አያቶላህ ጃዋር ግራኝ መሐመድ ከወንጀሉ ለመደበቅ የሚከተላቸው ስልቶች! – አቻምየለህ ታምሩ

ጆርጅ ኦርዌል ‹‹Notes on Nationalism›› በተባለው ዝነኛ ጽሑፉ ብሔርተኛ ልሂቃን የራሳቸው ወገን የፈጸመውን ግፍ አለማውገዝ ብቻ ሳይሆን ግፉን ለመደበቅ ያላቸው ችሎታም አስገራሚ ነው ይላል። የአያቶላህ ጃዋር መሐመድ ወታደሮች በትናንትናው እለት በሐረርጌ ውስጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሱትን ውድመት ለመደበቅ ኦ.ኤም.ኤን. የተባለው የአያቶላህ ጃዋር መሐመድ ቴሌቭዥን የሄደበት ርቀት ለጆርጅ ኦርዌል ጽሑፍ አይነተኛ ምሳሌ ነው።

ኅዳር 3 ቀን 2011 ዓ.ም. በጃዋር መሐመድ መንጋ በሐረርጌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያኖች መቃጠላቸውን የነገረችን ባለቤቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ናት። የእምነት ቤቱ ባለቤት ቤቷ መቃጠሉን የነገረችንን ነው እንግዲህ የአያቶላህ ጃዋር ቴሌቭዥን አልተቃጠለም ውሸት ነው የሚለን። ነገሩ የጊዮርጊስን መገበሪያ የበላ ተናገር ተናገር ይለዋል ነው። የኦ.ኤም.ኤን. የክህደት ዘገባ በቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ ጀርባ ያለው አካል ወንጀሉን ለመደበቅ የሚያደርገው እቅድ አካል ነው።

ባገራችን መንግሥት ስለሌለ ከ100 በላይ ንጹሐንን በሃይማኖታቸውና በማንነታቸው ምክንያት በግፍ ያስጨፈጨፈው ቀንደኛ ወንጀለኛ ያላንዳች ጠያቂ መንግሥት ነኝ በሚለው አካል ጠባቂ ተመድቦለት ደልቶት ተዘባኖ እየፏለለ ይገኛል። ወንጀል ከሕግ በላይ ሊሆን የሚችለው መንግሥት በሌለበት አገር ነው። በዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ አያቶላህ ጃዋር ከሕግ በላይ ነው። ምንም ቢያደርግ ተጠያቂነት የለበትም። በርግጥ በዚህ ተጠያቂው ቀንደኛ ወንጀለኛው ጃዋር ሳይሆን ቀዳማዊ ተጠያቂው ወንጀለኛው አገዛዝ ነው።

ባጭሩ አያቶላህ ጃዋር ተራራ ከሚያክለው ወንጀሉ ለመደበቅ የሚጠቀማቸው ሁለት ዋና ዋና ስልቶች አሉት። አንደኛው ጆርጅ ኦርዌል እንዳለው በሚቆጣጠረው ሚዲያና በሚያሰማራቸው እንደ በቀለ ገርባ አይነት ነውረኞች ወንጀሉን መደበቅ ሲሆን ሁለተኛው ስልት ደግሞ የሚፈጽመውን አሰቃቂ ወንጀል ከራሱ በተቃራኒ ነው በሚለው አካል እንደተፈጸመው ወደ ውጭ መግፋት [externalize ማድረግ] ወይም በተቃራኒ ያለ አካል ለመፈጸመው የተሰጠ ግብረ መልስ አድርጎ false equivalance መፍጠር ናቸው። የሐረርጌውን የቤተክርስቲያን ቃጠሎ የካደው የዛሬው የኦ.ኤም.ኤን. ዘገባ ከመጀመሪያው ስልት የሚመደብ ነው።

