ይህቺ ባቄላ ካደረች ……..! ከታምራት ይገዙ

“ቃየንም ወንድሙን አቤልን ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው፡፡ በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሳበት ገደለውም፡፡ እግዚአብሔርም ቃየንን አለው ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ አላውቅም የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን? አለውም፡፡ ምን አደረገህ የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምደር ወደ እኔ ይጮኻል” ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ4፣ 9-11

የቡዙሃኑ ዝምታና አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንደ አልሰማ መሆን ዋጋ እያስከፈለን እንደ ሆነ ቢያንስ ያለፉት ስድስት ወራቶች የማያስተምረን ከሆነ መቼ አንማርም ባይ ነኝ፡፡ አቶ ጀዋር ኢትዮጵያ ሁለት መንግስት አላት ብሎ አፉን ሞልቶ ሲናገር እና በአገራችን  ኢ-መንግስታዊ መሆን ሲሻው ምንግስት እንኮን ዝም ቢለው  ሁላችንም በምንችለው መንገድ ሃይ ልክህን እወቅ ከልክ አለፍክ ብንለው ኖሮ ባለፉት ሁለት ሳምንታትና አሁንም እያየነው ያለው አሳዛኝ ነገር በአገራችን ህዝብ ላይ ባልተፈጸመ ነበር፡፡ የቡዙዎቻችን ዝምታ ለማንወጣው ጸጸት ዳረገን ብል ማጋነን አይሆንም።

ሰሞኑን በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት የአሜሪካ ሴኔተሮች በጀዋር መሐመድ ላይና በአሸባሪነትና የሚመራውን OMN ሚዲያን አወገዙ። እነዚሁ ሴናተሮች በአገራችን ኢትዮጵያ የደረሰውን ሰቅጣጭ ግድያ አጥብቀው ያወገዙ ሲሆን እግረ መንገዳቸውን የጀዋር ቀኝ እጆችና እርዳታ የሚለግስትንም ጭምር ግልጽ አድረገዋል።  የአገራችን የፊደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ስሙን ጠርቶ እምነት ክህደቱን ለመጠየቅ ፍርድ ቤት ማቆም ያቃተውን አቶ ጀዋርን የአሜሪካ ሴነተሮች ስሙን በመጥቀሰ የሚያዘውን OMN ሚዲያ ጭምር ተጠያቂ መሆን እንዳለበት በአደባባይ ተናግረዋል። በኔ እምነት እነዚህ ሴኔተሮች “ይህቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም ” የሚለውን የአባቶቻችንን አባባል እየገባቸው ከመጣ ሰንበትበት ያሉ ይመስለኛል።

 የሴነተሮቹን ግጻጼ ለማድመጥ ሊንኩን ይጫኑ https://www.facebook.com/FRESENAY.NET/videos/1382936941864196/UzpfSTEwMDAwMDk2MDI2MDYyNTozMTAzNzMwMjk2MzM1NjE1/

በአገራችን በኢትዮጵያ መንግስት አለ ብለን የምናምንም ሆነ የማናምን አገርንና ህዝብን ለመጠበቅ  ሁላችንም አንድ ሆነን ዘብ ለመቆም ለነገ የምንለው ጉዳይ እንዳልሆነ ከሰሞኑ ክስተት ልንማር ይገባል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የአገሬ እና የህዝቤ ጉዳይ ያገባኛል ብሎ እየተናበበ መዳራጀት አለእት፡፡ ከተደራጀ ደሞ  ከአገርና ከህዝብ አልፎ አጣቢቅኝ ውስጥ ያለውን የጠ/ሚ አብይንም መንገስት ይታደጋል የሚል እምነት አለኝ። በሌላ በኩል ደሞ ጠ/ሚ አብይም ወቅቱን የዋጀ ግራና ቀኙን ያገናዘበ ነው የሚሉትን የመደመር ፍልስፍናን በድርጅታቸውና በውስጣቸው ማን እየተከተለ እንደሆነና ማን ከመደመር ይልቅ ወደ መቀነስ ፍልስፍና እየወሰደው እንደሆነ ተረድተው አቆማቸውን ቢያስተካክሉ ያጡትን የህዝብ ደጋፍ ለማግኘት ቡዙም አያስቸግረቸውም ባይ ነኝ። እንኮን ያጡትን የህዝቡን ድጋፍ ይቅርና አብረው ለውጥ አምጥተው ወደ ሖላ ላይ ያጦቸውን የትግል ጎዶቻቸውን ለምሳሌ አቶ ለማ መገርሳ እና አቶ ሽመልስ አቢዲሳን ጭምር መልሰው ያገኞቸዋል የሚል እምነት አለኝ ምክንያቱም በፖለቲካ ውስጥ ዥዋዥዊ መጫወት ያለና የሚጠበቅ ነው እነዚህም የለውጡ አካሎች የነበሩ ሰዎች በአሁን ሰዓት ዥዋዥዊ እየተጫወቱ ይገኛሉ በመጨረሻም ወደ አሸናፊው ዘለው ይወርዳሉ ባይ ነኝ።

