የህ ዋ ሓ ት መሪዎች እብደት- በትግራይ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና ከሙሁራን ተመራማሪዎች ጋር ሆነን የፓርላማ ምርጫ እካይደን የትግራይ ዲፋክቶ ሪፓፕሊክ መንግስት እንመሰርታለን !

የህ ዋ ሓ ት መሪዎች እብደት ፤ ክፍል 2

ፈደራል መንግስት የ20 12 ዓ ም ሀገራዊ የፓርላማ ምርጫ ሊያካይድ ካልቻለ እኛ በትግራይ ካሉት ተፎካካሪ ፓርቲዎችና ከክልላችን ካሉት ሙሁራንና ተመራማሪዎች ጋር ሆነን ለብቻችን ምርጫ አካይደን ዲፋክቶ የተግራይ ሊፓፕሊክ መንግስት በማቋቋም የትግራይ ህዝብ ድህንነት እና ሰላም እናራጋግጣለን በማለት የህዋሓት ልሳን በሆነው ወይን መጽሄት 43ኛ አመት /ቅጽ 2 / ቁጥር 5 ህትመት በማያሻማ አስቀምጦልናል ። ግን ጥያቄ አለኝ ?

1 ኛ በተግራይ ያሉ ተፋካካሪ ፓርቲዎች በማሳተፍ ምርጫ እናካይዳለን ካላቹሁ ከናንተ የመገንጠል አላማ የያዙ ፓርቲዎች እነማን ናቸው ?ዓረና ትግራይና የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲዎች ከሆነ የሚፈልጉት ሁሉም ቢሄሮች ቢሄረሰቦች በእኩልነት ያሳተፈ የኢትዮጱያ ዲሞክራሲያዊ ፈደራል ስርአት ለመመስረት የሚያምን ሆኖ የ20 12 ዓ ም ምርጫ ለማካየድ የማይቻል ከሆነ ሀገር ከመበታተኗ በፊት ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ፣ሁሉም የኢህአደግ አባል ፓርቲዎች እና አጋሮቹ ። እንዲሁም በሀገራችን የሚገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ስቢክ ማህበራት ያሳተፈ የአንድነት ሽግግር መንግስት መስርቶ አገር አረጋግቶ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በማካየድ መጀመሪያ ፈዳራላዊት ኢትዮጱያ መመስረት ፣ቀጥሎ የትግራይ ክልላዊ ፈደራላዊት መንግስት ለማቋቋም ነው የሚፈሉጉት ። አገር አቀፍ ፈደራል መንግስት እንዳለ የተጠበቀ ሆኖ ። ይህ ደግሞ በትግራይ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ቢሄር ቢሄረሰቦች ፈደራላዊ ስርአት መስርተው መብታቸው መራጋገጥበፈደራልመንግስትም እኩል ቦታና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አለባቸው ይላሉ ።በመሆኑም ትግራይ ገንጥለን ነጻ ሀገራዊ መንግስት እንመሰርታለን የሚለው የህዋሓት አማራር ክህደት እኔ በግሌ ፍጹም አልቀበለውም ።

የመድረክ አባል የሆነ ዓረና ትግራይም የሚቀበለው አይመስለኝም ። መላው የትግራይ ህዝብም አሁን የህዋሓት አማራር ሊከተለው እያሰበ ያለ የመገንጠል መንገድ ለትግራይ ህዝብ ከሁሉም ነገር ማለት በኢኮኖሚ ፣በማህበራዊ ፣በፓለቲካ ፣በዲፕሎማሲ ሊያገኛቸው የሚችሉ ሁሉም አይነት ጥቅሞች ሊያሳጡት ስለሚችሉ ይህ አስተሳሰብና ተግባር ማውገዝ አለበት።