4 COMMENTS

  1. በርግጥ ሰው እንኳን በሃማኖቱና በብሔሩ ምክንያት ይቅርና በማንኛውም ሰበብ መሞት የለበትም፡፡ በሐረርግ ውስጥ ስለተፈጸመው የቤተክርስቲየን ቃጠሎ ጉዳይ አስታከህ የጻፈከው ጉዳይ ዓላማው በሰበቡ የጀዋርን ስም እንደለመድከው ለማጥፋት እንጂ ስለቃጠሎው ስለተቆረቆርክ መስሎ አይታየኝም፡፡ መላው የኦሮሞ ሕዝብ አንተንና መሰሎችህን የነፍጠኛ ሥርዓት አቀንቃኞችን ዘውትር ስለምንከታተል ዋናው ዓላማችሁ የ150 ዓመት ጥያቄዎች የሆኑት የአሮሞ ሕዝብ የነጻነት፤ የዲሞክራሲ፤ የእኩልነት፤ በክልሉ ውስጥ ያለውን የተፈጥሮ ሃብት መጠቀምና ራሱን በራሱ የማስዳደር መብት ጥያቄዎችን ለማፈን ባለመቻላችሁ ነው እንጂ ሌላ ዓላማ አይመስለኝም፡፡ ዋናው ዓላማችሁ ኦሮሚያ ከተገነጠለች የአማራ ሕዝብ ሊኖር አይችልም ብላችሁ በዕውር አስተሳሰብ የአማራን ሕዝብ ስለምትነዱት ነው፡፡ በርግጥ የጠፈጥሮ ሃብት ለእንድ ሃገር ዕድገት አስተዋጽኦ የሚያደርግ ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን ወሳኝ አይደለም፡፡ ስለሆንም እናንተ ከእንግዲህ እንደበግ የምትነዱት እንኳን ኦሮሞ ይቅርና ሌላ ስለማታገኙ አማራን ነጻ ለማውጣት በትታገሉ ይሻላል፡፡ በመሆኑም የአንድ ግለሰብን ስም ለማጥጥት እንቀልፍ ከምታጣ ዋና አጀንዳችሁ የአማራ ጉዳይ ቢሆን ይሻላል፡፡ 200 ዓመትም ወይም 1000 ዓመት ይፍጅ የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ መውጣቱ አይቀርም፡፡ ለዚህ ክቡር ዓላማ ልጆቻችን ኮትክተን እናሳድጋለን፤ ፈጣሪ ሁሌም ከተጎዱ ነጻነት ለናፈቃቸው ሕዝቦች ጋር ነው፡፡

  2. በርግጥ ሰው እንኳን በሃማኖቱና በብሔሩ ምክንያት ይቅርና በማንኛውም ሰበብ መሞት የለበትም፡፡ በሐረርግ ውስጥ ስለተፈጸመው የቤተክርስቲየን ቃጠሎ ጉዳይ አስታከህ የጻፈከው ጉዳይ ዓላማው በሰበቡ የጀዋርን ስም እንደለመድከው ለማጥፋት እንጂ ስለቃጠሎው ስለተቆረቆርክ መስሎ አይታየኝም፡፡ መላው የኦሮሞ ሕዝብ አንተንና መሰሎችህን የነፍጠኛ ሥርዓት አቀንቃኞችን ዘውትር ስለምንከታተል ዋናው ዓላማችሁ የ150 ዓመት ጥያቄዎች የሆኑትን ማለትም የአሮሞ ሕዝብ የነጻነት፤ የዲሞክራሲ፤ የእኩልነት፤ በክልሉ ውስጥ ያለውን የተፈጥሮ ሃብት መጠቀምና ራሱን በራሱ የማስዳደር መብት ጥያቄዎችን ለማፈን ባለመቻላችሁ ነው እንጂ ሌላ ዓላማ አይመስለኝም፡፡ ዋናው ዓላማችሁ ኦሮሚያ ከተገነጠለች የአማራ ሕዝብ ሊኖር አይችልም ብላችሁ በዕውር አስተሳሰብ የአማራን ሕዝብ ስለምትነዱት ነው፡፡ በርግጥ የጠፈጥሮ ሃብት ለእንድ ሃገር ዕድገት አስተዋጽኦ የሚያደርግ ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን ወሳኝ አይደለም፡፡ ስለሆንም እናንተ ከእንግዲህ እንደበግ የምትነዱት እንኳን የኦሮሞ ሕዝብ ይቅርና ሌላም ስለማታገኙ አማራን ነጻ ለማውጣት በትታገሉ ይሻላል፡፡ በመሆኑም የአንድ ግለሰብን ስም ለማጥፋት እንቀልፍ ከምታጣ ዋና አጀንዳችሁ የአማራ ጉዳይ ቢሆን ይሻላል፡፡ 200 ዓመትም ወይም 1000 ዓመት ይፍጅ የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ መውጣቱ አይቀርም፡፡ ለዚህ ክቡር ዓላማ ልጆቻችን ኮትክተን እናሳድጋለን፤ ፈጣሪ ሁሌም ከተጎዱና ነጻነት ከናፈቃቸው ሕዝቦች ጋር ነው፡፡

  3. እናመሰግናለን አቻምየለህ ተበድለንም ሃዘናችንን በቅጡ እንዳንወጣዉ ሀሰት ነዉ ይሉናል እንዴት ያሳዝናል። በጭሮ አራስ ልጇ አጠገብ አርደዋት የሄዱትን ወጣት አይቶ ጁዋር እንዲህ ሲያላግጥ ማየት በጣም ያሳዝናል ይህ ግፍ መቺ ይቆም ይሆን? አድራጊዎችስ ይህን አሰቃቂ ድርጊት አድርገዉ ማላገጣቸዉን ቢተዉን። ተበዳይ እንግዲህ መላቀሱን አቁመህ የሚያዋጣህን መምረጥ ነዉ እነዚህ ሰዎች ርህራሄ አልፈጠረባቸዉም የግራኝ ደቀ መዛሙርትና የተግባር ልጆች ናቸዉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.