ፍትህ፣ ርህራሄ ለሁሉም ሁሉም ሰው፣ ሁሉም ዜጋ፣ ሁሉም የኛ ናቸው

ምንም አይነት ምክንያት መደርደር ወልዲያ የተፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ሊያቃልለው አይችልም። ግፍን በግፍ ማወዳደር የግፈኞች መገለጫ ነው። ሁለት ሰብአዊ ፍጡራንን በጭካኔ በገደለ ሰው እና ጥቅምት 11/12 በርካታ ንፁሀንን በጨፈጨፉት አረመኔዎች መካከል አንዳች የሞራል ልዩነት የለም። እንደነዚህ አይነት የጭካኔ ድርጊቶችን በአሀዝ ስሌት ለማቃለል መሞክር በየትኛውም ደረጃ የሚፈፀምን ግፍ ከመደገፍ ያልተናነሰ ድርጊት ነው።

አንድስ ቢሆን ለምን ይሙት!? አንድስ ቢሆን ለምን አካሉ ይጉደል፣ ለምንስ ቀሪው ህዝብ የፍርሀትና የመንፈስ ሰቆቃ ይድረስበት!? ተስፋዎቻቸው ሲቀጠፉ መንፈሳቸው እንክት በሚለው እናቶች ፣ ቅስማቸው በሚሰበረው አባቶች ጫማ እራሳችንን አስገብተን የሀዘኑን ልክ መረዳት አለብን። ፍትህ እንዲሰፍን ስንጠይቅ እንደ ዜጋ ለሁሉም እንጂ፣ ወደ ዘራችን ተጠምዘን እያዬን ሊሆን አይገባም።

አቶ ሽመልስ በጉዳዩ ላይ የተናገሩት ምናልባትም በሌሎች ቢነገር የተሻለ ነበር። አቶ ሽመልስ በክልላቸው ስለተደረገው ጭፍጨፋ በኦፊሴል ሲያወግዙ አላየንም። ጭራሽ የመንጋውን ድርጊት “ሰልፉ/ጥያቄው ትክክለኛ ነበር” በማለት በሰላባዎቹ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በመላው የሀገሪቱ ህዝብና በሀገራችን ላይ ጭምር ተሳልቀዋል። ከድርጊቱ ጠንሳሽ ጋርም “ወንድማችን” ሲሉ አብረዋል።

በነገራችን ላይ ኦሮሚያም ሆነ ሌሎች አካባቢዎች የነበሩት ፅንፎች ሰማይ የነኩት ከአቶ ሽመልስ የኢሬቻ ንግግር በኋላ ነው ። አቶ ሽመልስ ለደረሰው እልቂት፣ የአካል መጉደልና ንብረት መውደም ከጃዋር እና ከ OMN ባላነሰ እንዳውም በበለጠ (የክልል ፕሬዝዳንት እንደመሆናቸው) ተጠያቂ ናቸው።

በሚያስተዳድሯት ኦሮሚያ ለተፈፀሙትና በንግግሮቻቸው ለተፈጠሩት ምስቅልቅሎች ሁሉ፣ እንኳን ይቅርታ ሊጠይቁ እውቅናና ሀዘናቸውን ባልገለፁበት ሁኔታ፣ በወልዲያም ሆነ ቤትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚደርስን ማናቸውንም ድርጊት ለመኮነን አቶ ሽመልስ ምንም አይነት የሞራል ብቃት አይኖራቸውም። በተናገሩት “የተካይና የተነቃይ” ንግግር ሚሊዮኖች አንጀታቸው በተቃጠለበትና ፅንፈኝነት ባሻቀበበት ምህዳር ላይ ቆመው ስለ ሀዘንና ስለ ህግ በላይነት ቢደሰኩሩ አንሰማም፣ አንለማም። ኦሮሚያ ውስጥ የተጨፈጨፉት ምስኪኖች እና ጨፍጫፊዎቹ እኮ ወልዲያ ውስጥ እንደተገደሉት እና እንደ ገዳዮቹ ሁሉ ሰው ናቸው። ላንዱ ፍትህን ያልጠየቀ ለሌላው መጠየቅ አይችልም። ላንዱ ልቡ ያልተሰበረ ለሌላው የሚሆን እንጥፍጣፊ ርህራሄ ሊኖረው አይችልም።