2 ይህ የመገንጠል ጥያቂ የሚከተሉት በህዋሓት መሪዎች የተሰሩ ባይቶና እና 3 ይ ወያነ የሚባሉ ተፎካካሪ ፓርቲ ተብዬዎች እና ህዋሓት ብቻ ናቸው ። ታድያ ህዋሀት አነዚህና ሌላ እስከአሁን በተለያዬ ሻጥር ተሸፋፈነው የቆዩ ግማሾቹ ማንነታቸው የማን መሆናቸው ግልጽ ያልሆኑ በግልጽ ትግራይ መገንጠል አለባት እያሉ ለረጅም ጊዜ የቆዩ ።አንዳንዶቹ በህዋሓት አንጋፋ መሪዎች በኢኮኖሚ በሞራል እየታገዙ በትግራይ የግል መጽሄትና ጋዜጣ እያዛጋጁ ለወይን መጽሄትና ወይን ጋዜጣ ተክተው ለህዋሓት አማራር ልሳን ሆነው እየሰሩ የቆዩ አሁን ወደ ተፎካካሪ ፓርትነት ተቀይረው የህዋሓት አማራር እስትራተጂ አለማ ሊያራሙዱ (ሊያስፈጽሙ ) ህዝብ ለመደናገር ራሱ ህዋሓት ከሰራቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተወዳድሬ ነጻ የትግራይ መንግስት እመሰርታለሁ እያለን ያለ ህዋሓት ። ግን ይሳካለታልን? አበደን የትግራይ ህዝብ እኮ ከኢትዮጱያውነቱ የሚፍቀው አካል የለም እሱ ራሱ ባለቤት ነውና ።እነሱ እንደሆነ የኃላ ታሪካቸው እንደሚነግረን ከጥን ጀምረው አገርን የመካዳ እና መሸጥ ከአባታቸው አያታቸው ቀደምት አያታቸው ጀምረው ሀገር ከሀዲዎች ናቸው ።

3 የህዋሓት መሪዎች ሙሁራንና ተመራማሪዎች በመሳተፍ ትግራይ ለብቻዋ ምርጫ እንዲካይድ አደርጋለሁ ይለናል ፤ አይ ማለት ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ አጎዛ አንጥፉሉኝ አለ ይባል የለ ?መቸ ነው የህዋሓት አማራር ሙሁራንና ተማራማሪዎች የታረቃቸው ? ከፍተኛ ሙሁራን ቀንደኛ የአቤታዊ ዲሞክራሲ ስርአት ጠላቶች ናቸው እያለ እየፈረጃቸው የመጣ አይደለም ? ለመሆኑ ህዋሓት ሙሁራን ተማራማሪዎች የሚሉዋቸውስ እነማን ናቸው ?እነዚያ ህዋሓት በጠራው ስብሰባ ፣በድምጽ ወያነ ቲቪ እየቀረቡ በህዋሓት አማራርና ቋንቋ ፣አስተሳሰብ ቃላት እየመረጡ የሚናገሩ ናቸውን ? እነዚህ ከሆኑ ሙሁራን እያለን ያለው መልሱ አደሉም ነው ። ህዋሓት ከጥንቱ ከጥዋቱ ቡቁ ሀቀኛ ሙሁራን ወደ አጠገቡ አስጠግቶ አያወቅም ። አሁን ያለው ሀቀኛና ቡቁ በሙያው የሚተማመን ሙሁር ተመራማሪ ወደ ህዋሓት አይጠጋም አሁን የህዋሓት አማራር እያሰበው ያለው የመገንጠል አስተሳሰብ አይቀበለውም ። ግን ደግሞ አገር እጠፋች ዝምታን መርጦ በሩቅ ተመልካች መሆኑ ከወንጀሉ አይድንም ።በመሆኑ የሀገራችን ሙሁራን አገራችን ወደ ገደል እስገያባት ነው ።ስለ ሆነ እባካችሁ ሙሁሯዊ ግዴታችሁ ተወጡ ። አገር ከወደቀች ሙሁራውነታችሁን ይወድቃል። ።

