ሰው እንዴት እያወራና እያለቀሰ ይሞታል???

አሁን በሀገራችን ያለው የለቅሶ ፖለቲካ ነው!! ከአዲስ አበባ እስከ ድሬዳዋ፣ ከወልዲያ እስከ ወለጋ፣… ሁከትና ብጥብጥ በተነሳባቸው አካባቢዎች ያለው ነዋሪ በጥቂት አጉራ ዘለል ጎረምሶች ሰላምና ደህንነቱ ሲናጋ፣ በግፍ ህይወቱ ሲቀጠፍ ራሱን አደራጅቶ ሰላሙን ከማስከበርና ችግር ፈጣሪዎችን ለፍርድ እንዲቀርቡ ከማድረግ ይልቅ ቤቱ ውስጥ ተወሽቆ “ገደሉኝ፥ አቃጠሉኝ” እያለ ያለቅሳል። የአከባቢውን ነዋሪዎች አስተባብሮ ሕይወትና ንብረቱን ከጥቃት ከመታደግ ይልቅ ቁስልና ሬሳ ፌስቡክ ላይ ይለጥፋል። የራሱን ሰላምና ደህንነት ማስከበር የተሳነው እንከፍ ሁሉ “ዶ/ር አብይ ይቆረጥ፣ ጃዋር መሃመድ ይፈንዳ” እያለ ያላዝናል። ሀገሩን በጭባጫ አልጫ ብቻ ነው የሞላው? እንዴት 20ሺህ ተማሪዎች ያሉበት ዩኒቨርስቲ 20 በማይሞሉ ተማሪዎች ይታመሳል? ሰው እንዴት በጋራ ሰላሙን ማስከበር ተስኖት በፍርሃት እያለቀሰ ይሞታል?? ቲሽ.. ምድረ በቅባቃ

አውሮፓና አሜሪካ ያለው ዲያስፖራ ደግሞ የባሰ ነው። ነጋ ጠባ “ጃዋር አሸባሪ ነው! ህዝብ እያስፈጀ ነው! ይከሰስ! ይታሰር! ይሰቀል! ይገደል!…” ጲሪሪሪሪሪሪሪ!!! ከዚህ ሁሉ አስለቃሽ እንዴት ልብ ያለው ሰው ይጠፋል? ከዚህ ሁሉ ሙሾ አውራጅ እንዴት አንድ ለህዝብና ሀገር የሚያስብ ይጠፋል?  ሜሪካዊ_ዜግነት ያለው እብሪተኛ ነጋ ጠባ ህዝብ እያሸበር ሀገሬን ለማፍረስ መስራቱ ሳያንሰው፣ በዚህ ተግባሩ ሀገር ውስጥ ባይከሰስ እንዴት አሜሪካና አውሮፓ ድረስ ሄዶ ህዝብ ይቀሰቅሳል? የሀገሪቱ ፕረዘዳንት የምርጫ ተፎካካሪው እንዲከሰስ ስለጠየቀ ብቻ ቁምስቅሉን በሚያይበት ሀገር ጃዋር መሃመድ ሰብሰባ ጠርቶ ጥላቻ እየዘራ ዕልቂት ይደግሳል። ስንት መቶ ሺህ ኢትዮጵያዊ ባለበት ሀገር ህዝብን ለማጫረስ፣ ሀገርን ለማፍረስ ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው ከተማ እየዞረ ሲሰበሰብና የደም ገንዘብ ሲሰበስብ እንዴት እሱን ከስሶ ለፍርድ የሚያቀርብ እንዴት አንድ ሀገር ወዳድ ይጠፋል? ይህን ማድረግ ካቃታችሁ እዚህ ያሉት ምን እንዲያደርጉ ትፈልጋላችሁ? ጃዋር መሃመድ ከታች በተዘረዘሩት የአሜሪካና አውሮፓ ሀገራት እንዳሻው ተመካክሮ፣ ረብጣ ዶላር ሰብስቦ የመጣ ዕለት የእሱ ትክክለኝነት በተግባር ይረጋገጣል። ከማንኛውም ዓይነት ጥፋትና ወንጀል ነፃ መሆኑን ያስመሰክራል! ለዚህ ደግም ሙሉ ዕውቅና ምስክርነት የምትሰጡት አውሮፓና አሜሪካ ያላችሁት ናችሁ

እኔ በእያንዳንዷ ቀን የምናገረውና የምፅፈው ህይወቴን አስይዤ ነው። እዚህ በፍርሃት እያለቀሰ ለሚሞት ሰው ህይወቴን አልሰጥም። አውሮፓና አሜሪካ ተቀምጦ ህግና ስርዓት ይከበር እያለ የሚጮኸው ጃዋርን ለፍርድ ለማቅረብ አንዲት እርምጃ መራመድ ከተሳነው ተራ ወሬ፣ ባዶ ጩኸት፣ ከንቱ ቀረርቶ ብቻ ነው። ለዚህ ደግሞ እንኳን ህይወቴን ትኩረቴን አሌሰጠውም። ያን ዕለት ሀገር፥ ህዝብ ቅብርጥስ ማለቴን ትቼ እኔም እንደ እናተ የራሴን ህይወት መኖር እጀምራለሁ። ከዚህ በኋላ ስዩም እዚህ ቦታ ሰው አለቀ፣ ቤት ተቃጠለ የሚል ወሬ፣ አዎ ወሬ መስማት አልፈልግም። አንተ በራስህ ማድረግ የፈራህውን ነገር እኔ የማደርግበት ምክንያት የለም። አንተ ህግና ስርዓት ባለበት ሀገር ማድረግ ያቃተህን ነገር እኔ እዚህ ለማድረግ የምለፋበት ምክንያት የለም። በጭባጫና ወሬኛ ለሆነ ህዝብ የምጨነቅበት ምክንያት የለም

ስዩም ተሾመ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.