲካ ባለተራነት ጋር የተዛመደ እንጂ እውነትነት የለውም። ይፈቱ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.