እኔ ጠ/ሚ አብይ አሸናፊ ሆነው ይወጣሉ የሚል እምነት አለኝ። ያ ሳይሆን ቀርቶ አቶ ጀዋር አሸንፎ ከወጣ ለመቀጣጫ ይሆኑ ዘንድ የመጀመሪያው የሞት ቅጣት የሚፈጸምባቸው ጠ/ሚ ሲሆነ ተከታዮቹ አቶ ለማና አቶ ሽመልስ ይሆናሉ ይህንን ለማለት ነብይ መሆን አይጠበቅብንም ኮ/ል መንግስቱም ሆኑ ሞቹ ጠ/ሚ አቶ መለስ አድርገውታል ባይ ነኝ። ባይሆን ያን ግዜ የገሬ ሰው “አውቀሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ” የሚለውን የአቦው አባባል እየተረተ ወደ ሞት ሽረት ትግል ውስጥ ይገባል እንጂ በአክራሪዎች አይገዛም።

“ምን የሚሉት ነገር ነው ሁለት አውራ ከቤት

አንዱ ተሸንፎ ካላለ አቤት አቤት” (የህዝብ ግጥም )

በኔ እይታ አቶ ለማም ሆኑ አቶ ሽመልስ አብዲሳን እንዲሁም ሌሎቹ በአቶ ጀዋር የተጠለፉት ምክንያት ከጠ/ሚ አብይ መዘናጋትና አስቀድሞ ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ ከለመገመት የመጣ ነው ባይ ነኝ። አቶ ጀዋር እነዚህን ሰዎች ወደ እርሱ ጎራ ያስገባቸው በአንድ ቀን ለሊት አሊያም በአንድ ግዜ አይደለም ግዜ ውስዶ እያንዳንዱን ግለሰብ በተናጠል እየቀረበና እንዲሁም የኔ የሚላቸው እንደነ ፕ/ር ኢስቄል እንደነ ዶ/ር ገመችንና ለሎችን ጭምር በጡት አባትነት በመላክና በማሳመን ነው የሚል እምነት አለኝ። እንደ እውነቱ ከሆነ አቶ ጀዋር የኔ የሚለው የፖለቲካ እውቀት ባይኖረውም የሱ የሆነ የአክቲቭስትነት እውቀት አለው ያ ማለት ግን ኩሩውን የኦሮሞ ህዝብ ይመጥናል ማለት አይደለም።

ይህ የአክቲቭስትነት እውቀቱ የሚመሳሰለው ነፍሳቸውን ይማረውና አገራችንን ኢትዮጵያ ይህቺ አገር እያሉ ከሃያ አመት በላይ እንደገዞት እንደ አቶ መለሰ ዓይነት የመለያየት እውቀት ነው። አቶ መለስ የኔ በሚሉት አስተሳሰባቸው የዘሩት የመለያየት አዘዕርት እሸቶና እፍርቶ ይህው መሰብሰቡ ለአገርም ለህዝብም አስቸጋሪ በሆነበት ሰዓት አቶ ጀዋርና ደምበኞቹ  ደሞ ከድጡ ወደ ማጡ ሊወስዱን ግብ ግብ ይዘዋል።

በኔ እምነት አቶ ጀዋር በአገራችን የፊደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በኩል ፍርድ ቤት ተከሶ ቀርቦ እሱ አገር ውስጥ ከገባ ጀምሮ በእርሱ ቀስቃሽነት ለተገደሉት ንጹሃን ዜጎቻችን ተጠያቂ መሆኑን የእምነት ይክህደት ቃሉን እንዲሰጥ ማድረግ አለበት ይህንን ሳያደርግ ቢቀር ግን የአገራችን የፊደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እራሱ የግዜ ጉዳይ ይሆን እንደሆነ ነው እንጂ በኑጹሃን ዜጎቻችን ከመጠየቅ አያመልጡም። አቶ ጀዋርም ሊያውቀው የሚገባው የነዚህ የንጹሃን ደም እንደ አቤል ደም ከምድር  ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔርም ዘንድ ሄዶ እይጮኻ እንዳለ መገንዘብ አለበት። ደማቸውም ደመ ከልብ ሆኖ አይቀርም የሚል እምነት አለኝ።

በማለት የዛሬውን ጽሁፍ ላብቃ

ቸሩ እግዚአብሔር አገራችንን ኢትዮጵያ ይጠብቅልን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.