በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ሀይማኖት እና ብሔር ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ቀጥሏል ሁለት ቤተ ክርስቲያን አቃጥለዋል

ህብር ራዲኦ

. ጋራ ሙለታ (ኩርፋ ጨሌ ወረዳ) ዋቅጅራ መድኃኔ ዓለም ሙሉ በሙሉ ተቃጥሏል !

. ጋራ ሙለታ (ኩርፋ ጨሌ ወረዳ) ገንዲድ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሏል !

. ቀርሳ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ኦርቶዶክውያንን ቤት ንብረት ለይቶ መዝረፍ፣ ማውደምና መቃጠል !
፨ ምዕመናን ህይወታቸውን ለማትረፍ በየአቅጣጫው ሸሽተዋል ፤መሸሽ ያልቻሉ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል ይድነቃቸው ከበደ መረጃውን አጋርቷል።
በሰላም የኖረውን ሕዝብ በሀይማኖት እና በዘር ለመከፋፈል እና የእርስ በእርስ ግጭት ለማስነሳት የወልዲያውን ጥቃት መሰረት አድርጎ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከተከፈተው ጥቃት በተጨማሪ ትላንት በምዕራብ ሐረርጌ በተመሳሳይ ቤት ማቃጠል እና ማጥቃት የነበረ ሲሆን ዛሬ በምሥራቅ ሐረርጌ ተጠናክሮ ቀጥሉዋል።
በዶዶላ አባቱ እና ዘመዶቹ በቅርቡ ሀይማኖት እና ብሄር ላይ ባነጣጠረው ጥቃት የሞቱበት ግለሰብ ለኢትዮጲስ ጋዜጣ በሰጠው ቃለ መጠይቅ በኢትዮጵያ አይ.ኤስ መግባቱን እንደሚጠረጥር እና መንግስት እና ሕዝቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ማድረጉ አይዘነጋም።
በኢትዮጵያ በሰላም አብሮ በኖረው ሕዝብ መካከል በሀይማኖት እና በብሄር የእርስ በእርስ ግጭት እንዳይነሳ በስልጣን ጥም የሰከሩ ጽንፈኞች ከያዙት አውዳሚ መንገድ እንዲታቀቡ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲደረግ መቆየቱ አይዘነጋም።
የዛሬውን ቃጠሎ የሚያሳይ ፎቶ ባለማግኘታችን ለማስታወስ ያህል
ከስር ያለው ፎቶ አይሲስ ኢራቅ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ሲያቃጥል የተነሳ ፎቶ ሲሆን ይህንንም ከጎግል ማግኘት ይቻላል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.