ሰበር ዜና.. ጀዋርና መንጋው ደቡብ ኢትዮጵያን ብትንትኗን ለማውጣት የጀመሩትን ለማስቀጠል ሃዋሳ በገቡ ምሽት በምዝገባ ጣቢያው ተኩስ ነበር

የሲዳማ ህዝበ-ውሳኔ ማስፈጸምያ ጣብያዎች መካከል አንዱ የሆነው ሀዋሳ ከተማ ምስራቅ ክፍለ ከተማ የምርጫ ጣብያ ውስጥ ተቀምጦ የነበረ የመራጮች ካርድ እና የህዝበ ውሳኔው ማስፈጸምያ ቁሳቁሶችን ለመዝረፍ የተደራጁ ሀይሎች ከለሊቱ 10:30 አከባቢ በጥበቃ ሰራተኞች ላይ ቶክስ ከፍተዋል።

የጥበቃ ሰራተኞች ያደረጉትን የመልሶ ቶክስ ልውውጥ የሰማው በአከባቢው የነበረው ኮማንድ ፖስት ባፋጣኝ አከባቢው ላይ ደርሶ ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገባቸው ይገኛል። የምርመራው ውጤት እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል ሲል ማለዳ ሚድያ ኣስታውቋል።

ካሉት ምርጫ ጣቢያዎች ሁሉ ለምን ለይቶ ዘራፊዎቹ በሃዋሳ ከተማ ላይ ትኩረት ማድረግ ፈለጉ? በአጭሩ ሃዋሳ ውስጥ ፊደል የቆጠሩና የአንድነትን ጥቅም በራሳቸው አገናዝበው የሚወስኑና ጎጆን የሚመርጡ የሲዳማ ተወላጆችና ነዋሪዎች እንደሚበዙ ስለሚታወቅ መሆኑን ለመረዳት በፍጹም አይከብድም።

ጀዋርና ደጋፊዎቹ ሲዳማን ከተቀረው ሰፊዋ ደቡብ ኢትዮጵያ መለየት መነጠልና መገንጠል ለምን ፈለጉ? ለምንስ ይህንን ያክል ትኩረት በመስጠት የሃዋሳ ነዋሪ ያልሆኑትንና ምንም ጉዳዩ የማይመለከታቸውን ሰዎች በዝህ ወሳኝ ወቅት ወደ ሃዋሳ ማንቀሳቀስ ኣስፈለጋቸው?

ደቡብ ኢትዮጵያንና አማራውን 80 ቦታ ለመበጣጠስ መሰሪ ተንኮል የሚጎነግኑት እነኝህ ሃይሎች እንደ ጉድ ተንቦርቅቆ እውነተኛ ፌደራሊዝም ሕዝብ ለመንግስት በመቅረብ ሊያስገኝ የሚገባውን ጥቅም እንዳያስገኝ ተደርጎ የኢትዮጵያችንን 1/3ኛ የቆዳ ስፋት የሸፈነውን ክልል ገና ለማስፋፋት የጎሳ ፖለትካ አይቅርብኝ ብሎ ሰላማዊ ሰዎችን እንደ ሽንኩርት እየከታተፈ ሰላማዊ ያልሆነ የሽብር ተግባር ላይ መሰማራቱ ይታወቃል። ይህ ሃይል የተቀረችውን ኢትዮጵያ ወደ 80 ትንንሽ ትርጉም አልባ ክልሎች ለመበታተን ከወያኔ ጋር በማበር ዛሬ ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለነው ብሄር ብሄረሰቦች ያዘነ በመምሰል በ1ኛነት ሲዳማን ከአጎራባች ጌዴኦ ወላይታ አማሮ ለያይቶ እርስ በራሳችን ስንፋጅ ሊጨራርሱን መሆኑን የምናውቅ በሚገባ እናውቃለን።

ይህ ምንም ዕፍረት ያልፈጠረበት አካል ሃዋሳ ውስጥ ሕዝብ አንድነትን ሊመርጥ ይችላል በተባለበት ክፍል በምሽት ተኩስ ከፍቶ የመመዝገቢያ ካርድ ለመዝረፍ ያደረገውን ሙከራ ስትመለከት እነዝህን ከፋፋዮች አጥብቀህ ለመታገል መቁረጥ ግድ ይለሃል።

ለቅማንትና አገው ሕዝብም ያዘኑ በመምሰል ትንሽ ሊፎካከረን ይችላል ያሉትን የአማራን ክልልንም ለማሳነስ በአቅማቸው ከወያኔ ጋር በመሆን የብሄረሰብ አዛኝ በመምሰል ኢትዮጵያን የማዳከም ዘዴያቸውን እምቢ ብለህ ካልካድክ በስተቀር ግልጥ ያለ ሃቅ መሆኑን ማንም አስረጂ አያስፈልግህም።

አሁንም የጎሳ ፖለትካን ጥለው ወደ ኢትዮጵያዊነት ፖለትካ እያሻገሩን ካሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ጋር በመተባበር እልህ ኣስጨራሹን ትግል አጥብቀን በመታገል ኢትዮጵያን ለመበጣጠስ ከሚፈልጉ ጠላቶቿ እንታደጋታለን። ለእነዝህ የኢትዮጵያ ጠላቶችም ግልጥ አድርገን አስምረን ልንነግራቸው የሚገባው ከግብጽም ጋር በመተባበር እያሴራችሁብን ያለውን እውነታ በሚገባ እናውቃለንና ሕዝባችንን ለማታለል አትሞክሩ። አይሳካላችሁም።

ኢትዮጵያ በክብርና ነጻነት ለዘላለም ትኑር!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.