የአማራ ክልል የፀጥታ ሀይል ሁኔታውን በቁጥጥር ስር ለማዋል የወሰደው እርምጃ፣ ባለስልጣናቱ የሰጧቸው መግለጫዎችና የወልድያ ህዝብ ለተማሪዎቹ እያሳዬ ያለው ሀዘኔታ እና ፍቅር ሊወደስ ይገባዋል። “ወልዲያ ውስጥ ያሉ የሌላ ክልል ተማሪዎች ሁሉ ልጆቻችን ናቸው” የሚለው የወልዲያ ህዝብ መፈክር ከምንጊዜውም ምርጥ መፈክሮቻችን ውስጥ አንዱ ሆኖ ሊመዘገብ ይገባል።

ፍትህ በግፍ ለተገደሉ የወልድያ ዩኒ ተማሪዎች!!!
ፍትህ በኦሮሚያ ለተጨፈጨፉት ንፁሀን!!!

የግፍ ሰለባ ለሆኑ ሁሉ ነብስ ይማር!!!

3 COMMENTS

  1. “ፍትህ በአማራ ክልል ለተጨፈጨፉት ንፁሀን (ጉሙዝ፣ ቅማንት፣ ኦሮሞ፣ ወዘተ) !!! ” ለምን አላልክም? አማራ ሲገድል ግፍ ሳይሆን ጽድቅ ነው??? ፈሪሳዊ!

  2. For so long Ethiopia had been fed lies after lies. It is time right now to bring out the truth about the cause of death of the late PM Meles Zenawi, his cause of death needs to be brought out since it makes a huge difference for the talks Ethiopia , Sudan and Egypt are having.

