በርካታ የአማራ ተማሪዎች ባደረባቸው የደህንነት ስጋት ከጅማ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ወጥተው በአካባቢው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተጠለሉ መሆናቸውን ተናገሩ

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ

በጅማ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ተማሪ እንደሆነ የገለፀው ምንጫችን የኦሮሚያ ተማሪዎች ሰልፍ ካደረጉበት ከጥቅምት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ትምህርት መቋረጡን ገልጧል።

ተማሪው እንደሚለው በጅማ ዩኒቨርስቲ በግቢው ውስጥ ጦር መሳሪያ ገብቷል በመባሉ፣ የአማራ ተማሪዎች ይውጡ የሚል ወረቀት መበተኑ፣የተደራጁ የኦሮሚያ ተማሪዎች ሌሊት ላይ እንደሚገቡ እየተነገረ ስለሆነ ባትገቡ ይሻላል መባሉን ተከትሎ ቁጥራቸው ከ500 በላይ የሚሆኑ የአማራ ተማሪዎች በአካባቢው በሚገኘው በኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው እንደሚገኙ ተናግሯል።

ዛሬ ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም ረፋድ ላይ ከጅማ ዩኒቨርስቲ የደወለች ተማሪ እንደገለፀችው በኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ከተጠለሉት ተማሪዎች መካከል በአንዲት የአማራ ተማሪ ላይ ድብደባ በመፈፀሙ ወደ ግቢው ሆስፒታል የገባች መሆኑን ገልፃለች።

የጅማ ዩኒቨርስቲም የተፈጠረውን ችግር በውይይት ከመፍታት ይልቅ በዝምታ እየተመለከተ ነው ሲሉ ተማሪዎች ወቅሰዋል።

መንግስትና የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትም የተፈጠረው ችግር ያሳሰባቸው አይመስሉም ብለዋል።

በትናንትናው እለት በደምቢ ዶሎና በሐሮማያ ዩኒቨርስቲዎች የተደራጁ የኦሮሞ ተማሪዎች በፈፀሙት ድብደባ ሶስት የአማራ ተማሪዎች መገደላቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.