በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ግጭት የተጠረጠሩ 13 ግለስቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ግጭት የተጠረጠሩ 13 ግለስቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ።

ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ተሳታፊና ተባባሪዎች ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 13 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ነው ዩኒቨርሲቲው ዛሬ የገለጸው ፡፡

በአሁኑ ስዓትም የወልድያ ከተማ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ከተማሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው ተብሏል ፡፡

የግቢው የፀጥታ ሁኔታም አየተረጋጋ ይገኛል፡፡ አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው የነበረውን መረጃ በማሰባሰብ በትላንትናው እለት ከስዓት በፊት ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢና በኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር በኩል ለተለያዩ ሚዲያዎች መረጃዎችን በስልክ የማሳወቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል ፡፡

ይሁን እንጅ በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች ስለ ዩኒቨርሲቲው እየተለቀቁ ያሉት መረጃዎች ከላይ ከተገለፁት በተቃራኒው መሆኑን የገለጸው ዩኒቨርሲቲው፤ በዩኒቨርሲቲው ያልተፈጠሩ የሀሰት ምስሎችንና ቁጥሮችን በማሰራጨት የተጠመዱ አካላትን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሣሥቧል።

(ኢ.ፕ.ድ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.