  3. የዘር ተሰላፊዎች እይታ በዚያው የራሴ ነው ብለው በሚያምኑት ዙሪያ መሆኑ አስገራሚ አይሆንም። በኦሮሞ ጠባቦች እይታ ሌላው ዜጋ ንጽህ ኦሮሞ እስካልሆነ ድረስ ቢሞት ቢሰደድ ቢደበደብ ደንታ የላቸውም። ንጽህ ኦሮሞ ብሎ ነገርም የለም! ማንም የአለማችን ሰው ንጽህ ዘር የሚባል የለም! የሚያስገርመው ግን የጠ/ሚሩ ነገር ነው። እንዴት እንዲህ ዓይነት ዘረኛ አስተሳሰብ ያላቸውን ሰዎች እጎናቸው አሰልፈው ኢትዪጵያ አትፈርስም ይሉናል? ስንት ህብራዊና ዓለም አቀፍ አመለካከት ያላቸው የኦሮሞ ልጆች እያሉ እንዲህ አይነት የመድረክ ዲስኩረኛና ጉረኛ ከፋፋይ ሃሳቡን እንዲያራምድ በመንግሥት ይፈቀድለታል? በውኑ ኦሮሞ ክልል የኦሮሞዎች ብቻ መኖሪያ ነውን? ዛሬ በቄሮና በሌሎች አፍራሽ ሃይሎች ድምር ሥር ሃገሪቱን የሚያምሰው የኦሮሞ የፓለቲካ ወስላቶች ስብስብ የፓለቲካ ነፋስ ሳይታስብ አቅጣጫ ለውጦ እርስ በእርሳቸው እንደሚያነካክሳቸው መገመት አይችሉም? ያልፈው ታሪካችን የሚያሳየን ይህኑ ነው። ዛሬ ጀግኖች እየተባሉ በከተማ ሆ የሚባልላቸው የመድረክ ሰዎች በስንቶች ንጹሃን ደም ላይ ተረማምደው ለዛሬ እንደደረሱ ሰው ማወቅ እንዴት ይሳነዋል። ጀግኖቹ እማ በተንኮልና በጠላት ጥይት አፈር ተመልሶባቸዋል!
    ተምረናልና እናስተምራለን የሚሉት የዘር ልክፍት ሙሁራን “ክልል፤ ቋንቋ፤ አማራ፤ ትግሬ፤ ኦሮሞ” ገለመሌ ሲሉን እውቁ ተቀዳሚ ሃጂ ሙፍቲ እንድሪስ ኡመር ዘለቀ እንዲህ ይሉናል። “አለማችን አንድ መንደር ሆኗል”. እዚህ ላይ የተማረው ማን ነው? አማራ ነው በግድ አጥምቆ ስሜን ቀይሮ ክርስቲያን ያደረገኝ የሚለው ነው ወይስ የሼሁ እይታ? ዘረኞች ዘራቸውን ተገን አርገው ህዝባችንን ለመጋጥ እንጂ ለኦሮሞም ሆነ ለአማራ ወይም ለትግራይ ህዝብ እዚህ ግባ የሚባል መልካም ነገር የሰሩት የለም። አውሬ ጫካ ውስጥ እንደሚደበቀው ሁሉ እነዚህ ሃይሎችም ህዝባችንን መደበቂያ አድርገውታል። ፓለቲካ የሽወዳ ትርክት ነው። ትላንት መሬት ላራሹ ያሉን ናቸው ዛሬ በጋምቤላ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች “መሬት ለባለ ሃብት” በማለት ደን እየመነጠሩ እያስመነጠሩ ምድሪቱን ራቁቷን ያስቀሯት። አቶ ሽመልስ በኦሮሞ ፓለቲካ የሰከረ፤ በወደቀ ሰው የሚፎክር ገልጃጃ ፍጡር ነው። ግን ፓለቲካዊው ትሩፋቱ በአንድ ጀምበር ጨለማ ገብቶ ሰካራም እንደ ረገጠው ቆርቆሮ የሚጠራመስበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። የሰው ልጅ መደበቂያ ዘርና ቋንቋ አይደለም። እውነት እንጂ! ለኦሮሞው፤ ለአፋሩ፤ ለትግሬው፤ ለሃረሬው ባጠቃላይ ለሰው ዘር ሁሉ ርህራሄ የሌለው ሰው ሳይሆን ተኩላ ነው። የኦሮሞ ፓለቲከኞችም በበጎች በረት ውስጥ የተሰገሰጉ ተኩላዎች ናቸው። ሰው ዘሩን ብቻ ለይቶ እንባ ካፈሰሰ ሂሊናው የተበላሸ ፍጡር እንደሆነ ያመላክታል። የማንም ሞትና ጉስቁልና የሁላችንም ሃዘን ሊሆን ይገባል። በወያኔና በሻቢያ ተዘርቶ አሁን በኦሮሞ የፓለቲካ ጽንፈኞች ጣራ ላይ የወጣው ወልጋዳው የዘር ፓለቲካ ሁሉንም ያጠፋል እንጂ ለማንም አይጠቅምም። ሆን ተብሎ በሰውር በሚደረግ የፓለቲካ ደባ የስንት ወገኖቻችን ህይወት ለዘመናት ተቀጥፏል። አሁንም መከራውና ኡኡታው ከፋ እንጂ አልተለወጠም። ዶ/ር አብይ በሚያማምሩ ቃላቶች ሰውን ከመስበክ አልፈው ህግና ደንብ እንዲከበር፤ የኦሮሞ ብሄርተኞች በሌሎች የሃገሪቱ ዜጎች ላይ የሚያደርሱትን ግፍ ለመግታት ቢታገሉ ተመራጭ ነው። ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል እንዲሉ የኦሮሞ የጸጥታ ሃይሎች፤ በተለይም የአዲስ አበባ ፓሊስ በንጽሁሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰውን በደል ማቆም አለበት። ያለዚያ ሰው ራሱን ከጅምላ ጥቃትና ከፍትህ መዛባት ለመጠበቅ ራሱን ማዘጋጀት ይኖርበታል። ዓይን እያየ ታርዶ ከመሞት፤ ተፋልሞ ማለፍ ይሻል ይመስለኛል። የኦሮሞ ፓለቲካ ገና ብዙ ገመና እንደሚያመነጭ ይታየኛልና። ጎበዝ ጠንቀቅ ይሻላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.