4 ኢህአደግ እንዋሀዳለን ብሎ ላይና ታች የሚለው ያለም በእኔ እይታ አሁን ያለው በተለያዩ ቡዱኖች ተከፋፍሎ እየተጎታተለ እያለ ፣በሴራ እየተጠላለፈ ባለበት በአሁኑ ጊዚ ለኢትዮጱያ ህዝቦች ለማጭበር በሀገር ዳረጃ ያሉ ሁሉም ሚዲያዎች በመቆጣጠር በባዶ ዲስኩር ቢያሰማንም በአሁኑ ጊዜ እዋሀድ አለሁ ቢለንም እየተከለው ያለው የውህደት አቅጣጫ አንደኛ ሁሉም ፓርቲዎች በሴራ በተጠላለፉበት ሁኔታ ላይ ነው ያሉ ።ሁለተኛ በመቦዳደንና በመዶላለት ፣በድለላ ወ ዘ ተ የሚፈጸም ውህደት ስለሆነ ።ሰወስተኛ በተላላኪነትና በግብታውነት እየተፈጸመ ስላለ ፤ አራተኛ የውህደቱ ሂደት ህዝብ ያላሳተፈ ስለሆነ እና ስለማያውቀው ውህደቱ በአሻዋማ ምድረበዳ የተመሰረት ቤት ስለሆነ ዘላቂነት የሌለው በመሆኑ ይህ ውህደት አገርን አተራምሶ የሚበታትን ስለሆነ አገር አፍራሽ ነው ።

5 መፍቲሄው ሆኖ የሚታየኝ በአሁኑ ጊዜ መንግስት የለም ።ሀገራችን በኢኮኖሚ ማሽቆልቆላ ፣በጸጥታ መናጋትና እጦት ዜጎች ዋስትና አጥቷል ።በአጠቃላይ ሀገራችን በጨለማ ድባብ ተውጣ አለች። ስለሆነ ጊዜ በማይሰጥ ጊዚያዊ የአንድነት መንግስት በመቋቋም ሀገራችን ለማዳን እንራባረብ ።

የትግራይ ህዝብ ሆይ አነዚህ የህዋት አማራር ወገንህ መስለው አንተን ወደ የጨለማ አዘቅት ግባ ነው እያሉህ ያሉ በመሆኑም የነዚህ መንገድ አንተ ኢትዮጱያ ራስ መሆንም እካዱህ ይገኛሉ ።ስለዚህ ሁኔታው በውል አጢነህና አጥንተህ ወደ ትክክለኛው በሞቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ያለፉበት አላማ ወደ ኃላ መለስ ብለህ በማዬት አቃምህን ውሰድ ! ! !
ይቀጥላል ፤

2 COMMENTS

  1. አገር መምራት እንዲ ከሆነ ቀላል ነው ማለት ነው።ትግራይ አገር ስትሆን መሀል አገር ያለ ትግሬ ተነቅሎ ትግራይ ሲኼድ፣ለዘመናት የተለፋበት ጥሪት፣ላለፉት አስርተ አመታት የተዘረፈ ንብረትና መሬት ሲመለስ የት ሊደረስ ነው።እንደገና በኤርትራውያን እንደሆነው ወንድም ሕዝብ እያልን ስደተኛ እያልን ልንቀጥል ነው?
    ትግራይ አገር ሆና የለመደ የወያኔ ጠባብ ዘረኛ መንግስት አድዋ፣አክሱም ፣ሽሬ፣መቀሌ እያለ ሌላ እሳት ሌላ የወገን እልቂት ልናይ ነው?
    ትግሬይ አገር ስትሆን በሰሜን ከኤርትራ፣በምስራቅምራብናደቡብ ከወገኑ ጋር ሌላ የድንበር ጦርነት እሳት።
    እነዚህ በመጠጥና በጫት፦ጌች የናወዘ ጭንቅላት የያዙ ሰዎች አመራር ሕዝባችን እንደፈለጉ ለማድረግ ማን ፈቀደላቸው።የአብይ መንግስት ለትግራይ ሕዝብ ሀላፊነት የለበትም?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.